Quantcast
Channel: Zehabesha Amharic » Health
Viewing all 281 articles
Browse latest View live

Health: የአሳ የጤና በረከቶች

$
0
0

Fish
በፋሲካው ታደሰ

አሳ በፕሮቲን ይዘቱ ወደር የማይገኝለት እንደሆነ ይነገራል።

ዝቅተኛ የካሎሪ መጠን መያዙም በበርካቶች ዘንድ ተመራጭ አድርጎታል።

አሳ መመገብ ኦሜጋ 3 ፋቲ አሲድ፣ ካልሲየምና ሌሎች በርካታ ሚኒራሎችን እንድናገኝ ያስችላል።

ቆዳችን ለስላሳ፣ ተለጣጭና ያማረ እንዲሆንም አሳን መመገብ ይመከራል።

የባህር ውስጥ ምግቦች በኦሜጋ 3 ፋቲ አሲድ የበለጸጉ ናቸው።

ይህ ጠቃሚ ፋት ደግሞ በደም ውስጥ ያለውን ትራይግላይሴራይድ በመቀነስ የልብ እና የአዕምሮ ጤናን ይጠብቃል።

የባህር ውስጥ ምግቦች በቫይታሚን እና ሚኒራሎች የበለጸጉ ሲሆን፥ ለተሻለ የአይን እይታ እና ድብርትን ለመከላከል ይረዳል።

አንዳንድ አሳዎች ሪቦፍላቪን እና ኒያሲን የተባሉ ቫይታሚኖችን እንዲሁም አይረን (ብረት)፣ ፎስፎረስ እና ፖታሲየም የተባሉ ንጥረ ነገሮችን ይዘዋል።

እነዚህ ቫይታሚኖችና ሚኒራሎች በእድሜ የገፉ ሰዎች ላይ የሚከሰቱ እንደ አርትራይተስ፣ ካታራክት (የአይን ህመም) እና የልብ ህመሞችን ለመከላከል ያግዛሉ።

አሳን መመገብ ከዚህም በተጨማሪ የመርሳት ህመም (አልዛይመር)ን ለመከላከልና የህጻናትን የአዕምሮ እድገትን ለማፋጠንም ከፍተኛ ድርሻ አለው።

ህጻናት የአሳ ዘይት ቢወስዱ የአስተሳሰብ አድማሳቸው እንደሚሰፋ የሚነገር ሲሆን፥ ይሁን እንጂ ለህጻናቱ የሚሰጠው የአሳ ዘይት መጠን በባለሙያዎች ሊታዘዝ ይገባል።

አሳ የቆዳና ጸጉር ጤናን ለመጠበቅም አይነተኛ ድርሻ እንዳለው መረጃዎች ይጠቁማሉ።

በርካታ ጥናቶች እንዳረጋገጡት ድብርትን ለማጥፋት የኦሜጋ 3 ፋቲ አሲድን መጠቀም በተለይ በአሜሪካ እየተዘወተረ ነው።

በቫይታሚን ዲ የበለጸገው አሳ የአጥንት ጥንካሬን በማሳደግ ረገድም ጠቀሜታው የጎላ ነው ተብሏል።

ምንጭ፡- http://www.everydayhealth.com እና http://www.mahderetena.com

The post Health: የአሳ የጤና በረከቶች appeared first on Zehabesha Amharic.


Health: 6ቱ የእርጎ የጤና በረከቶች

$
0
0

Yogurt Health Benifts
እርጎ አቅም በሚያጎለብት ፕሮቲንና የአጥንት ጤናን በሚጠብቅ ካልሲየም የበለጸገ ነው።

እርጎ ከሚሰጣቸው ዘርፈ ብዙ ጠቀሜታዎች መካከል የተወሰኑትን እንመልከት።

1. ክብደት ለመቀነስ ያግዛል

የሰውነት ክብደት ለመቀነስ እርጎ ጠቀሜታው የጎላ እንደሆነ ነው የሚነገረው።

በቅርቡ በቲኔስ ዩኒቨርሲቲ የተደረገ ጥናት እርጎ የያዘው አሚኖ አሲድ ስብን በማቅለጥ ያልተፈለገ ውፍረትን ለመቀነስ እንደሚረዳ አረጋግጧል።

2. ጎጂ ባክቴሪያዎችን ይገድላል

በእርጎ ውስጥ የሚገኙ ባክቴሪያዎች በአንጀታችን ውስጥ ጉዳት የሚያስከትሉ ደቂቅ ዘአካላትን (ማይክሮ ኦርጋኒዝምስ) ለማጥፋት ይረዳል።

3. በቫይታሚን የተሞላ ነው

እርጎ ፖታሲየም፣ ፎስፎረስ፣ አዮዲን፣ ዚንክ እና ቫይታሚን ቢ5 በመያዝም ወደር የማይገኝለት የምግብ አይነት ነው።

የነርቭ ስርአትን ለማስተካከልና የቀይ የደም ህዋሳትን ቁጥር ለማሳደግ የሚረዳውን ቫይታሚን ቢ12 መያዙም ይነገርለታል።

4. ከስራ በኃላ ዘና የማለት ስሜትን ይፈጥራል

በፕሮቲን እና ካርቦሃይድሬት የተሞላው እርጎ በመክሰስ ስአት ቢወሰድ ይመከራል።

ከስፖርታዊ እንቅስቃሴ በኃላም እርጎን መጠጣት ለአጥንት ጥንካሬ ያግዛል።

5. የደም ግፊትን ይቆጣጠራል

በየቀኑ የምንወስደው ከመጠን ያለፈ ጨው የሚያስከትላቸውን የኩላሊት እና የልብ ህመም ለመቀነስም ከእርጎ የምናገኘው ፖታሲየም ከፍተኛ አስተዋጽኦ አለው።

6. መልካም ፈገግታን ያላብሳል

እርጎ ምንም እንኳን የስኳር ይዘት ቢኖረውም ጥርስን ግን አያጠቁርም።

ከእርጎ ውስጥ የምናገኘው ላክቲክ አሲድም ጥርስን የሚያጠቁሩና የሚያበሰብሱ ጀርሞችን ለመግደል ያግዛል።

ምንጭ፡- http://www.fitnessmagazine.com

The post Health: 6ቱ የእርጎ የጤና በረከቶች appeared first on Zehabesha Amharic.

Health: ለአፍ ጠረን መንስኤ የሆኑ 16 ክስተቶችና ህመሞች -የዶክተሩ ትንታኔ

$
0
0

ይህ ጽሁፍ በዘ-ሐበሻ ጋዜጣ የጁን ዕትም ላይ ታትሞ ወጥቷል::

የህክምና ባለሙያዎቹ ‹‹ሃሊቶሲስ›› ይሉታል፡፡ ቃሉ ‹‹ትንፋሽ›› የሚል ትርጉም ካለው ሃልተስ ከተባለው የላቲን ቃልና መጥፎ ሁኔታን ከሚያመለክተው ኦሲስ ከተባለው ባዕድ መድረሻ ነው፡፡ ብዙው የህብረተሰብ ክፍል መጥፎ የአፍ ጠረን በሚል ያውቀዋል፡፡ መጥፎ የአፍ ጠረን አለዎት? ሌሎች ሰዎች መጥፎ የአፍ ጠረን እንዳላቸው ለማወቅ አስቸጋሪ ባይሆንም የራስዎን ሁኔታ ማወቅ ግን ሊያዳግትዎ ይችላል፡፡ የአሜሪካ የጥርስ ህክምና ማህበር መጽሔት ከራሳችን መጥፎ የአፍ ጠረን ጋር እንደምንለማመድና ‹‹አፋቸው በጣም የሚሸት ሰዎች እንኳ ችግራቸውን ላያውቁት እንደሚችሉ›› ገልጿል፡፡ ስለዚህ አብዛኞቻችን መጥፎ የአፍ ጠረን ያለን መሆኑን የምናውቀው አንድ ሰው ስለሁኔታው ሲነግረን ነው፡፡ ምንኛ ያሳፍራል፡፡
bad breath
መጥፎ የአፍ ጠረን የብዙ ሰዎች ችግር መሆኑ ብቻ መጽናኛ የአፍ ጠረን አስነዋሪና ተቀባይነት የሌለው ነገር ተደርጎ ይታሰባል፡፡ አንዳንድ ጊዜ ከባድ የስሜት መቃወስ ሊያስከትል ይችላል፡፡ በእስራኤል የቴል አቪቭ ዩኒቨርሲቲ፣ የአፍ ማይክሮባዮሎጂ ላቦራቶሪ ኃላፊ የሆኑት ዶ/ር ሜል ሮዘንበርግ እንዲህ በማለት ገልፀዋል፡፡ ‹‹መጥፎ የአፍ ጠረን ግምታዊም ሆነ እውነተኛ ከህብረተሰቡ ለመገለል፣ ከትዳር ጓደኛ ለመፋታትና ራስን ለመግደል ምክንያት ሊሆን ይችላል›› ታዲያ ዛሬ ዛሬ በአዲስ አበባ በርካታ ፋርማሲዎችና ሱፐር ማርኬቶች፣ ‹‹መጥፎ የአፍ ጠረን መድሃኒት እንሸጣለን›› የሚል ማስታወቂያ ማንበብ አዲስ አይደለም፡፡ መድሃኒቶቹ ካለሐኪም ትዕዛዝ የሚሸጡ ከመሆኑ ጋር አይነትና አጠቃቀማቸው ሁሉ፣ ለራሳቸው ለሻጮቹና ሸማቾቹ ጭምር ደናገር ሲፈጥሩ ይታያል፡፡ ባለሙያዎቹ ግን ድርጊቱ ተራ የገበያ ሥራ ሲሉ ያጣጥሉታል፡፡ አንድ የጥርስና አፍ ህክምና ስፔሻሊስት ስለዚሁ ጉዳይ የሚሉት አላቸው፡፡

ጥያቄ፡- የአፍ ውስጥ ህክምና ሲባል ምን ማለት ነው?
ዶ/ር፡- ጥሩ፤ ብዙው የህብረተሰብ ክፍል የአፍ ውስጥ ህክምና ሲባል የጥርስ ሐኪም ወይም ዴንቲስት በሚል ነው የሚረዳው፡፡ ነገር ግን ዴንቲስት ከአፍ ውስጥ ህክምና አንዱ እንጂ ሁሉንም አይወክልም፡፡ ስለዚህ አፍ እና በአጠቃላይ ከአንገት በላይ ያለው የሰውነታችን ክፍል በተመለከተው ‹‹ከአንገት በላይ ህክምና›› የሚባለው አጠራር ትክክል ሳይሆን አይቀርም፡፡ በእንግሊዝኛውም ENT በሚባል አህጽሮተ ቃል ይታወቃል፡፡ E- ear N- nose T- throut የሚባለው መሆኑ ነው፡፡ ከዚህ በቀር ግን ኢፍታሞሎጂስት (ዓይን)ን እንዲሁም በህክምናው ዓለም ጠጣሩ የአዕምሮ /ኒውሮሎጂስት/ ሳይንስ፣ ራሳቸውን የቻሉ የአንገት በላይ ህክምና ክፍሎች መሆናቸውን መዘንጋት አይገባም፡፡ የእኛ ስፔሻሊቲ ግን አፍ ውስጥ እና የፊት አካባቢ አጥንቶች ናቸው፡፡

ጥያቄ፡- የአፍ ውስጥ በሽታ መንስኤን ቢነግሩን?
ዶ/ር፡- የአፍ ውስጥ በሽታ /ፓረንዶንታል ዲዚስ/ የምንለው ጥርስ አቃፊ አካባቢ ያለው ህመም ነው፡፡ የሰው ልጅ ከተወለደ ከጥቂት ሰዓታት በኋላ ጀምሮ ከ300 ባክቴሪያዎች በላይ ሰውነታችን ውስጥ ገብተዋል፡፡ እነዚህ ባክቴሪያዎች በተለያዩ የሰውነት ክፍሎችን ከመሰራጨታቸው ጋር በአፍ ውስጥም ቦታ አላቸው፡፡ ስኳር ነክ የሆኑ ምግቦችን ስንመገብ ቶክሲክ የሆኑ ባክቴሪያዎች ወደ አሲድነት ይለውጡታል፡፡ ለጥርስ መቦርቦርም እነዚህ አሲዶች ዋና ድርሻ አላቸው፡፡ ስለዚህ ምግብ ተመግቦ ሳያፀዳ የተኛ ማንም ሰው በዚህ አሲድ ምክንያት ጥርሱ ሊቦረቦር ይችላል ማለት ነው፡፡
ሁለተኛውና ትልቁ ደግሞ ሌሊት ስንተኛ የምራቅ መጠናችን ስለሚያንስ ካልሲየምና ፎስፈረስ በየጥርስ ዙሪያችን ይከመራሉ፡፡ እነዚህም በተገቢው ሁኔታ ከቁርስ በኋላ ካልፀዱ የጥርስ በሽታን አምጪ ናቸው፡፡ ስለዚህ ማንም ሰው በ24 ሰዓት ውስጥ ሁለት ጊዜ ጥርሱን እንዲያፀዳ ይመከራል፡፡ በመሀሉ ምንም አይነት ምግብ ከተመገብን በኋላ አፋችንን በውሃ መጉመጥመጥ አለብን፡፡ ለሶስት ተከታታይ ቀናት ጥርሱን ያላፀዳ ሰው በአራተኛው ቀን ማጽዳት ቢሞክር ቆሻሻው ስለሚለጠፍ ብሩሹም ሊያስወጣለት አይችልም፡፡ ስለዚህ ከግል እንክብካቤ ባሻገር በየስድስት ወሩ ደግሞ ሐኪም ዘንድ ቀርቦ ስኬሊንግ /ማጽዳት/ የአፍ ውስጥ ጤንነትን ማረጋገጥ ይችላል፡፡

ጥያቄ፡- የአፍ ውስጥ ህክምና ከጥርስ ህክምና ይለያል ማለት ነው?
ዶ/ር፡- አዎ! ይሄንንም በቅጡ መረዳት ይገባል፡፡ አንድ ካርዲዮሎጂስት ጋ የሚሄድ ታካሚ ልቤን ስላመመኝ መድሃኒት ጻፍልኝ፣ እኛ ጋ የሚመጠውም ጥርሴን ሙላልኝ ማለት የለበትም፡፡ ጥርስ መሙላት ማለት ህክምና ማለት አይደለምና፡፡ ለሁሉም በሽታዎች የየራሱ ሐኪም ስላለ ምን ያስፈልጋል አያስፈልግም ለሙያተኛው ቢተው ነው የሚሻለው፡፡

ጥያቄ፡- ለጥርስና ለአፍ ውስጥ በሽታዎች ምክንያት የሆኑትን ምግቦች ማወቅ እንችላለን?
ዶ/ር፡- አይ! ይሄ በአጠቃላይ ከህብረተሰባችን የአኗኗርና የአመጋገብ ዘዬ መለወጥ ጋር ተያይዞ መታየት ያለበት ነገር ነው፡፡ እንደሚታወቀው ሁሉ በአሁኑ ወቅት ብዙ የምግብ ግብአቶቻችን የገበያ ወይም የሱፐር ማርኬት ውጤቶች ናቸው፡፡ እነዚህ የምግብ ግብአቶች ደግሞ ቀጥታ ፕሮቲናቸው የወጣ በመሆኑ ለሰውነት ያላቸው ጠቀሜታም የዚያን ያህል አይደለም፡፡ ለምሳሌ ቀደም ባለው ዘመን እናቶች በቤት ውስጥ ጋግረው ሲያበሉን የቆየው ኦርጋኒክ ዳቦና አሁን በዳቦ ቤቶች ወይም ሱፐር ማርኬቶች ተዘጋጅተው የምንመገባቸው ዳቦዎ እኩል ጠቀሜታ አላቸው አይባልም፡፡ ሌሎቹንም የምግብ አይነቶች እንዲሁ ማየት ይቻላል፡፡ በጥቅሉ ፕሮሰስድ የሆኑ ምግቦች በቀላሉ ጥርስ ላይ የመጣበቅና የመጠራቀም ባህሪይ እንዳላቸው ነው፡፡ ስለዚህ ከላይ እንዳልኩት እነዚህን በወቅቱ ካላፀዳን ይለጠፉና ወደ ፓራንዶንታል ዲዚስ /ጥርስ ዙሪያ/ በሽታ ይሸጋገራል ማለት ነው፡፡ እንግዲህ ይህን ስል በሽታውን ያመጣው ምግቡ ሳይሆን ምንም ተመገብን ምንም ጽዳት ካደረግን ምንም በሽታ አይኖርም ነው፡፡

ጥያቄ፡- በባህል ሁኔታ ጥርሳችን የምንፍቅባቸው እንጨቶችስ ምን ያህል ጠቀሜታ አላቸው?
ዶ/ር፡- እስካሁን የተናገርኩት ከምግብ በኋላ ጥርስን ማጽዳት ተገቢ መሆኑን ነው፡፡ በዚህ ረገድ ጥርሱን ምንም ከማያፀዳ ባህላዊ ጥርስ መፋቂያዎች የተሻሉ መሆናቸውን አውቃለሁ፡፡ እርግጥ የጥርስ መፋቂያ እንጨቶች ቆሻሻል በመቀነስ አስተዋፅኦ ያላቸው ቢሆንም፣ ጫን ተብለው በተያዙ ቁጥር ድድን በመክፈት ሌላ ችግር ማስከተላቸው አይቀርም፡፡

ጥያቄ፡- የጥርስ ብሩሽ ሳሙና አፍ ያሸታል የሚባለውስ?
ዶ/ር፡- ስህተት ነው፡፡ ብሩሽና ሳሙናውን ያዘጋጁት እኮ በሳይንስ የኖቤል ተሸላሚ የሆኑ ሳይንቲስቶች ናቸው፡፡ በብሩሹ ደረጃ ጠንካራ፣ ለስላሳና መካከለኛ የሆኑ አሉ፤ ይህም እንደ አመራረጡ ነው፡፡ ሳሙናውም በይዘት ያካተተው ፍሎራይድ የመሰለ ለጥርስ ተፈላጊ የሆነ ኤለመንትና ፀረ ባክቴሪያዎች አሉት፡፡

ጥያቄ፡- በአሁኑ ወቅት በብዙ የከተማችን ፋርማሲዎችና ሱፐር ማርኬቶች ‹‹የአፍ ጠረን መድሃኒት እንሸጣለን›› የሚል ማስታወቂያ ጽፈው እያየን ነው፡፡ እስቲ ስለ አፍ ጠረን መድሃኒት ትንሽ ቢያብራሩልን?

ዶ/ር፡- ‹‹የአፍ ጠረን መድሃኒት አስመጥተናል›› ማለት በሌላ አነጋገር የሞተ አይጥ ሽታ የሚያጠፋ መድሃኒት እንሸጣለን ማለት ነውኮ፡፡ ስለዚህ እነዚህ ሰዎች የአፍ ሽታ ምክንያቱን አላውቁም፡፡ ባለማወቃቸውም ጉዳዩን ለገበያ ተጠቅመውበታል ማለት ነው፡፡ ባይሆን እንኳ ሐኪሙ የአፍ መጉመጥመጫና ሌሎች የሚያዛቸው አሉ፡፡ አሁን እያየን እንዳለነው አንዳንድ የህብረተሰብ ክፍል ሐኪም ቀርቦ ከመታየት ይልቅ በገበያ ማስታወቂያዎች ተማልሎ በራሱ ላይ ተጨማሪ በሽታ በመሸመት ላይ ይመስላል፡፡ አንዳንድ ፋርማሲስቶችም ከሐኪም ትዕዛዝ ውጭ መሸጥ የሌለባቸውን መድሃኒቶች እንደሚሸጡ ይታወቃል፡፡ አንድ ጊዜ የታዘዘ መድሃኒትን ደጋግመው የሚገዙና የሚጠቀሙ ሰዎች ቁጥርም ቀላል የሚባሉ አይደሉም፡፡ እንደዚሁ ሁሉ የሀገር ውስጥና የውጭ መድሃኒቶች በሚል ተጨማሪ ዋጋ የሚጠይቁ እንዳሉ የማናውቅ አይደለንም፡፡ ለእኔ ግን ይህ ሁሉ ከባድ ስህተት ነው ባይ ነኝ፡፡

እንግዲህ በገበያ ላይ የሚገኙ የአፍ መጎመጥመጫዎች ሊጠቅሙ ቢችሉም መጥፎ የአፍ ጠረንን በመከላከል ረገድ ሙሉ በሙሉ ልትተማመንባቸው እንደማትችል በቅርብ ጊዜ የተደረጉ ጥናቶች ያሳያሉ፡፡ እንዲያውም ብዙውን ጊዜ አልኮል ባለባቸው መጉመጥመጫዎች መጠቀም የአፍ ድርቀት ሊያስከትል ይችላል፡፡ አንዳንድ በጣም ውጤታማ ናቸው የሚባሉ የአፍ መጉመጥመጫዎች በጥርስ ላይ የሚላከኩ ቆሻሻዎችን መቀነስ የሚችሉት 28 በመቶ ብቻ ነው፡፡

ስለዚህ የምትመርጠውን የአፍ መጉመጥመጪያ ከተጠቀምክ በኋላም ቢሆን በአፍህ ውስጥ ከነበሩት ባክቴሪያዎች ውስጥ ከ70 በመቶ በላይ የሚሆኑቱ ላይጠፉ ይችላሉ፡፡ በተለያዩ ጊዜያት በተደረጉ ሙከራዎች መሰረት በአፍ መጉመጥመጪያ ተጠቅሞ ጥርስንም ካፀዱ ከ10 ደቂቃ እስከ አንድ ሰዓት ባሉት ጊዜያት ውስጥ መጥፎ የአፍ ጠረን እንደሚያገረሽ ነው፡፡

በግልጽ መረዳት እንደሚቻለው መጥፎ የአፍ ጠረንን በመከላከል ረገድ ግዴለሽ መሆን አያስፈልግም፡፡ ከዚህ ይልቅ አፍህንና ጥርስህን ዘወትር እንክብካቤ እንደሚያስፈልጋቸው ውድ መሳሪያዎች አድርገህ መያዝ ይኖርብሃል፡፡ ስለዚህ የሚገባቸውን እንክብካና ጥንቃቄ አድርግላቸው፡፡ እንደህ ካደረግህ መጥፎ የአፍ ጠረንንና በዚሁ ሳቢያ የሚመጣውን ጭንቀትና ሐፍረት ትቀንሳለህ፡፡ ከዚህም በላይ አፍህ ንፁህና ጤነኛ ይሆናል፡፡
ጥያቄ፡- አመሰግናለሁ፡፡
ዶ/ር፡- እኔም አመሰግናለሁ፡፡

The post Health: ለአፍ ጠረን መንስኤ የሆኑ 16 ክስተቶችና ህመሞች -የዶክተሩ ትንታኔ appeared first on Zehabesha Amharic.

Health: የቴምር (Dates) 10 የጤና በረከቶች

$
0
0

dates  copy
በርካቶቻችን በብዛት የምንጠቀመው እና በተለይም በረመዳን ጾም ወቅት በእስልምና እምነት ተከታዮች ዘንድየሚዘወተረው ቴምር በርካታ የጤና ጠቀሜታዎች አሉት።

በቫይታሚን፣ ማዕድናትና የተለያዩ ንጥረ ነገሮች የበለጸገ መሆኑ በርካታ የጤና ጠቀሜታዎች እንዲኖሩት አስችሎታል፡፡…ለምሳሌ ያህል…

1) ስብና ኮልስትሮል፡ ከየትኛውም የኮልስትሮል ዓይነቶች የጸዳና በጣም አነስተኛ የስብ መጠን ያለው መሆኑ ክብደት መቀነስ ለሚፈልጉ ተመራጭ ነው፡፡

2) ፕሮቲን፡ ቴምር በፕሮቲንና አስፈላጊ ማዕድናት የበለጸገ መሆኑ ለሰውነት እጅጉን ጠቃሚ ያደርገዋል፡፡

3) ቫይታሚን፡ በቫይታሚን የበለጸገ ነው ቴምር፡፡ ከቫይታሚን ዓይነቶች ቢ1፣ ቢ2፣ ቢ3፣ ቢ5፣ ኤ1 እና ሲ ንም አካትቶ ይዟል፡፡

4) ሀይል እና ጉልበት፡ ቴምር ቀላል የማይባል የሀይል ክምችት ስላለውም ንቁና በሀይል የተሞላን እንድንሆን ያስችለናል፡፡

5) ፖታሲየምና ካልሲየም፡ ቴምር የፖታሲየም ክምችቱ ከፍተኛ ነው፡፡ ይህም በልብ በሽታ እንዳንጠቃና አካላችን ውስጥ ያለው የኮልስትሮል መጠን እንዲቀንስ ይረዳል፡፡ ቴምር በአንጻሩ አነስተኛ የሶዲየም መጠን ነው ያለው፡፡ ብዙ ፖታሲየምና ትንሽ ሶዲየም ደግሞ ለጤናማ የነርቭ ስርዐት ወሳኝ ነው፡፡

6) ብረት፡ ቴምር በብረትና በፍሎሪን የበለጸገ መሆኑ ደግሞ ብረቱ የብረት ማዕድን እጥረት ላለባቸው ሰዎች፣ ፍሎሪኑ ደግሞ ጥርስን ከመበስበስ ይከላከላል፡፡

7) ድርቀት፡ ለድርቀትም ቢሆን ውሀ ውስጥ የተነከረ ቴምር መመገብ ፍቱን እንደሆነ ይታወቃል፡፡

8) ሰውነትን ማጽዳት፡ በአልኮል መጠጣት ሳቢያ ሰውነት ውስጥ የሚከማቸውን መርዛማ ኬሚካሎች ከሰውነታችን ውስጥ በማስወገድም ይረዳል – ቴምር !

9) ካንሰር እና የዓይን ችግር፡ የዓይን ህመም ችግርንና የሆድ ነቀርሳ (ካንሰር)ን ለማከምም ብቃት እንዳለው ይታወቃል – ቴምር፡፡

10) (የቆዳ ችግር) ቴምር የቆዳ ችግሮችን በማስወገድም መልካም ዝና አለው፡፡ ጸጉርን በማፋፋት የጸጉር መሳሳትንም ይከላከላል፡፡

በርከት ያሉ ቪታሚኖችን እና ሚኔራሎች በመያዙ ለጤናችን በርካታ ጠቀሜታዎች እንዳሉት ይነገርለታል። ሀይል ሰጪ፣ ፋይበር፣ እንዲሁም ካልሺየም፣ አይረን፣ ፎስፈረስ፣ ሶዲየም፣ ፖታሲየም፣ ማግኒዚየም፣ እና ዚንክ ሚኔራሎች በቴምር ውስጥ የሚገኙ በመሆኑ ቴምርን ለጤና ጠቃሚ ያደርጉታል። ስለዚህም ቴምርን አዘውትረን መመገብ ለጤናችን ከሚሰጠው ጠቀሜታዎች ውስጥም፦
የሆድ ድርቀትን ይከላከላል
ቴምር በባህሪው የማለስለስ ባህሪ ስላለው ምግብ በአንጀታችን ውስጥ በቀላሉ እንዲዘዋወር በማድረግ የሆድ ድርቀት ለመከላከል ይረዳል። ለዚህም ይረዳን ዘንድ ቴምሩን በውሃ
ውስጥ ዘፍዝፈን በማሳደር ጠዋት ላይ መመገብ ይመከራል።

ለአጥንት ጤንነት እና ጥንካሬ
በቴምር ውስጥ የሚገኙት ሚኔራሎች ለአጥንታችን ጥንካሬ እና ጤነነት እጅጉን ጠቃሚ እንደሆኑ ይነገራል። ቴምር እንደ ሴሌኒየም ማንጋኒዝ፣ ኮፐር እና ማግኒዚየም ማእድናትን በውስጡ በመያዙም ለአጥንት ጤናማ እድገት እና ጥንካሬ ጠቃሚ ነው።

ደም ማነስን ይከላከላል

ቴምር በውስጡ በያዘው ከፍተኛ የምግብ ማእድናት ንጥረ ነገቾች ክምችት የደም ማነስ ችግር ላለባቸው ሰዎች እጅጉን ጠቃሚ ነው።

አለርጂን ይከላከላል
ቴምርን ከሌሎች ለየት የሚያደርገው አለርጂን ለመከላከል የሚረዳውን ሰልፈር ንጥረ ነገር በውስጡ በመያዙ ነው። ስለዚህም ቴምርን አዘውትረን የምንመገብ ሰዎች ለተለያዩ አይነት አለርጂዎች የመጋለጥ እድላችን እጅጉን እንዲቀንስ እንደሚያደርገው ይነገርለታል።

ለነርቭ ጤንነት

በቴምር ውስጥ የሚገኙት ቪታሚኖች የተስተካከለ እና ጤናማ የነርቭ ስርዓት እንዲኖረን ስለሚያደርግም ለጤናችን ጠቃሚ ያደርገዋል።

ለልብ ጤንነት
ቴምር ለልባችን ጤንነት በርካታ ጠቀሜታዎች ስላሉት ተመራጭ ያደርገዋል።

ቴምር የልብ ጤንነትን ይጎዳል የሚባለውን የኮሌስቴሮል መጠን የመቀንስ እቅም ስላለው ለድንገተኛ የልብ ህመም እንዳንጋለጥ በመርዳትም ለልባችን ጤንነት ጠቀሜታ አለው።
ስንፈተ ወሲብን ይከላከላል

ጥናቶች እንደሚያመለክቱት ከሆነ ቴምር በውስጡ በያዘው ንጥረ ነገሮች አማካኝነት የሰዎችን የወሲብ ፍላጎት ከፍ እንዲል እና የወሲብ ፍራቻ ላለባቸው ሰዎች ድፍረትን እንዲያገኙ በማድረግ ስንፈተ ወሲብን ለመከላከል ይረዳል።

በእርግዝና እና ወሊድ ወቅት ተመራጭ ምግብ ነው

ቴምር በእርግዝና ወቅት ለጽንሱ ጤንነት ብሎም በወሊድ ጊዜ ምጥ አስቸጋሪ እንዳይሆንና የተሻለ የማማጥ አቅም እንዲኖረን ያስችላል።

የአዕምሯችንን ጤንነት ያሳድጋል
ጥናቶች በቴምር የምናገኘው ቫይታሚን ቢ6 የተሻለ የአዕምሮ ተግባራት እንዲኖርና ሰዎች በትምህርታቸው የተሻለ ውጤት እንዲያስመዘገቡ ማገዙን ተናግረዋል።

ምንጭ፦ http:// naturalsociety.com

The post Health: የቴምር (Dates) 10 የጤና በረከቶች appeared first on Zehabesha Amharic.

Health: ቅናት ለፍቅር ምኑ ነው?

$
0
0

ብዙ ሰዎች እርር ድብን ብለን እናውቅ ይሆናል፡፡ በቅናት! ዛሬ እኔ እና እናንተ ስለ ቅናት ልናወጋ፣ በቅናት ያረርንባቸውን ጊዜያቶች በድጋሚ ልናጤን ነው፡፡ የእናንተን አላውቅም እንጂ እኔ በበኩሌ ከዚህ ቀደም የኔው ጉድ በቅናት አንፃር ያደረገችበትን ቀኖች በምናቤ እንደ ፎቶ አልበም ደርድሬያቸዋለሁ፡፡ መቼም ቀንቼ አላውቅም አትሉኝም፡፡ ቅናት መጠኑ ይብዛም ይነስም የሁላችንንም ልብ ያንኳኳል፡፡ ቅናት እና እሳት ቤት አይዘሉም፡፡ እርግጥ ነው ቅናት ውስጣችን አስደሳች ስሜት የሚፈጥር አለመሆኑን እናውቃለን፡፡ ከዚህ አኳያ ቅናትን ከአሉዊ ስሜቶች ተርታ ልንፈርጀው እንችላለን? ወይንስ ለትዳር አጋራችን ወይንም ለፍቅር ጓደኛችን ያለን ፍቅር ኃያል መሆኑን ማረጋገጫ አድርገን እንወስደዋለን? ይህንን ጥያቄ ለመመለስ ብዕሬ ጉሮሮዋን ጠራርጋለች፡፡ 

ከሁሉ በፊት ግን ስለምንወያይበት ርዕስ ግልፅ የሆነ መረጃ ሊኖረን ይገባል፡፡ ለዛም ነው ቀድመን ቅናት ምንድን ነው? የሚለውን ጥያቄ መመለስ ያለብን፡፡ 
Jealousy

ቅናት ምንድነው?

ቅናት ማለት በተቃራኒ ፆታ ግንኙነት ውስጥ እያለን በተለያዩ ምክንያቶች በውስጣችን ሊፈጠር የሚችል፣ የምንወደውን ሰው ከማጣት ጋር የተያያዘ የስጋት እና ሽብር ስሜት ነው፡፡ ቀደም ብዬ እንደጠቀስኩት ይሄ የሽብር ስሜት ነው፡፡ ቀደም ብዬ እንደጠቀስኩት ይሄ የሽብር ስሜት በተለያዩ ምክንያቶች ሊፈጠር ይችላል፡፡ በተጨማሪም ቅናት ያለንን ግንኙነት ሊጠቅምም ሊጎዳም እንደሚችል በዘርፉ የተመራመሩ ሰዎች ገልፀዋል፡፡

አሉታዊ ቅናት

ቅናትን አሉታዊ የምንልበት ዋናው ምክንያት በዓለም ላይ ከተፈፀሙ የትዳር ጓደኛ ግድያ መንስኤዎች መካከል ቅናት ፊት አውራሪ ሆኖ በመምራት ላይ ስለሚገኝ ነው፡፡ ይሄ ደግሞ ቅናት ልክ የማይኖረው ከሆነ አደገኛ ሊሆን እንደሚችል ያሳያል፡፡

ቅናትን አሉታዊ ቅናት የምንለው መቼ ነው? ቅናት ከልክ እንዳለፈ ለማረጋገጥ የተወሰኑ ምልክቶችን ልጠቃቅስ፡፡

ሀ. የቅናት ስሜት በሚፈጠርበት ወቅት ስሜታችንን ለመግለፅ ቃላትን ሳይሆን ጉልበትን መጠቀም ስንጀምር፤ በግልፅነት ከመወያየት ይልቅ ቅናት እንዲያድርብን አደረግን የምንለው ሰው ላይ ለዱላ ስንጋብዝ፡፡

ለ. የትዳር አጋርህ/ሽ፣ ጓደኛህ/ሽ ካንተ/ካንቺ ጋር በሌለ/ች ሰዓት ጊዜህን/ሽ ‹‹ምን እያደረገ/ች ይሆን?›› በማለት ቀኑን ሙሉ የምንብሰለሰል ከሆነ አልፎ ተርፎም ቀኑን ብቻ ሳይሆን ሌሊትም ኮርኒስ እየቆጠርን ነገር የምንበላ ከሆነ ችግር አለ ማለት ነው፡፡

ሐ. የቅናት ስሜት ከፍቅር የመነጨ ሳይሆን እምነት ከማጣት የመጣ ሲሆን፤

መ. የትዳር አጋርህ/ሽ ውሎውን/ዋን ለመናገር ወይም አንተ/አንቺ በሌለህበት/ሽበት ሰዓት የተፈጠሩ ነገሮችን ለመናገር የምትሳቀቅ/ቂ ከሆነ፤

ሠ. በዚህ በመዘዘኛ ቅናት ምክንያት ለምግብ ያለን ፍላጎት ከቀነሰ፤ ጭንቀት ውስጥ ከገባን፤ የልብ ምታችን በተደጋጋሚ የሚጨምር ከሆነ፣ ከልክ በላይ የሚያልበን እንዲሁም ቶሎ የሚደክመን ከሆነ፤

ረ. በመጨረሻም ቅናት ከፍቅረኛችሁ ጋር ያላችሁ ግንኙነት ላይ ክፍተት እየፈጠረ ከመጣ ችግር አለ ማለት ነው፡፡

ከዚህ በተጨማሪ ሊንዳ ብሎር የምትባል ክሊኒካል ሳይኮሎጂስት ቅናታችን አሉታዊ መሆን አለመሆኑን ለማረጋገጥ እነዚህን ሶስት ጥያቄዎች ራሳችሁን ጠይቁ ትለናለች፡፡

1. ይሄ ቅናት የዕለት ተዕለት ኑሮአችሁ ጋር እየተጋጨ ነው?

2. የምወደውን ሰው እያሳዘነ እና እየጎዳ ነው?

3. ቅናቱ እኔ ከምቆጣጠረው በላይ እሱ ይቆጣጠረኛል?

ከላይ ለተዘረዘሩት ሶስት ጥያቄዎች መልሳችሁ ‹‹አዎን›› ከሆነ ጉድ ፈልቷል ማለት ነው ትላለች የሳይኮሎጂ ባለሙያዋ፡፡

እንግዲህ ወዳጆች ከላይ የጠቀስኳቸው ነገሮች በተደጋጋሚ በፍቅር ግንኙነትሽ/ህ ጊዜ የሚከሰቱ ከሆነ ቆም ብሎ ማሰብ ያስፈልጋል፡፡ በአቅራቢያችን ወደሚገኝ የስነ ልቦና አማካሪ ብንሄድ መፍትሄ ልናበጅለት እንችላለን፡፡ አሊያም ማማከሩ ለውጥ ካላመጣ በሰላም መለያየቱ ሁሉ የሚበጅ ይመስለኛል፡፡

አዎንታዊ ቅናት

ቅናት በአብዛኛው ግንኙነቶች አደጋ ላይ ሲጥል ብንመለከተውም መጠኑ ሳይበዛ ግን አዎንታዊ ጎኑ ሊያመዝን የሚችልበት ሁኔታ ይፈጠራል፡፡ ታዲያ አዎንታዊ ቅናት ስል ደስ የሚል ስሜት የሚፈጥር ቅናት ማለቴ እንዳልሆነ ይገባችኋል፡፡ ታዲያ ቅናትን አዎንታዊ የምንለው እንዴት ነው?

አንዳንድ ጥናቶች እንደሚያትቱት መጠነኛ ቅናት በፍቅር ጓደኛ ላይ ደስ የሚል ስሜት ይፈጥራል፡፡ ምክንያቱም የፍቅር ጓደኛችንን ምን ያህል እንደምንወድ ሊያሳይ ይችላል፡፡ የፍቅር ወይም ትዳር አጋራችን መጠነኛ ቅናትን እንደ ፍቅር መገለጫ ሊመለከቱት ይችላሉ፡፡ ይሁን እጂ ብዙ ጥንዶች የተሰማቸውን ደስ የሚል ስሜት ቅናት ላደረበት አጋራቸው ሲያካፍሉት አይስተዋልም፡፡ በሌላ መልኩ ደግሞ መግባባት ባለመቻል እና ንትርክ መካከላቸው ያለው የፍቅር ድባብ የተጋረደባቸው ጥንዶች መጀመሪያ በፍቅር ሲወድቁ ለፍቅረኛቸው የነበራቸው ወይንም ስለ ፍቅረኛቸው የሚወዱትን ጎን መልሶ ለማግኘት ይቸገራሉ፡፡ ታዲያ በዚህ ወቅት ፍቅረኛቸውን ከሌላ ሰው ጋር ቢመለከቱት/ቷት በሚፈጠርባቸው የቅናት ስሜት ያ ጠፍቶ የነበረ የጠብ ምክንያት ግልጽ ሊሆን ይችላል፡፡ ስለዚህ ከዛ ሰው ጋር ያላቸውን ግንኙነት እንዲያድሱ ያስገድዳቸዋል፡፡ ከንትርክ የበለጠ ጥሩ የጋራ ታሪክ እንደነበራቸው ያስታውሳሉ፡፡ ያንንም ጥሩ ጊዜ ለመመለስ የሚያስችል አቅም ያገኛሉ፡፡ ‹‹በእጅ ያለ ወርቅ ከመዳብ ይቆጠራል›› እንዲሉ ነው ነገሩ አንዳንዴ፡፡

የቅናት መንስኤዎች

ቅናት አዎንታዊ እና አሉታዊ ጎኖች እንዳሉት ሁሉ መንስኤዎቹም የተለያዩ ናቸው፡፡ የቅናት መንስኤ በተለይ ቅጥ ያጣ ቅናት መነሻው የፍቅር አጋራችን ላይ ከመጠን ያለፈ ጥገኛ መሆን እና በራስ መተማመን አለመቻል ነው፡፡ ይሁን እንጂ የሁሉም አፍቃሪ ቅናት መንስኤ ጥገኛ መሆን እና በራስ መተማመን አለመቻል አይደለም፡፡ አንዳንድ ድርሳኖች እንደሚያስነብቡን አዎንታዊ ቅናቶች ኃያል ከሆነ ፍቅር ሊመጣ እንደሚችል እና መንስኤውም ፍቅረኛችን ካላት/ካለው የሶስተኛ ወገን ግንኙነት ጋር ሳይሆን ሌሎች ግዑዝ ከሆኑ ነገሮች ጋር በተያያዘ ሁሉ ሊመጣ ይችላል፡፡ ለአብነት ያህል ፍቅረኛ ሆዬ በስራ ብዙ ሰዓቱን/ቷን የሚያሳልፍ/የምታሳልፍ ሲሆን ወይንም ብዙ ጊዜውን/ዋን በማንበብ የምታሳልፍ/የሚያሳልፍ ከሆነ አዎንታዊ የምንለው አይነት ቅናት ሊያድርብን ይችላል፡፡ ቅናቱም የፍቅር ግንኙነቱን የሚያቀጭጭ አይነት ቅናት አይደለም፡፡ ጊዜ ከመፈለግ ጋር የሚያያዝ ብቻ ነው፡፡ ከዚህ በተጨማሪ የቅናት መንስኤ አሁን ካላቸው ግንኙነት በፊት በነበራቸው ግንኙነት የተከዱ ወደፊት በሚኖራቸው ግንኙነት የቅናት ስሜት ሊያድርባቸው ይችላል፡፡ ይህ ቅናት በበኩሉ በአመዛኙ ከእምነት ማጣት ጋር የተያያዘ ነው፡፡

አሉታዊ ቅናትን ለማስወገድ

‹‹እርር ድብን ማለት አንገሽግሾኛል፤ ጨጓራዬን ልተፋው ነው፤ አንድ በሉኝ›› የሚሉ ከሆነ ደግሞ ቅናትን ፈፅሞ ልናጠፋው ባንችል እንኳ እንዴት ልንገራው እንደምንችል እንመልከት፡፡

1. መፍትሄው ብዙ ጊዜ ያለው እዛው ፍቅረኛችን እጅ ስለሆነ የሚስማማንን ስሜት ለፍቅረኛችን ግልፅ ማድረግ ይመከራል፡፡

2. ምክንያታዊ ለመሆን መሞከርም ጥቅም አለው፡፡ ለምን በሉኝ? ብዙ ጊዜ ቅናት ያሳደረብን ጉዳይ የሚጨበጥ ነገር ላይሆን፣ ጨርሶ ያልታሰበና ያልተፈጠረ የእኛ አዕምሮ ብቻ ያውጠነጠነው ሊሆን ይችላል፡፡ ስለዚህ የሚያስቀናንን ጉዳይ ከእውነታው ጋር በማስተያየት፣ ምክንያታዊ ለመሆን በመጣር የሚስማማንን ስሜት መርምረን ልንገራቸው እንችላለን፡፡

3. ለራሳችን ያለን ክብር ሊጨምር ይገባል፡፡ በራስ መተማመናችንን ከፍ ያደርጋሉ የምንላቸውን የሌሎችን በራስ መተማመን የማይነኩ ነገሮችን ማድረግ ጠቃሚ ነው፡፡ አለ አይደል እኛ ከፍ ብለን እንድንታይ ሌላው ዝቅ ማለት የለበትም፡፡ ሌላውን ዝቅ ሳያደርጉ እኛን ከፍ የሚያደርጉ ነገሮችን ማድረግ በራስ መተማመናችንን ይጨምራል፡፡

4. ፍቅረኛሞች በአመለካከት ስለሚለያዩ ከሶስተኛ ወገን ጋር ያላቸው የግንኙነት ገደብ ይለያያል፡፡ ስለዚህ የኛን ገደብ ባለማወቅ ፍቅረኛችን ልታስቀይመን/ሊያስቀይመን ትችላለች/ይችላል፡፡ በመሆኑም አስቀድመን የሚመቹንን እና የማይመቹንን ከሶስተኛ ወገን ጋር ያሉ ግንኙነቶች ግልፅ ማድረግ መልካም ነው፡፡

ሰላም ሰንብቱልኝማ!!

The post Health: ቅናት ለፍቅር ምኑ ነው? appeared first on Zehabesha Amharic.

Health: ድብት እያንገላታኝ ነው፤ ምን ትመክሩኛላችሁ? –ጥያቄና 3ቱ መፍትሄዎች

$
0
0

depression zehabesha
በሰላሳዎቹ መጀመሪያ የምገኝ ሲሆን ባለትዳርና የሁለት ልጆች አባት ነኝ፡፡ ወላጆቼና እኔ በአንድ ከተማ ውስጥ የምንኖር ሲሆን፣ እኔ የተከራየሁት ቤት ከቤተሰቦቼ የራቀ ነበር፡፡ እናቴ በተደጋጋሚ እያመማት ስለነበር በቅርበት ለመሆን ብዬ ቤት ተቀይሬ ወላጆቼ ያሉበት አካባ ተከራይተን ለመኖር ከባለቤቴ ጋር ወስነን ቀየርን፡፡ ይህ በሆነ በሁለት ወሩ አካባቢ እናቴ ሞተች፡፡ ከቆይታ በኋላ ባለቤቴ ‹‹እናትህ መሞታቸው ላይቀር የለመድኩትን ሰፈር አስለቅቀህ…›› ምናምን እያለች መጨቃጨቅ ጀመረች፡፡

የእኔ ሁኔታም ከጊዜ ወደ ጊዜ እየተቀየረ መጣ፡፡ አሁን መስሪያ ቤቱ በሰጠኝ የትምህርት ዕድል ተጠቅሜ በከተማችን በሚገኝ ዩኒቨርሲቲ ዲግሪዬን እየተማርኩ ነኝ፡፡ ነገር ግን ለአለባበሴ ግድ የለኝም፣ ዝም ብዬ ተስፋ እቆርጣለሁ፣ የማልጠቅም ነኝ ብዬ አስባለሁ፣ ምንም ነገር ብሰራ አልደሰትም፣ የሚታየኝ መኝታ ክፍል ገብቼ መተኛት ብቻ ነው (በጣም ረዥም ሰዓት እተኛለሁኝ)፡፡

የቀድሞ ጓደኞቼን በሙሉ ርቄአቸዋለሁ፡፡ ትምህርቴን ላጠና እፈልግና ትኩረቴ አይሰበስብም (ማጥናትም ይደብረኛል)፣ የምግብ ፍላጎትም የለኝም (በቀን አንዴ ከበላሁ ይበቃኛል)፣ ወዘተ፡፡ አሁን ደግሞ በሁኔታዬ እናደዳለሁ፣ ይጨንቀኛል፡፡ ከስነ ልቦና አንፃር ሲታይ ይህንን ለማስወገድና እንደ ቀድሞዬ ለመሆን ምን ትመክሩኛላችሁ? ለምትሰጡኝ ምላሽ ከወዲሁ አመሰግናለሁ፡፡
የሁልጊዜ ተከታታያችሁና አድናቂያችሁ ካለሁበት፡፡

መልስ፡-
ከጽሑፍህ የተገነዘብኩት፣ በእንግሊዝኛው ‹ዲፕረሺን› በአማርኛው ደግሞ ድብት ተብሎ የሚጠራው ችግር ነው፡፡ ድብት ከስሜት ጋር የተያያዙ ችግሮች፣ ምድብ የሚካተት ሲሆን በምድቡ ከተካተቱ ችግሮች ውስጥ በብዛት የሚከሰተው ድብት ነው፡፡ የድብት ምልክቶች ከሰው ሰው የሚለያዩ ቢሆንም፣ የዘርፉ ጠበብቶች ዋና ዋና ምልክቶች ያሏቸውን ለይተዋል፡፡ ከእነዚህ ዋና ዋና ምልክቶች ውስጥ፣ ሁለቱና ከዛ በላይ የሆኑት ለተከታታይ ሁለት ሳምንትና ከዛ በላይ አንተ ላይ ከተከሰቱ ድብት አለብህ ተብሎ ይወሰዳል፡፡ እነዚህ ምልክቶችም፡-

– ለነገራት የነበረን ፍላጎት መቀነስ ወይም ከዚህ በፊት ያዝናኑን የነበሩ ሁኔታዎች አሁን ደስታ አልሰጡን ማለት፣
– የድካም ስሜት መሰማት (ያለምንም ወይም በጥቂት አካላዊ እንቅስቃሴ)፣
– የማልቀስ ፍላጎት (በተደጋጋሚ ማልቀስ) እና በተደጋጋሚ መበሳጨት፤
– ብቻን የመሆን ከፍተኛ ፍላጎት፣
– የወሲብ ፍላጎት መቀነስ/ማጣት
– ለመተኛት አለመቻል ወይም እንቅልፍ ማብዛት፤
– የምግብ ፍላጎት መቀነስ ወይም በጣም መጨመር፤
– ትኩረትን መሰብሰብ አለመቻል ወይም ውሳኔ ለመስጠት መቸገር፤
– የባዶነት ስሜት መሰማት ወይም የጥፋተኝነት ስሜት መሰማት፤
– ከፍተኛ የክብደት መቀነስ ወይም መጨመር፤
– የእረፍት ማጣት ስሜት ወይም ከመጠን በታች እየሰሩ እንደሆነ መሰማት፤
እንደ አሮን ቤክ ያሉ ታዋቂ የስነ ልቦና ባለሙያዎች እንደሚያስረዱት፣ ራስን ከመጠን በላይ መመርመር፣ የአልጠቅምም ስሜትን ማዳበርና በግንኙነቶች መካከል ያልተፈቱ ችገሮች መኖር የድብት አይነተኛ ምንጮች ናቸው፡፡ እንደ ባለሙያዎቹ ማብራሪያም፣ ድብት መፍትሄ ካልተሰጠው እየተባባሰ የሚሄድና ወደ ዓለምን የመጠራጠር የሰብዕና ችግር እየተባባሰ ይሄዳል፡፡

ለድብርት የሚሰጠው ስነ ልቦናዊ ድጋፍ ዋነኛ አላማ ደግሞ፣ ግለሰቡ ስለራሱ እና ስለ ዓለም ያለውን አተያይ ማስቀየር ነው ይላሉ ጠበብቱ፡፡ በመሆኑም ጠያቂያችን የድብት ችግርህን ለመቅረፍ የሚያግዙ ሶስት በተከታታይ መተግበር ያለባቸው አቅጣጫዎችን እንጠቁምህና ተግብራቸው፡፡

የመፍትሄ አቅጣጫ 1
አስተሳሰብን መለወጥ

የተወደድክ ጠያቂያችን ሆይ! አንድን ችግር ለመቅረፍ በመጀመሪያ ደረጃ ችግሩን በሚገባ መገንዘብ ወሳኝ ነው፡፡ ስለሆነም አንተ ላይ እየታዩ ያሉ ምልክቶችን መመርመር የመጀመሪያው ተግባርህ መሆን አለበት፡፡ ይህንንም ለመከወን ወረቀት አውጣና በአንተ ላይ እየታዩ ያሉ ምልክቶችን ዘርዝረህ ፃፋቸው፡፡
ድብት በአምስት የተለያዩ የህይወት ዘርፎቻችን ላይ ምልክቶችን ያሳያል፡፡ አንደኛው በባህሪያችን ላይ ነው (ለምሳሌ ራስን ማግለል፣ ራስን መጣል፣ ወዘተ) ሁለተኛው በተነሳሽነታችን ላይ ነው፡፡ (ለምሳሌ ለነገሮች ያለን ፍላጎት መቀነስ) ሶስተኛ በስሜታችን ላይ ነው (ለምሳሌ መበሳጨት፣ መጨነቅ)፡፡ አራተኛ በአስተሳሰባችን ላይ ነው (ለምሳሌ ትኩረትን ለመሰብሰብ መቸገር)፡፡ አምስተኛ በአካላችን ላይ ነው (ለምሳሌ የድካም ስሜት፣ የምግብ ፍላጎት ማጣት)፡፡ እናም በእነዚህ አምስት ዘርፎ ላይ አንተ ላይ እየታዩ ያሉ ምልክቶችን በዝርዝር መፃፍ፣ የችግርህን መጠን ለመረዳት ያስችልሃልና የመጀመሪያው ተግባርህ አድርገው፡፡
በመቀጠል የኋልዮሽ በመጓዝ የልጅነት ዕድሜህን መፈተሽ አስፈላጊ ተግባር ነው፡፡ በተለይ ደግሞ አንተን በማሳደግ ሚና ከነበራቸው ሰዎች ውስጥ የስሜት ችግር (ለምሳሌ ድብት፣ የስሜት መቀያየር ችግር ወዘተ) ያለባቸው ሰዎች መኖራቸውን ለይ፡፡ ምክንያቱ ደግሞ እንደነዚህ አይነት ችግር ያለባቸው አሳዳጊዎች፣ ልጆችን የማግለል ባህሪ ስለሚታይባቸው ያሳደጓቸው ልጆች የመገለል ስሜትን ከህፃንነት ጊዜያቸው ጀምሮ ስለሚያዳብሩ፣ በጎልማሳነት ዕድሜያቸው ለድብት የመጋለጥ እድላቸው ከፍተኛ ይሆናል፡፡

ልጅነትህን ከቃኘህ በኋላ የችግርህ መነሻ የት እንደሆነ መለየት ትችላለህ፡፡ ችግሩ ከየትም ይነሳ ከየት በመቀጠል መተግበር ያለብህ ጉዳይ፣ አሁን ያሉና ጠቃሚ ያልሆኑ አስተሳሰቦችህን መለየት ነው፡፡

ለምሳሌ ‹‹በሙሉ ትክክለኛነት መስራት ካልቻልኩ መስራቴ ዋጋ የለውም››፣ ‹‹የእኔ ዋጋማነት የሚለካው ሰዎች ስለኔ ባላቸው አመለካከት ነው››፣ ወዘተ የሚሉ አመለካከቶች ካሉህ ነቅሰህ ማውጣት፡፡ አስተሳሰቦችን ነቅሰህ ካወጣህ በኋላ ደግሞ ትክክለኛነታቸውን መፈተሹ ጠቃሚ ተግባር ነው፡፡ ይህንን ለማድረግ ደግሞ ያን አስተሳሰብ ለመያዝ ያስቻሉህ ምክንያቶችን መፈተሽ ተገቢ ነው፡፡ በምሳሌ ላስረዳህ፣ በጽሑፍህ ላይ ‹‹የማልጠቅም ነኝ ብዬ አስባለሁ›› ብለሃል፡፡ የማልጠቅም ነኝ ብለህ ለማሰብ ምክንያቶችህ ምንድን ናቸው? ምክንያቶችህስ የዚህ አይነት ድምዳሜ ላይ ለመድረስ በቂ ናቸው ወይ? በቂ ከሆኑስ (ከጽሑፍህ በመነሳት እኔ አይመስሉኝም) ጠቃሚ ሰው ለመሆን የተሻለው መንገድ የቱ ነው? መጨነቅ ወይስ የእርምት እርምጃ መውሰዱ? ወዘተ አይነት ጥያቄዎችን በማንሳት እያንዳንዱን አስተሳሰብህን መሞገት የአስተሳሰብ ለውጥ እንድታመጣ ዐብይ ሚና ይጫወታል፡፡

ከዚህ ጋር ተያያዥ የሆነው ሌላው ተግባር ራስህ ለራስህ ኃላፊነት መውሰድ ነው፡፡ በምንም መስፈርት ለአንተ ከአንተ የቀረበ ሰው የለም፡፡ አንተ የቤተሰብ ኃላፊ ነህ፡፡ ይህንን ኃላፊነትህን የምትወጣው በህይወት ስትኖርና ጤነኛ ስትሆን ነው፡፡ ስለሆነም ሌሎች ኃላፊነቶችህን ለመወጣት ከመሞከርህ በፊት በመጀመሪያ፣ አንተን ለራስህ በህይወትና በጤና መኖር የሚያስችሉህ ተግባር መወጣት ይጠበቅብሃል፡፡ ይህንን ለማድረግ ደግሞ በመጀመሪያ ለእኔ ተግባራት ኃላፊነት መውሰድ ያለብኝ እኔ ነኝ የሚል አስተሳሰብን መያዙ ወሳኝ ነው፡፡ ይህንን አስተሳሰብ ካዳበርክ በኋላ ደግሞ ቀጥሎ የምጠቁምህን ተግባራት በመተግበር ሁኔታህን ወደ መለወጥ ትጓዛለህ፡፡

የመፍትሄ አቅጣጫ 2.
ባህሪን መለወጥ

የተለያዩ የስነ ልቦና ጥናቶች እንዳሳዩት፣ የስሜት ለውጥ የባህሪ ለውጥን ተከትሎ የሚመጣ ጉዳይ ነው፡፡ በምሳሌ ለማስረዳት፣ የናፈቀህን ሰው እቅፍ አድርገህ ስትስመው (ባህሪ) ውስጥህን ደስ ይልሃል (ስሜት)፡፡ በመሰረቱ የአንተ ችግር የስሜት ችግሮች ውስጥ የሚካተት ነው፡፡ ችግርህን ለመቅረፍ ደግሞ ባህሪህን በመለወጥ ስሜትህን መለወጥ ወሳኝ ነው፡፡ ባህሪህን ለመለወጥ ስትነሳ ደግሞ ከቀላል ባህሪያት መጀመሩ ተገቢ ነው፡፡ ከባድ ባህሪያትን ለመለወጥ ጀምረህ ባይሳካልህ ችግርህን እንደማያባብሰው ልብ ይሏል፡፡

በመሆኑም የመጀመሪያው ተግባርህ ማተኮር ያለበት ራስህን በመንከባከብ ላይ ነው፡፡ በቀን ውስጥ (ጠዋት ቢሆን ይመረጣል) ራስህን ለመንከባከብ የሚያስችልህ የሆነ ጊዜ መድብ፡፡ ይህን ስታደርግ ከዚህ ሰዓት እስከዚህ ሰዓት ብለህ መገደብ ይጠበቅብሃል፡፡ በዚህ በገደብከው ሰዓት ውስጥ መከወን አለብኝ የምትላቸውን ራስን የመንከባከብ ተግባራት ዘርዝረህ አውጣ (ለምሳሌ ሰውነቴን መታጠብ፣ ልብሴን መቀየር፣ ካልሲዬን ማጠብ፣ ጥሩ ምግብ መብላት፣ የአካል እንቅስቃሴ ማድረግ፣ የታዘዘልኝን መድሃኒት መውሰድ፣ መጽሐፍ/ጋዜጣ መጽሔት ማንበብ፣ ወዘተ…)፡፡

በአጠቃላይ ለአንተ አስፈላጊ የሆኑ ተግባራትን በሙሉ መዘርዘር አስፈላጊ ነው፡፡ በመቀጠል ከእነዚህ ተግባራት ውስጥ በገደብከው ሰዓት ውስጥ የቻልከውን ለመከወን ጣር፡፡ የገደብከው ሰዓት ካለቀ ትግበራን አቁምና ወደ ሌሎች ተግባራቶችህ አምራ፡፡

በቀጣዩ ቀን ደግሞ ዝርዝርህ ውስጥ ያሉ ተግባራትን በወሰንከው የሰዓት ገደብ ውስጥ ብቻ ለመከወን ሞክር፡፡ እንዲህም እያደረክ ለተወሰኑ ቀናት ሙከራህን ቀጥል፡፡ በዚህ ወቅትም በየቀኑ የወከንካቸውን ተግባራት ቁጥር በመመዝገብ፣ ከቀን ቀን ቁጥራቸውን ለመጨመር ጥረት አድርግ፡፡ በስተመጨረሻው በገደብከው ሰዓት የምትከውናቸው ተግባራት ቁጥር እየጨመረ ሲሄድና የድብት ሁኔታህም በመጠኑ የቀነሰ መስሎ ሲሰማህ ወደ ቀጣይ ተግባራት ታመራለህ፡፡
ቀጣይ ተግባራህ የጊዜ አጠቃቀምህን በተወሰነ መልኩ ማስተካከል ነው፡፡ በአንተ ላይ ከታዩ የድብት ምልክቶች አንዱ የበዛ እንቅልፍ መተኛት ነው፡፡ በመሆኑም በየቀኑ የተኛኸውን ሰዓት በማስላት በአንድ ሳምንት ውስጥ በአማካኝ በቀን ምን ያህል ሰዓት እንደምትተኛ አስላና አግኝ፡፡ በመቀጠልም በስሌት ካገኘኸው ሰዓት ላይ አንድ ሰዓት ያነሰ ለመተኛት ዝግጅት አድርግ፡፡ በአጠቃላይም በሳምንት ሰባት ተጨማሪ ሰዓታት ታገኛለህ፡፡ ድብት የያዛቸው ሰዎች መተኛት የሚያበዙት፣ በነቁበት ሰዓት የሚሰሩት ነገር ማጣታቸው አንደኛው ምክንያት ነው፡፡

ስለሆነም ትርፍ ያገኘኸውን ሰዓት ለሁለት ተግባራት ለማዋል ጣር፡፡ አንደኛው ስታወራቸው የሚያዳምጡህ ሰዎችን ፈልግና (ለምሳሌ ልጆችህን) ከእነሱ ጋር ለማሳለፍ ሞክር፡፡ ሁለተኛው ደግሞ ከዚህ ቀድሞ ስትከውናቸው የሚያዝናኑህ አሁን ግን ብዙም የማይመስጡህ ተግባራት ላይ ለማድረግ ሞክር (እደበረህም ቢሆን)፡፡ እነዚህን ተግባራት መከወንህ የእንቅልፍ መጠንህን ይቀንሳል፣ የእጠቅማለሁ ስሜትህን ያዳብራል፣ ብሎም የተለያዩትን ስሜታዊ ችግሮችህን ይቀንሳል፡፡

የመፍትሄ አቅጣጫ 3
ራስህን መፈተሽ

ቀደም ሲል የጠቆምኩህን አቅጣጫዎች በሚገባ ከውኛቸዋለሁ ብለህ ስታምን ወደዚህኛው አቅጣጫ ፊትህን አዙር፡፡ ጊዜ ውሰድና የእኔ ጠንካራ ጎኖችና ልጠቀምባቸው የምችላቸው ዕድሎች ምን ምን ናቸው ብለህ በዝርዝር ፃፋቸው፡፡ ይህን በፃፍክበት ወረቀት ጀርባ ደግሞ ደካማ ጎኖችና ላሻሽላቸው የሚገቡት የትኞቹ ናቸው ብለህ ዘርዝር፡፡ በተመሳሳይም ነገራትን እንዳልከውን የሚገድቡኝ ሁኔታዎች ምንድን ናቸው ብለህ ፃፋቸው፡፡

በመቀጠል ከደካማ ጎኖችህ አንዱን ብቻ በማንሳት፣ እንዴት ማሻሻል እንደምትችል አቅጣጫ ንድፍና ትኩረትህን በእሱ ላይ በማድረግ ለማሻሻል የምትችለውን ሁሉ አድርግ፡፡ ያን ደካማ ጎን በተወሰነ መልኩ አሻሽያለሁ ብለህ ስታምን ወደ ሌላኛው ደካማ ጎንህ ማሻሻል አዝግም፡፡ በተመሳሳይ በእያንዳንዱ ገዳቢ ነገር ትክክል ገዳቢው ሁኔታ ሲመጣ፣ እንዴትስ ልታልፈው እንደምትችል/እንዳለብህ አቅጣጫ አስቀምጥ፡፡ እነዚህን ተግባራት መከወን ህይወትህ ወደተለመደው/የቀድሞው ሁኔታህ እንዲመለስ ያደርጋል፡፡

በስተመጨረሻ አንድ ሶስት የሚሆኑ ማሳሰቢያዎች አሉኝ፡፡ አንደኛውና ዋነኛው እነዚህን አቅጣጫዎች ስትተገብር በቅደም ተከተል መሆን አለበት፡፡ አለበለዚያ ጉዳቱ ያመዝናል፡፡ ለምሳሌ ዘለህ ደካ ጎንህን ለመለወጥ ብትሞክር ችግርህን የመቅረፍ ሁኔታህ አናሳ ይሆናል፡፡ ወይም ደግሞ ችግርህን ታባብሰዋለህ፡፡ ሁለተኛው ማሳሰቢያዬ የተለያዩ ዕፆችን ወይም ያልታዘዙ መድሃኒቶች ወይም መጠጦችን የምትጠቅም ከሆነ ከቻልክ ለሁሌ ካልቻልክ ደግሞ ከችግርህ እስክትወጣ አቁማቸው፡፡
ወደ ሶስተኛውማሳሰቢያዬ ስዘልቅ፣ ቀደም ብዬ እንደገለፅኩት የድብት ችግር ያለባቸው ወላጆች በቀጣይ ወደ ድብት ያጋልጣቸዋል፡፡ ስለሆነም በተቻለህ አቅም ልጆችን ከማግለልና ከመቆጣት ራስህን ቆጥብ ባይ ነኝ፡፡ እነዚህን ካልኩ በኋላ ደግሞ መልካም የለውጥ ጊዜ እየተመኘሁልህ የዛሬ ምክሬን በዚሁ አጠናቅቃለሁ፡፡

The post Health: ድብት እያንገላታኝ ነው፤ ምን ትመክሩኛላችሁ? – ጥያቄና 3ቱ መፍትሄዎች appeared first on Zehabesha Amharic.

Health: ካንሰርን ለመፈወስ ብቸኛው መንገድ * ስምንቱ ልዩ የካንሰር መከላከያ ስልት

$
0
0

– ካንሰርን ለመፈወስ ብቸኛው መንገድ
– ልዩ ትኩረት የሚያሻቸው አምስት ካንሰሮች
– ስምንቱ ልዩ የካንሰር መከላከያ ስልት
– ሊወሰዱ የሚችሉ ሁለት የካንሰር ክትባቶች

ስለምን ሁሉም ሰው ካንሰር ይፈራል? ለዚህ ደግሞ ምክንያቱ አንዴ በካንሰር በሽታው ሁሉንም የሰውነት አካል ሊነሳ የሚችል ሲሆን በተለይ ከ30 ዓመት ጀምሮ ያሉትን ሁሉንም የህብረተሰብ ክፍሎች ማጠቃት የሚችል ነው፡፡ ምንም እንኳን ለሁሉም አይነት ካንሰር ፈውስ ባይኖርም አንዳንድ ካንሰሮችን ግን ቀድሞ ሲጀምሩ በምርመራ ማወቅ ከቻሉ ባሉበት ማምከን ስለሚቻል ከካንሰሩ ስጋት ነፃ መሆን ይችላሉ፡፡ በመሆኑም ሁለተኛው የካንሰር መፈወሻ የሚባለው ሴቶችንም ሆነ ወንዶችንም በብዛት ለሚያጠቁ ካንሰሮች ዓመታዊ ምርመራ በማድረግ የተከሰተን ካንሰር ወዲያው በእንጭጩ ማስቀረት በመሆኑ ዓመታዊ የካንሰር ምርመራና ህክምና አንድ ቁልፍ ስልት ነው፡፡
cancer
በመሆኑም በተለይ ለሚከተሉት አምስት ካንሰሮች ልዩ ትኩረት ይስጡ፡፡ በተለይ በሴቶች የጡትና የማህፀን፣ ለወንዶች ደግሞ የፕሮስቴት፣ ለሁለቱም ፆታዎች ደግሞ የሳንባና የትልቁ አንጀት ካንሰር ምርመራ ተግባራዊ ማድረግ ያስፈልጋል፡፡

በካንሰር ለመፈወስ ስምንቱ የካንሰር በመከላከያዎች የመጀመሪያው ዘዴ ደግሞ ለካንሰር አጋላጭ የሆኑ የአኗኗርና የአመጋገብ ዘይቤዎችን ማስቀረትና ካንሰር ተከላካይ አመጋገባችንና አኗኗራችን ተግባራዊ ማድረግ ነው፡፡ በሽታው ከመከሰቱ በፊት ማስቀረት ከቻሉ ከካንሰር ስጋት ነፃ መሆን ቻሉ ማለት ነው፡፡ ከእነዚህም ውስጥ የሚከተሉትን ስምንት ቀላል ነገሮችን ይተግብሩ፤ ከሲጋራ መራቅ፣ ጤናማ ክብደትን ማሳካት፣ የአካል ብቃት እንቅስቃሴ ማዘውተር፣ አትክልትና ፍራፍሬ ማዘውተር፣ የአልኮል አወሳሰድን መቀነስ፣ ቆዳን ከአደገኛ ፀሐይ ብርሃን መከላከል፣ በስጋ ዘመድ ውስጥ በካንሰር የተያዘ ካለ ለዚያ ካንሰር ልዩ ጥንቃቄና ምርመራ ማድረግ ናቸው፡፡

3ቱ የካንሰር መከላከያ ክትባቶች

ሌላው ሶስተኛው የካንሰር መፈወሻ ስልት አሁንም ክስተቱን በክትባት ማቆም ነው፡፡ እስካሁን በክትባት ደረጃ ውጤታማ ክትባት የተገኘላቸው የጉበት ካንሰር አማጭ ለሆነው ሄፓታይተስ ቢ ቫይረስና ለማህፅ በር ካንሰር (ለሴቶች) አስተማማኝ መከላከያ በመሆን በጥቅም ላይ እየዋለ ያለው ጋርዳሲል የሚባለው ክትባት ነው፡፡ እነዚህ ክትባቶች አዘውትረው ለሚከሰቱ የጉበትና የማህፀን ካንሰር አስተማማኝ መከላከያ በመሆናቸው አገልግሎት ላይ እየዋሉ ሲሆን ለጡት ካንሰር መከላከያ ክትባት የሚደረገው ምርመራ ግን ተስፋ ሰጪ ቢሆንም ገና ወደ ትግበራ አልገባም፡፡

በታዳጊ ሀገራት ውስጥ እየጨመረ ስለመሆኑ

ካንሰር እና የህብረተሰብ ጤና ባለሙያዎቹ ደጋግመው በተለይ በደሃ ሀገራት እየተበራከተ ያለውን የካንሰር በሽታን ለመከላከል መንግሥትና ኤጀንሲዎቹ ትኩረት አድርገው እንዲሰሩ መጎትጎታቸውን ቀጥለዋል፡፡

በ1970 ዝቅተኛ እና መካከለኛ ገቢ ያላቸው ሀገራት በዓለማችን በካንሰር የተያዙ 15% የሚሆኑ ዜጎችን አቅፈው መያዛቸው ነበር የሚታወቀው፡፡ 2008 ላይ ታዲያ 4 እጥፍ ማለት በሚቻል መልኩ ዕድገት በማሳየት 56% የካንሰር ታማሚዎችን እነዚህ ሀገራት መሸፈናቸውን ነው በጤና ላይ የሚሰሩ መፅሔቶች የለቀቁት መረጃ የሚያሳየው፡፡ ሩቅ በማይባል ጊዜ ውስጥ ማለት እስከ 2030 ድረስ አሃዙ 70% ሊደርስ እንደሚችል በመግለፅ የጉዳዩን አሳሳቢነት ለማሳየት ይሞክራሉ፡፡ ይሄም የዓለማችንን 2/3 የካንሰሩ ኬዝ የድሃና በማደግ ላይ ያሉ ሀገራት እንደሚሸፍኑ የሚያረጋግጥ ነው፡፡

በዓለማችን ቀዳሚው ገዳይ በሽታ እንደሆነ የሚነገርለት ካንሰር እንደ ኢትዮጵያ ባሉ ደሃ ሀገራት ባለው ሰፊ ማህበረሰብ ዘንድ እስከ ቅርብ ጊዜ ድረስ ሰፊ ግንዛቤ ያልተያዘበት ከሌሎች ተያያዥ በሽታዎች ጋር ተዳብሎ ሲጠራ የቆየ እንዲሁም በሂደት የሰው የአኗኗር ስልት መቀየርን ምክንያት በማድረግ የተስፋፋ ስለመሆኑ ነው የጤና ባለሙያዎች የሚያስረዱት፡፡
በሀርቫርድ ዩኒቨርሲቲ የማህበረሰብ ጤና መምህርና የጤና ፖሊሲ ጥናቶችን ከሚያረቁ ባለሙያዎች መካከል የሆኑት ዶ/ር ጁሊዮ ይሬንኮ እንደሚሉት ካንሰር ባደጉት እና እያደጉ ባሉ ሀገራት ጭምር ሰዎች በወጣትነት የዕድሜ ዘመናቸው ውስጥ ሳሉ ለህልፈት የሚዳርጋቸው ቀዳሚ በሽታ መሆኑን እና በደሃ ሀገራት ደግሞ የጉዳዩን አሳሳቢነት ያህል ትኩረት ያልተሰጠው ስለመሆኑ ነው የሚያስረዱት፡፡ ይህን የወቅቱ አሳሳቢ ጉዳይ መግታት ይቻለን ዘንድ ከፍተኛውን የካንሰር ተጠቂ ሰዎች ቁጥር እየሸፈኑ ያሉት ዝቅተኛ እና መካከለኛ ገቢ ያላቸው ሀገራትን በተለያዩ መንገዶች ዓለም አቀፍ ድጋፎች ሊደረግላቸው እንደሚገባ ነው የሚያሳስቡት፡፡ አሁን ላይ ዓለም አቀፍ የካንሰር ቁጥጥር እና ክብካቤ ግብረ ኃይል የዓለም የጤና ድርጅት በሲጋራ ስርጭት ቁጥጥር በአመጋገብ እንዲሁም በጤናማ አኗኗር ዙሪያ የሚሰራውን ስራ በአጋርነት እየሰራ መሆኑ ነው የሚታወቀው፡፡
የጤና ፖሊሲ ረቂቅ ባለቤቶቹ ዝቅተኛና መሀከለኛ ገቢ ያላቸው ሀገራት በማይድን ካንሰር የሚሰቃዩ ዜጎቻቸውን ህመም የሚያስታግሱ መድሃኒቶች በቀላሉ የሚያገኙበት ሂደት እንደሚመቻችም ነው ሃሳብ ያቀረቡት፡፡ ለበሽታው ስርጭት ከፍተኛ መሆን በተለይ በአፍሪካ የተካሚዎችን አቅም ያላገናዘበ የመድሃኒት ዋጋ መቅረቡ ነው፡፡
የጡት ካንሰርን ለማከም የሚውለው ታሞክሴፊን የተሰኘው መድሃኒት ውድነትን በማንሳት፡፡ ከዚህ ባለፈ በማላዊ፣ ጋና እና ካሜሩን ባሉ ሀገራት የ50% የፈዋሽነት ደረጃ ያለውን የመጀመሪያ ደረጃ የኬሞቴራፒ መድሃኒት ለማግኘት ሰዎች እስከ 50 የአሜሪካን ዶላር ድረስ እንዲያወጡ ማስፈለጉንም እነዚህ ባለሙያዎቹ በማሳያነት ያቀርባሉ፡፡
ዝቅተኛና መካከለኛ ገቢ ባላቸው አንድ ኮለምቢያና ሜክሲኮ ባሉ ሀገራት ደግሞ በአንፃሩ በቂ በሚባል ደረጃ ለዜጎች የካንሰር ህክምና ፕሮግራች በብሔራዊ የጤና ኢንሹራንስ ፖሊሲ አማካኝነት ሲሸፈን በተለይ ድሆችን ተደራሽ ያደረገ እንቅስቃሴ በመሆኑ ለአብነት የሚነሳ ተግባር ነው፡፡
በዘርፉ የሚታየው የባለሙያዎች እንዲሁም የህክምና ቁሳቁሶች እጥረት እንደ ኢትዮጵያ ባሉ አዳጊ ሀገራት በሽታውን ለማከም ፈተና የሆኑ ጉዳዮች ናቸውም ተብሏል፡፡

The post Health: ካንሰርን ለመፈወስ ብቸኛው መንገድ * ስምንቱ ልዩ የካንሰር መከላከያ ስልት appeared first on Zehabesha Amharic.

Health: ፒያኖ መጫወት ለአዕምሮ ጤና የሚያስገኘው ጠቀሜታ

$
0
0

Piano and Brain Health
ይህ ጽሁፍ በዘ-ሐበሻ ጋዜጣ ላይ ታትሞ ወጥቷል::

ብዙ ሰዎች የዕለት ተዕለት ህይወታቸውን አስደሳች ለማድረግ ይረዳል ብለው የሚያስቡትን ነገር ለማከናወን ይጥራሉ፡፡ ከእነዚህ ሰዎች ውስጥ ብዙዎች አመጋገባቸውን ጤናማ ለማድረግ እና የአካል ብቃት እንቅስቃሴ የሚሞክሩ ናቸው፡፡ ከቅርብ ጊዜ ወዲህ ከዚህም እዚያም የአትክልት ቤቶች ከስጋ ቤቶች እኩል እየተስፋፋ መምጣት፣ የአካል ማጎልመሻ ጂምናዚየሞች ቁጥር መብዛት የዚህ ማሳያ ነው፡፡ ምንም እንኳን እነዚህ ድርጊቶች ጤና በመጠበቅ እና ደስታን በማጎናፀፍ ረገድ ቁልፍ ሚና የሚጫወቱ ቢሆንም ሌሎች በተለይ ደግሞ ለአዕምሮ ጤና የሚጠቅሙ ልምምዶችም ይኖራሉ፡፡አንዱ ሙዚቃ መጫወት ነው፡፡ ከሙዚቃም መሳሪያዎች መካከል ፒያኖ መጫወት፡፡

ሙዚቃ መጫወት የአንድን ሰው ሁለንተናዊ ጤንነትን ለማሻሻል ይረዳል፡፡ ለአዕምሮ ጤና መጠበቅም ጉልህ አስተዋፅኦ ያበረክታል፡፡

ከሙዚቃ መሳሪያዎች መካከል ደግሞ አንዱ እና ዋነኛ የሆነውን ፒያኖ መማር እና መጫወት መቻል ማንም ሰው ሊገምተው ከሚችለው በላይ በርካታ ጥቅም ለአዕምሮ ጤና ይሰጣል፡፡

አንድ ሰው ፒያኖ መማር ከሚጀምርበት ወቅት አንስቶ ዕድሜ ልኩን አብረው የሚዘልቁ ጥቅሞችን ያገኛል፡፡ ልጅም ይሁን አዋቂ ያለምንም ልዩነት ፒያኖ የሚጫወት ከሆነ ዘርፈ ብዙ ጤና ነክ ጥቅሞችን ይቋደሳል፡፡ ከዚህ በታች የተዘረዘሩት ነጥቦች ፒያኖ በመጫወት የሚገኙ ልዩ ልዩ ጥቅሞች ናቸው፡-

– ፒያኖ መጫወት የአንድን ሰው የማሰብ እና የማሰላሰል አቅም ይጨምራል፡፡ ጥናቶች እንደሚጠቁሙት ሙዚቃ እየፈጠሩ መጫወት ሌሎች ድርጊቶች የማይወጡትን በከፍተኛ ሁኔታ አንጎልን የማነቃቃት ስራ ይሰራል፡፡ አንድ ሰው ፒያኖ በሚጫወትበት ጊዜ አንጎሉ ውስጥ የሚገኙ ኒውሮኖች ትስስር ይጨምራል፡፡

– ፒያኖ መጫወት የዓይንን እና የእጅን ቅንጅት ያጠናክራል፡፡ አንድ ሰው የፒያኖ መጫወቻ መምሪያን እያነበበ በሚጫወትበት ወቅት ዓይኑ እና እጁ ከመቼውም ጊዜ በበለጠ መልኩ ወዳጅነታቸው ጥብቅ ይሆናል፡፡

– ፒያኖ መጫወት የቀላል ጡንቻዎቻችንን ቅልጥፍናም ይጨምራል፡፡ የእጅ መጠን የፒያኖ ጨዋታ ክህሎትን አይወስንም፡፡ ወሳኙ ነገር ጣቶቻችን የፒያኖ ጨዋታ የሚጠይቀውን ቅልጥፍና እንዲለማመዱ ማድረግ ነው፡፡

– ፒያኖ መማር ቀላል የማይባል ቁርጠኝነትን የሚጠይቅ ሥራ ነው፡፡ የታወቀ ፒያኒስት ለመሆን በትጋት ለረጅም ጊዜ ልምምድ ማድረግ የግድ ነው፡፡በየቀኑ የፒያኖ ትምህርት ያለ ማቋረጥ መውሰድም አንድ ሰው በህይወቱ ይበለጥ ስርዓት ያለው ሰው እንዲሆን ያግዘዋል፡፡ እንዲህ አይነት ስርዓት ደግሞ በሌሎች የህይወታችን ክፍሎች ውስጥም ጠቀሜታ ይኖዋል፡፡

– ፒያኖ መጫወት ውጥረትን እና ጭንቀትንም ይቀንሳል፡፡ አንድ ሰው ፒያኖ ለመጫወት ሌላው ቀርቶ ለጥቂት ደቂቃዎች እንኳን ቁጭ በሚልበት ወቅት ሃሳቡ አንድ ስፍራ ላይ ይሰበሰባል፡፡ ይሄ በበኩሉ የደም ግፊትን መጠን ዝቅ በማድረግ ወይም በማስተካከል የሚሰማን ውጥረት እና ጭንቀት እንዲቀንስ ያደርጋል፡፡

– ፒያኖ መጫወት የአዕምሮን ጤናማ ይጠብቃ፡፡ ብዙ ፒያኒስቶች እንደ ድብርት ባሉ የአዕምሮ ጤና ጠንቆች እምብዛም አይቸገሩም፡፡ ማህበራዊ ችግሮች ብቸኝነት የመሳሰሉ ፒያኖ በመጫወት ሊቃለሉም ይችላሉ፡፡

ፒያኖ በማወት የሚመጣ አንድም ችግር የለም፡፡ ይልቁንም የፒያኖ ትምህርት እና ስልጠና መውሰድ እና መጫወት በጥቅሉ ለአካልም ሆነ ለአዕምሮ የሚያስገኘው ጥቅም የትየለሌ ነው፡፡ አንድ ሰው ፒያኖ በሚጫወትበት ወቅት ህይወቱን በስርዓት መምራትን ከመማር ጀምሮ የፈጠራ ችሎታውን እስከማሻሻል ድረስ ቀላል የማይባሉ ለውጦችን ያመጣል፡፡ ከዚህ በተጨማሪም ፒያኖ መማርም ሆነ መጫወት ምንም አይት የዕድሜም ሆነ አዕምሮ ገደብ የለውም፡፡ ወሳኙ ነገር ፍላጎቱ ብቻ ነው፡፡

The post Health: ፒያኖ መጫወት ለአዕምሮ ጤና የሚያስገኘው ጠቀሜታ appeared first on Zehabesha Amharic.


Health: አናናስን ከውሃ ጋር ቀላቅሎ የመጠጣት የጤና በረከቶች

$
0
0

Pineapple with water
በሙለታ መንገሻ

ሁሌም ጠዋት ጠዋት የምንጠጣው ውሃ ውስጥ አናናስ ጨምሮ መጠጣት ለጤናችን ጠቃሚ መሆኑን ይነገርለታል።

ሰውነታችን ጤነኛ እንዲሆን እና በሽታን የመከላከል አቅሙ እንዲጨምር ከፈለግንም ሁሌም ጠዋት ጠዋት የምንጠጣው ውሃ ውስጥ አናናስ ጨምረን መጠጣት ይመከራል።

አናናስ ለጤና ጠቃሚ የሆኑ እንደ ቪታሚን C እና ብሮሜሊን ንጥረነገሮችን በውስጡ በመያዙ ነው ለጤና ተመራጭ የሚያደርገው።

ስለዚህም ቢያንስ ለአንድ ዓመት ያክል ሳናቋርጥ የምንጠጣው ውሃ ውስጥ አናናስ ጨምረን ከጠጣን በጤናችን ላይ ከፍተኛ ለውጥ ልናይ እንደምንችልም ተነግሯል።

ስለዚህም ይህን ውህድ በምንጠጣበት የምናገኛቸው የጤና ጠቀሜታዎችም፦

ለካንሰር እንዳንጋለጥ ይረዳናል

የምግብ መፈጨት ስርዓታችንን ያግዛል

ጤናማ እና ጠንካራ ጥርስ እንዲኖረን ይረዳናል

ክብደትን ለመቀነስ ይረዳል

የሰውነት መቆጣትን ይከላከላሉ

ጉበታችንን እና አንጀታችንን ለጉዳት ከሚዳርጉ ጥገኛ ህዋሳት ይከላከላል ።

ምንጭ፦ naturalmedicinehouse.com

The post Health: አናናስን ከውሃ ጋር ቀላቅሎ የመጠጣት የጤና በረከቶች appeared first on Zehabesha Amharic.

Health: የሴትን ልጅ ልብ ለመማረክ እና ቀጣይነት ያለው ግንኙነት ለመመስረት የሚረዱ 6 ነጥቦች

$
0
0

ethiopian health ove
ሴቶች በፍቅር ውስጥ አጥብቀው የሚፈልጉት ምንድነው?

በጥንዶች መካከል ለሚኖር የተሳካ የፍቅር ግንኙነት የፍላጎት መጣጣም እጅግ አስፈላጊ መሆኑ አጠያያቂ አይደለም፡፡ በዚህ ረገድ የሰው ልጆች በአጠቃላይ፣ ተመሳሳይ የሚመስል መሰረታዊ ፍላጎቶች ቢኖራቸውም ወንዶችና ሴቶች በየግል ከፍተኛ ቦታ የሚሰጧቸው የተለያዩ የስሜት ፍላጎቶች ይኖሯቸዋል፡፡
በግንኙነት መስክ ውስጥ ከምንጠቀምባቸው ክህሎቶች ሁሉ የመጀመሪያውና ጠቃሚ ነገር፣ የተጓዳኛችንን ጥልቅ ፍላጎት እና ተግባራት አስቀድሞ መረዳት ሲሆን፣ ይህ ማስተዋል አብሮን ያለውን ሰው ጠንቅቀን እንድንረዳ ስለሚያግዘን ችግሮች ከመሰከታቸው በፊት እንድንታደጋቸው ብሎም ከተፈጠሩ በኋላ በንቃት እና በጥበብ መለስ እንድንል ይረዳናል፡፡ አንዳንድ ጊዜ የሰዎችን መሻት ሳይነግሩን የማወቅ ክህሎትን መማርና መለማመድ፣ አታካችና አድካሚ ቢመስልም ውጤቱ ግን እጅግ አመርቂ እንደሚሆን አያጠያይቅም፡፡ አብዛኛውን ጊዜ በጥንዶች መካከል ተቀራርቦ ፍላጎቶችን ማውራት፣ ስሜትን መጋራትና ምክንያትን መግለጽ፣ የተሻለ ቅርርቦሽን በመፍጠር በትዳር ላይ መተማመንን ስለሚጨምር መልካም የሚባል ውጤትን ሊያስገኝልን ይችላል፡፡

ብዙውን ጊዜ ሰዎች ጥምረት የሚገቡት በዘርፉ በቂ የሚባል ዝግጅት ሳይኖራቸው እንደሆነ በተደጋጋሚ በዚህ አምድ ላይ የተነሳ ጉዳይ ነው፡፡ ይህም ትዳርን ውስብስብ እና አታካች እያደረገ መጥቷል፡፡ ከስልጣኔ ጋር ተያይዞ የመጣውም የሰው ልጅ ፍላጎት መጨመርና በትንሽ ነገር ያለመርካት አባዜ፣ በትዳር ውስጥ ተስፋ መቁረጥ የራሱን የሆነ ሚና ይጫወታል፡፡
በአንድ ወቅት ኖራ ሃይደን የተባለች የማህበራዊ ህይወት ተመራማሪ በመጽሐፏ እንዳለችው፣ አብዛኛው ወንዶች ስለ ሴቶች ያላቸው አተያይ እጅግ አስደንጋጭ ነበር፡፡ በወንዶች ዓይን ሴቶች ማለት፣ በዚህች ምድር ላይ ካሉ ነገሮች ሁሉ በላቀ ደረጃ እጅግ ውስብስብና፣ ፍላጎታቸው የማይታወቅ በቀላሉ የማይረኩ ፍጡሮች እንደሆኑ ይገልፃሉ፡፡
በዚሁ ጥናት ላይ የሴትን ልጅ ፍላጎት ከመረዳትና፣ ሴትን ልጅ ደስተኛ ከማድረግ ይልቅ (ኑዩክለር ፊዚክስ ማጥናት እንደሚቀል ገልጧል)
ይህ በእውነቱ ከእውነታው ጋር እጅግ የሚጣረስና ለሴቶች እጅግ አስደንጋጭ ጉዳይ ነው፡፡ ይህ እሳቤ የሚመነጨው ሁላችንም በራሳችን ግለኛ ዓለም ውስጥ ተከልለን የራሳችንን ተፈጥሮና ፍላጎት ብቻ ስለምናዳምጥና የሌሎችን ማንነት ለማወቅና ተጣጥሞ ለመኖር ምንም አይነት ጥረት ስለማናደርግ ይመስለኛል፡፡
በተለያየ ጊዜ በዘርፉ የተሰማሩ ባለሙያዎች፣ ስለወንዶችና ሴቶች ረቂቅ ባህሪያትና ፍላጎት ለማወቅ በርካታ ጥናቶችን አካሂደዋል፡፡ ከእነዚህ ጥናቶች የተውጣጣውን መደምደሚያ መሰረት በማድረግ ከ90 በመቶ በላይ የሚሆኑት ሴቶች የሚስማሙበትንና፣ ሴቶች ከትዳር አጋራቸው ወይም ፍቅረኛቸው አጥብቀው የሚሹትን 6 ነጥቦችን ከሀገራችን ነባራዊ ሁኔታ ጋር በማጣጣም ላካፍላችሁ ወደድኩ፡፡

የሴትን ልጅ ልብ ለመማረክ እና ቀጣይነት ያለው ግንኙነት ለመመስረት የሚረዱ 6 ነጥቦች
(Caring) እንክብካቤ
1. በጥናቱ ውስጥ ከተካተቱ አብዛኛዎቹ ሴቶች በፍቅር ለሚንከባከብ ወንድ በቀላሉ እንደሚሸነፉ ገልፀዋል፡፡ ይህም የሚሆነው ሴቶች በተፈጥሮ ካላቸው የእንስትነት ባህሪ የተነሳ ከወንዶች ስሜት እና ፍቅርን ብቻ ሳይሀን፣ ከለላን፣ አለኝታነትን እና እክብካቤን አጥብቀው እንደሚሹ ተናግረዋል፡፡ ይሄም ምኞት እና ደህንነት እንዲሰማው ስለሚያደርግ ህይወትን ለቀቅ አድርገው በመመልከት የበለጠ ደስተኛ ያደርጋቸዋል፡፡

2. ትኩረት
ይሄንን ፍላጎት በሁለት ከፍለን ልናየው እንችላለን፡፡
2.1 መደመጥ
Joeu Barton የተባለ የስርዓተ ፆታ ተመራማሪ በጥናቱ ላይ እንዳሰፈረው፣ ሴቶች በቀን ውስጥ በአማካኝ 20,000 ቃላቶችን ሲጠቀሙ፣ በተቃራኒው ወንዶች ደግሞ 7,000 ቃላትን በመጠቀም ሀሳባቸውን ያስረዳሉ፡፡ ይህም በግልፅ እንደሚያስረዳን አንደኛ ሴቶች ለቋንቋ እና ለንግግር ፈጣን የሆነ አዕምሮ እንዳላቸው ሲሆን፣ ሌላው እና ትኩረት ሊሰጠው የሚገባው ጉዳይ፣ ሴቶች በንግግር ራሳቸውን በመግለፅ የበለጠ ነፃነት እንደሚሰማቸው ሲሆን ችግር በገጠማቸውና በጨነቃቸውም ጊዜ በማውራት ብቻ ያለ ምንም ተጨማሪ ምክርና መፍትሄ የተሻለ እፎይታና እረፍት እንደሚሰማቸው ሲሆን፣ በዚህም ጊዜ ንግግራቸውን በትኩረት ለሚያዳምጣቸው ወንድ የተለየ ፍቅርና አክብሮት ይኖራቸዋል፡፡
2.2 አንዲሰት ሴት አብሯት ካለ ወንድ ከፍቅርና እንክብካቤ ባሻገር አትኩሮ ትሻለች
በርካታ የህይወት ተሞክሮዎች እንደሚያመለክቱት፣ ሰዎች በተሰበሰቡበት ግብዣ ላይ አንድ ወንድ ፍቅረኛውን ወይም የትዳር አጋሩን ከሰዎች ጋር በሚኖረው ጨዋታ እጇን በማሻሸት ወይም በመሳም፣ አብሮነቱን ቢያረጋግጥላት በቀላሉ ልቧን በፍቅር በማቅለጥ የጥሩ ስሜት ባለቤት እንድትሆን እንደሚረዳ ይታመናል፡፡ አብዛኛውን ጊዜ ወንዶች በግንኙነት ውስጥ የሚመለከቱት፣ ትልቁን ምስል ብቻ በመሆኑ አብሮነት በራሱ በቂ ነው ብለው ሊያስቡ ይችላሉ፡፡ ሴቶች ደግሞ ባላቸው የተለያየ አፈጣጠር ዝርዝር ነገሮች ላይ ትኩረት ስለሚያደርጉ እያንዳንዱን እንቅስቃሴና ፍሰት ይከታተላሉ፡፡ በመሆኑም ወንዶች ፍቅረኛቸው ወይም የትዳር አጋራቸውን ከመነፈጠሯም ረስተው ለረጅም ሰዓት ከሶስተኛ ወገን ጋር ጨዋታ ውስጥ ሊገቡ ይችላሉ፡፡ ይህ በሴቶች አዕምሮ ውስጥ የመተውና አትኩሮት የማጣት ስሜትን ሊያጭር ስለሚችል ወንዶች ትኩረት ሊያደርጉበት ይገባል፡፡ ይሄንን በጣም ቀላል ግን ከፍተኛ ተፅዕኖ ሊፈጥር የሚችል እውነታ በመረዳት፣ በሄዳችሁበት ሁሉ ለሴቶቻችሁ አብሮነት ትኩረትና ዕውቅናን በመስጠት፣ ስሜታቸውን ከመጉዳት ብትታደጉ በምላሹ ፍቅር እና አድናቆትን ትቀበላላችሁ፡፡
እዚህ ጋ ልብ ልንለው የሚገባው እውነታ፣ ይህ ዓለም መስጠትንና መቀበልን መሰረት ያደረገ ነው፡፡ የሰውን ስሜት ጎድቶ መልካም የስሜት ምላሽ መጠበቅ የዋህነት ስለሆነ፣ የምንፈልገውን ለማግኘት የሚፈለገውን መስጠት ግድ ይለናል፡፡

3. (Security) ጥበቃ
ከጥንት ጀምሮ ሲወርድ ሲዋረድ የመጣው፣ የወንድ ልጅ ከለላ እና መጋ መሆን፣ አሁንም ድረስ በብዙዎች ዘንድ ተቀባይነት ያለው እውነታ ነው፡፡ በዚህ በሰለጠነው እና የሴቶች እኩልነት በተረጋገጠበት 21ኛው ክፍለ ዘመን እንኳን፣ ሴት ልጅ በግሏ ገቢ በማስገኘት ሀብት ማካበት ብትጀምርም፣ የወንድ ልጅ ግብአት አቅራቢ እና ጠባቂ መሆን የሴትን ልጅ ስሜት ለማረጋጋት በጣም አስፈላጊ ነው፡፡ ከዚህም በዘለለ ወንድ ልጅ ለሴት ከተለያየ አደጋ ጠባቂ ሆኖ መገኘቱ፣ እምነቷን የበለጠ ስለሚያጠነክረው ፍቅሯ እየጎለበተ ይሄዳል፡፡

4. Blind Loyalty (ፍፁም የሆነ ተአማኒነት)
በአብዛኛው አንዲት ሴት የፍቅር ግንኙነት ውስጥ ስትሆን ወይም በወንድ ስትፈቀር ራሷን የተለየች ፍጡር አድርጋ እንድታይ ትሆናለች፡፡ ይህም ምን አልባት ከሴቶች ተፈጥሮ በተጨማሪ ወንዶች በፍቅር መብረቅ በተመቱ ጊዜ ያፈቀሯትን ሴት የግላቸው ለማድረግ የሚጠቀሙበት ገደብ የለሽ ሙገሳና ማሞካሸት፣ ሴቶች ለራሳቸው ያላቸውን አመለካከት በማዛባት፣ ውጫዊ መስህብን እንደ ብቸኛ የማንነታቸው መለኪያ አድርገው እንዲወስዱት ሳያስገድዳቸው አልቀረም፡፡
በመሆኑም በግንኙነት ውስጥ አንዲት ሴት የራሷን የመስህብ ደረጃ ጠንቅቃ ብታውቅም ባፈቀራት ወንድ እይታ ስትፈረጅ ‹‹ሁሉን ያስናቀች ቆንጆና ፀባየ ሰናይ መሆኗን እንዲነገራት ትፈልጋለች›› በማንኛውም አጋጣሚ የእሷ ወንድ የሌላዋን ቆንጆ አለባበስ ወይም አቋም ቢያደንቅ እሷን የወሰደባት ያህል ስለሚሰማት መጠንቀቅ ያስፈልጋል፡፡ በመሆኑም የሰውን ቆንጆ በመቃረም፣ የትዳር አጋራችንን ስሜት ከምንጎዳ፣ ያገባናትን ሴት በትዳር አብረን እንድንኖር ውሳኔ ላይ ያደረሰንን መልካም ሰብዕና፣ ውበት፣ ወይም ተግባር በማስታወስ ከልብ የመነጨ አድናቆታችንን እና ሙገሳችንን መቸርን ብንለማመድ፣ ለትዳራችን ዕድሜ ማራዘሚያነት እንደሚጠቅም ጥናቶች እና ተሞክሮዎች ያመለክታሉ፡፡

5. Understanding (መረዳት)
በርካታ ሴቶች ከተጓዳኛቸው አጥብቀው የሚፈልጉት ተጨማሪው ነገር፣ የትዳር አጋራቸው የእነሱን ሚና እና በቤት ውስጥ ያላቸውን አስተዋፅ እንዲረዳ እና ዕውቅና እንዲሰጥ ነው፡፡ አንዳንድ ወንዶች ሴት ልጅ በቤት ውስጥ የምታከናውናቸውን ረቂቅና እጅግ ወሳኝ ተግባራት ባለማወቅ ዕውቅናን ሲነፍጉ ይስተዋላሉ፡፡ የሴት ልጅ ተፈጥሮ ማለትም በሴትነት የምታልፋቸውን ከባባድ ደረጃዎች፣ እርግዝና፣ ወሊድ፣ ማጥባት እና ልጅን መንከባከብ በምድራችን ካለ ነገር ሁሉ እጅግ ውድ፣ ፈታኝ እና ዋጋ ሊተመንለት የማይችል መሆኑን በመረዳት፣ ሴት ሆነው ያንን መክፈል እንኳን ባይችሉ፣ ክብደቱን በመረዳት እና ርህራሄ በማሳየት ሊያዝኑላቸው፣ ሊንከባከቧቸው እና ሊደግፏቸው ይገባል፡፡ ይሄም በሴት ልጅ ልቦና ውስጥ እስከ መጨረሻው ለመቀመጥ ጥርጊያ መንገድ ይሆናል፡፡

6. Sex (ወሲብ)
በተጣማሪዎች መካከል ፍቅር ሰምሮ ኑሮ እንዲደረጅ፣ በሐሳብ እና ፍላጎት መጣጣም ተቀዳሚው መሆኑ የማያጠያይቅ ሀቅ ነው፡፡ መከባበሩ፣ መፈቃቀሩና የሐሳብ መጣጣሙ እንደተጠበቀ ሆኖ በወሲብ አለመጣጣም ባለትዳሮች ከትዳራቸው ውጪ ሌላ ሰው መጎብኘታቸው የተለመደ ተግባር እየሆነ መጥቷል፡፡
ብዙውን ጊዜ ተጣማሪዎች፣ የሐሳብ አለመጣጣምን አቻችለውና ተቻችለው ኑሮን ሲገፉ ይስተዋላል፡፡ በአሁኑ ዘመን እየተስተዋለ የመጣው እውነታ እንደሚያመለክተን ግን በወሲብ አለመጣጣምን ማስታመም ስለሚያቅታቸው ወይም ከሌላ ጋ ሲማግጡ ወይም ከነጭራሹ ትዳርን ሲያፈርሱ ይታያሉ፡፡
በአብዛኛው በርካታ ወሲብ ነክ ፅሑፎችና ጥናቶች አንድን ወንድ እንዴት ለወሲብ ማነሳሳት እንዳለብን እና እንዴት እርካታ ላይ እንዲደርስ መርዳት እንዳለብን የሚገልፁ ናቸው፡፡ ይህም የሚያሳየው የሴት ልጅ ስሜት ይሄ ነው የሚባል አትኩሮት ከማህበረሰቡ ጭምር እንዳልተቸገረው ነው፡፡
Nora Hayden (How to satisfy a women every time) በተሰኘው መጽሐፏ ላይ እንደገለፀችው 80% የሚሆኑት ሴቶች፣ እውነተኛ እርካታ ላይ እንደሚደርሱ ሆኖም የትዳር አጋራቸውን ለማስደሰት ሲሉ ብቻ እርካታ ላይ እንደደረሱ እንደሚያስመስሉ ይናገራሉ፡፡ ይህም የሚሆነው ወንዶች በወሲብ ጊዜ የሴትን ልጅ ፍላጎት እና የስሜት ምስጢር መረዳት ስለሚያቅታቸው እነሱ በሚረኩበት መንገድ ይረካሉ ብለው በማሰብ ዘልማዳዊ የሆነውን ግንኙነት ያደርጋሉ፡፡ ሆኖም ፈጣሪ ወሲብን በትዳር መካከል እንድትደሰትበትና ትውልድን እንድናስቀጥልበት የሰጠን ታላቅ ፀጋ በመሆኑ፣ የሴትም ልጅ ስሜት መጠበቅ እና በባሏ መደሰት እንዳለባት በመረዳት በግልፅ በመወያየትም ሆነ በዘርፉ የተፃፉ ጽሑፎችን በማንበብ፣ ደስታውን የጋራ የማድረግ የወንዶች ተቀዳሚ ኃላፊነት ነው፡፡
በመጨረሻ ማንሳት የምፈልገው ነጥብ፣ ብዙዎች በትዳር ላይ በግንኙነት ዙሪያ በመርህ ደረጃ የሚነሱ ጠቃሚ ምክሮችን ማንበብ ፋይዳ ቢ መሆኑን ሲናገሩ ይታያል፡፡ ለዚህም እንደ ምክንያትነት የሚያነሱት መከራከሪያ የፀሐፊዎቹ ወይም አነበብን የሚሉ ሰዎችን ግለ ህይወት በናሙናነት በማንሳት፣ በትዳር ህይወታቸው ስኬታማ አለመሆናቸውን ነው፡፡ እዚህ ጋ መረዳት ያለብን ቁም ነገር፣ ችግሩ ያለው ከዕውቀቱ ወይም ከንባቡ ሳይሆን ያወቅነውን እና የሰማነውን በልቦናችን አኑረን መተግበር ስለሚሳነን መሆኑን ነው፡፡ በመሆኑም ተፈጥሮ የለገሰችን ሰብዕና፣ በህይወት ተሞክሮ እና ዕውቀት በማዳበር፣ ያካበትነውን ዕውቀት በመተግበር እና ለውጥ በማምጣት ትዳራችን በግምት ሳይሆን፣ በጥበብ የምንመራትን ልቦና ይስጠን፡፡

ሴት ልጅ ምን መስማት አትሻም!
ሴቶች ስለ ሌላ ሴት ወይም ስለ ቀድሞ ጓደኛህ ስታደንቅ መስማት አትፈልግም፡፡ ከሌላ ሴት ጋር እንድታወዳድራትም እንዲሁ፡፡ ስለ ሰውነት ቅርጽና ውበቷ አድናቆት እንጂ ነቀፌታ ቅር ያሰኛታል፡፡ በድንገት ተሳስተህ የሌላ ሴት ስም ማንሳትም አይኖርብህም፡፡ በሌላ መንገድ ያስጠረጥርሃልና፡፡ ከአሁን ቀደም በነበረህ የሴት ልጅ ትውውቅ ውስጥ አላግባ ያደረካቸውን ነገሮች ማውራትህ ከባድ ግምት ውስጥ ይጥልሃልና በተቻለ መጠን ከኋላ ፈቅር ታሪክህ ውስጥ ጥሩ ጥሩውን እንጂ የሚያስተችህን ለመርሳት ወይም ላለማንሳት ጥረት አድርግ፡፡ በሌላዋ ላይ ይህን ያደረገ በእኔም ላይ ማድረጉ አይቀርም የሚል እምነት ይኖራታልና፡፡ ሴቶች ስለ አንተ ማወቅ የሚፈልጉትን ሲጠይቁህ እውነቱን መናገሩን ብቻ ነው የሚያዋጣው፡፡ ብዙ ጊዜ ሴቶች ለማወቅ በሚመስል መልኩ ይጠይቃሉ እንጂ የሚጠይቁትን ነገር ቀድሞውኑ ያውቁታልና አትዋሽ!
በተቻለ መጠን ከአሁን ቀደም ከነበረህ የፍቅር ትስስር እንዴት እንደተለያየህ ምክንያትህን አሳማኝነት ያለውና ከአንተ በኩል ከፍተኛ ጥረት ማድረግህ ላይ ያነጣጠረ ይሁን እንጂ ኃላፊነትህን ስላለመወጣትህ የሚያንፀባርቁ ምክንያቶችን ወይም ደግሞ ቀድሞውኑ ለመለያየት የማያበቁ ምክንያቶችህን ሴቶች መስማት አይፈልጉም!! ቢሰሙም ትዝብት ውስጥ ይጥሉሃልና ጠንቀቅ በል!!

Health: የውሃ ምስጢሮች

$
0
0

‹‹እኔ እኮ አይጠማኝም››፤ ‹‹አያስመለክተኝም››፤ እንዲያም ሲል ‹‹ሰው እንዴት ባዶ ውሃ ይጠጣል?›› የሚሉ ሰዎች አጋጥመዋችሁ ይሆናል፡፡ እውነታው ወዲህ ነው፡፡ ፈሳሽ እየወሰዱ ያለ ምግብ ለሳምንታት መቆየት ይቻላል፡፡ የውሃ እጥረት ግን ከማናቸውም ንጥረ ምግቦች እጥረት በተለየ መልኩ በፍጥነት ህይወትን ያሳጣል፡፡ ያለ ውሃ ለ10 ቀናትም እንኳ በህይወት መቆየት አይቻልም፡፡ የሰውነታችን እያንዳንዱ እንቅስቃሴ የውሃን ተሳትፎ በቀጥታም ሆነ በተዘዋዋሪ የሚጠይቅ ነው፡፡ ይሁንና ስለ ውሃ አስፈላጊነት ብዙው ሰው በውል አልተገነዘበውም፡፡ እንዲያውም የንጥረ ምግብ ምድብነቱንም የሚጠራጠሩ ሰዎች አሉ፡፡ ውሃ የሚጠጡት ሊጠማቸው አለበለዚያ ምግብ ሲያንቃቸው ብቻ ነው፡፡
water for health
ከወንዶች የሰውነት ክብደት 60 በመቶ ከሴቶች ደግሞ 50 በመቶ ያህል ውሃ መሆኑ ይታወቃል፡፡ የሰውነት ውሃ መጠን ከወንዶች ይልቅ በሴቶች ላይ አንሶ መገኘቱ ስለ ስብ ክምችታቸው ነው፡፡ ውሃ እና ስብ አያጣጣሙም፡፡ በሰውነታችን ውስጥ ከ38-45 ሊትር የሚገመት ውሃ ይገኛል፡፡ አንጎል 78፣ ደም 83፣ ጡንቻ 75፣ አጥንት 22 በመቶ ውሃ ናቸው፡፡ ዕድሜ እየገፋ ሲሄድ የሰውነት የውሃ መጠን እየቀነሰ፣ የሰውነት ስብ ክምችት እየጨመረ ይሄዳል፡፡ ፆታ፣ ዕድሜ፣ ውፍረት የመሳሰሉት ጉዳዮች የሰውነት ውሃ መጠንን እንደሚወስኑ ልብ ይሏል፡፡

ሰማንያ በመቶ የሚሆነውን ፈሳሽ ፍላጎታችንን የምናሟላው ከምንጠጣው፣ ቀሪውን ሃያ ከመቶ የምናሟላው ደግሞ ከምንበላው ነው፡፡ አትክልትና ፍራፍሬዎች በርካታ ውሃን አዝለዋል፡፡ እንካችሁ ውሃ ከነሙሉ ትጥቁ ይሉናል፡፡ ለምሳሌ ሀብሃብ፣ ቲማቲም፣ ቆስጣ እና ሰላጣ 90 በመቶ ይዘታቸው ውሃ ሲሆን በአቅራቢያችን የሚገኘው ዋጋውም እየተወደደ ያስቸገረን የቫይታሚን ሲ አለኝታችን ‹‹ብርቱካን›› ደግሞ 87 በመቶ ውሃ ነው፤ በፕሮቲን ምንጭነታቸው የምናውቃቸው ሥጋ፣ ዓሣ፣ ዶሮ ሳይቀሩ ከግማሽ እስከ ሁለት ሦስተኛ ይዞታቸው ውሃ ነው፡፡

የውሃ ጠቀሜታ በሰውነታችን ውስጥ ለመጠጥ ፍጆታችን ውሃን እንምርጥ ዘንድ ያሉት ሳይንሳዊ መረጃዎች ግድ ይሉናል፡፡ ከዚህም ሌላ በርካሽ ዋጋ በየቦታው የምናገኘው ጥም ቆራች መጠጥም ውሃ ነው፡፡

ውሃ ማጓጓዣ ነው
ንጥረ ምግቦች እና ወሳኝ ማዕድናት በመላው የሰውነት ክፍሎች የሚዘዋወሩት፤ ቆሻሻ ተረፈ ምርቶች ከሰውነት የሚወገዱት በውሃ ተሸካሚነት ነው፡፡ ያለ ውሃ የሰውነት ዋና ዋና የስራ ሂደቶች ክፉኛ ይስተጓጎላሉ፡፡

ውሃ ማለስለሻ፣ ማለዘቢያም ነው
በውስጣዊ የሰውነት አካላት ዙሪያ የውሃ መኖር እንደ መከላከያ ግድግዳ በመሆን ከውጫዊ ድንገተኛ ጫና ይጠብቃቸዋል፡፡ የዚህ ጥበቃ ተጠቃሚ ከሆኑ የሰውነታችን ብልቶች ውስጥ አንጎል፣ አይን፣ እና ህብለ ሰረሰር ይገኙበታል፡፡
ውሃ በምራቅ እና በሌሎች የሰውነታችን ፈሳሾች ውስጥ በብዛት ስለሚገኝ የተፈጨ ምግብ በጉሮሮ ወርዶ ወደ አንጀት እንዲደርስ የምግብ ቧንቧን የማለስለስ ሚና ይጫወታል፡፡ በተለያዩ ምክንያቶች ምራቅ የቀነሰባቸው ሰዎች ምግብ ለመዋጥ የሚቸገሩት በዚህ ምክንያት ነው፡፡ በተለያዩ የሰውነት ክፍሎች ያሉ የአጥንት መገጣጠሚያዎች እንደልብ እንዲተጣጠፉ አሁንም ውሃ የራሱ ድርሻ አለው፡፡

ውሃ በሰውነት ውስጥ በሚካሄዱ ኬሚካላዊ ዑደቶች ንቁ ተሳታፊ ነው
የፕሮቲን እና የካርቦሃይድሬት ዑደት ልመት ውጤቶች የሰውነት ህዋሳት በሚጠቀሙበት መልኩ እንዲቀየሩ ውሃ የሚጫወተው ሚና በቀላሉ የሚታይ አይደለም፡፡ እንደ ተረፈ ምርት ሆኖ ከሰው ሰራሽ ብክለት ነጻ የሆነ አንድ ብርጭቆ ያህል ውሃ በየቀኑ በዚህ መልኩ ይፈጠራል፡፡ እኛ እንገነዘበው ይሀናል እንጂ ህዋሳት ለዕለት ፍጆታቸው ፈጥኖ የሚያደርስላቸው በመሆኑ ውሃን በጉጉት ይጠብቁታል፡፡

ውሃ የሰውነት ሙቀትን ይቆጣጠራል
በጤና እንሰንብት ዘንድ የሰውነታችን ሙቀት ተገቢ በሆነ ልክ ተወስኖ መቆየት አለበት፡፡ የውጪው አየር ሙቀት ሲለዋወጥ የሰውነታችን ሙቀት አብሮ አይለዋወጥም፡፡ ይህም የሆነበት ዋናው ምክንያት ሰውነታችን አብዛኛውን እጅ ውሃ በመሆኑ፣ ውሃ ደግሞ በተፈጥሮው የሙቀት ለውጥ የሚያስተናግደው ዝግ ብሎና ተረጋግቶ ስለሆነ ሙቀትን አፍኖ ይይዛል፡፡
በሞቃታማ የአየር ንብረት ወቅት ከሰውነታችን ውስጥ የውሃ ትነት ይከሰትና አላስፈላጊ ሙቀት አብሮ እንዲወገድ ያደርጋል፡፡ በዚህም ላይ ላብ አለ፡፡ ሳናስተውለውም ቢሆን ቀንና ሌሊት ያልበናል፤ በተለይ በሞቃት የአየር ንብረት እና በከፍተኛ አካላዊ እንቅስቃሴ ወቅት የላብ መጠን ይጨምራል፡፡
ከዚህም በተጨማሪ ውሃ ቆዳችንን በማለስለስ ውበትን እንደሚያጎናፅፍ ይታወቃል፡፡ የስነ ቆዳ ውበት ባለሙያዎች መፍቀሬ ውበት ወይዛዝርት ደንበኞቻቸውን አበክረው የሚመክሩት ዘወትር ውሃ በበቂ ሁኔታ እንዲጠጡ ነው፡፡

የሰውነት ፈሳሽ ሚዛን መጠበቅ
ሰውነታችን በየቀኑ የውሃ ብክነት ከውሃ አወሳሰድ ጋር እንዲመጣጠን የሚያስችል ውስጣዊ አሰራር አለው፡፡ የፈሳሽ እጥረት ሲያጋጥም ኩላሊቶች መልኩ ቡናማ የሆነ መጠኑ ያነሰ ፈሳሽ በሽንት መልክ እንዲወገድ በማድረግ የሰውነት ፈሳሽን ይቆጥባሉ፡፡ በተጨማሪም አንጎላችን ዝም አይልም፤ የውሃ ጥምን በማወጅ ፈጥነን ውሃ እንድንጠጣ ያሳስባል፡፡ የፈሳሽ ሚዛኑ ወደ መበራከት ካመዘነ ኩላሊቶች የጠራ ሽንትን አብዝተው ያመርታሉ፡፡ አንጎል በበኩሉ ውሃ ጥምን ያነሳል፡፡

ውሃ ከሰውነታችን የሚወገድባቸው መንገዶች
በሚታይና በማይታይ መልኩ ውሃ ከሰውነታችን ይወጣል፡፡ ቆዳ፣ ኩላሊቶችና ሳንባዎች በውሃ መወገድ ሂደት ዋና ዋና ተሳታፊዎች ናቸው ማለት ይቻላል፡፡ ዝርዝሩን ቀጥለን እንመልከት፡፡

በቆዳ በኩል
የሰውነት ሙቀትን ለመቆጣጠር ከሚያስችሉ ዘዴዎች አንዱና ዋነኛው በቆዳ በኩል ውሃን ማውጣት ነው፡፡ ይህም እንደ አካባቢው የሙቀት መጠን እና እንደ አካላዊ እንቅስቃሴ ሁኔታ ይለያያል፡፡ በአማካይ በላብ በኩል የሚወገደው የውሃ መጠን 100 ሚሊ ሊትር ነው፡፡
በሞቃት አካባቢዎች የሚኖሩ ሰዎች ውስጣዊ የሰውነታቸውን ሙቀት ለመቆጣጠር ሲባል በቀን እስከ 2 እና 3 ሊትር የሚደርስ ላብ ሊያልባቸው ይችላል፡፡ ይህን የሚተካ ውሃ ካልተወሰደ የፈሳሽ ሚዛኑ እንደሚዛባ መገመት አያዳግትም፡፡ አድካሚ የሆነ አካላዊ እንቅስቃሴ ከታከለበት ደግሞ ሁኔታውን ይበልጥ ያባብሰዋል፡፡
የሰውነት እንቅስቃሴ ከወትሮው በጨመረ ቁጥር የሰውነት ሙቀትም ይጨምራል፡፡ ታዲያ ተማሪው ሙቀት መወገድ የሚችለው በላብ አማካኝነት ነው፡፡ ከፍተኛ ደረጃ ስፖርታዊ እንቅስቃሴዎች የላብን መጠን 1 ሊትር በሰዓት ሲያደርሱት ይህ ድርጊት በሞቃታማ አካባቢ ከሆነ ግን በላብ የሚወገደው የውሃ መጠን 2 እና 3 ሊትር በሰዓት ሊደርስ ይችላል፡፡
በበሽታ ምክንያት የሚመጣ የሰውነት ትኩሳት ሌላው ላብ አምጪ ጉዳይ ነው፡፡ የሰውነት ሙቀት ከተለመደው በ1 ዲግሪ ሴልሽየስ ከጨመረ የላብ መጠን በግማሽ ሊትር ይጨምራል፡፡ ትኩሳት ላለባቸው ሰዎች ተጨማሪ ፈሳሽ እንዲወስዱ ሐኪሞች የሚመክሩት ለዚህ ነው፡፡
ላብ የሚታይ ነገር ነው፡፡ የማይታ ነገር ግን በቆዳ በኩል የሚባክን ውሃ አለ፡፡ ስለ እርሱ ጥቂት ላውጋችሁ፡፡ ውሃ ከቆዳችን ያለማቋረጥ በትነት መልኩ የሚወጣ ሲሆን መጠኑም በቀን 350 ሚሊ እንደሚደርስ ይገመታል፡፡ የቆዳ ላይ ትነት እና ላብ አይገናኙም፡፡ አንድ አስገራሚ ማስረጃ ላቅርብ፡፡ ያለ ላብ አመንጪ ዕጢዎች የሚፈጠሩ ሰዎች አሉ፡፡ (እንዲህ ያለ ሰው ገጥሞኛል) ታዲያ ሰዎቹ በምንም አይነት ሁኔታ ውስጥ ሆነው ባያልባቸውም ሊከሰት ይችል የነበረውን ከፍተኛ የሰውነት ሙቀት መጠን በቆዳ ትነት አማካኝነት ይከላከሉታል፡፡ ይህ ባይሆን ኖሮ ምን ይውጣቸው ነበር?

በኩላሊቶች በኩል
ከሰውነት በኩላሊቶች አጣሪነት የሚወገደው የሽንት መጠን በሆርሞን ቁጥጥር ስር ያለ እና የሰውነት የፈሳሽ ሚዛንን ለመጠበቅ ሲባል ወቅታዊ ማስተካከያ የሚደረግበት ነው፡፡ ብዙ ፈሳሽ እየወሰደ የሚገኝ ግለሰብ ብዛት ያለው ጠራ ያለ ሽንት ሲኖረው በአንፃሩ የፈሳሽ አወሳሰዱ የቀነሰ ሰው የሚኖረው ሽንት መልኩ የደፈረሰ፣ መጠኑ ያነሰ ነው፡፡ ይህ ቀላል የሽንት ቀለምን የመለየት ዘዴ የሰውነት የፈሳሽ ሚዛንን ለመገምገምና የእርምት እርምጃ ለመውሰድ ያስችላል፡፡ የሰውነት ፈሳሽ እጥረት ሲያጋጥም ኩላሊቶች ውሃን በመቆጠብ ስራ ይጠመዱና በሽንት መልክ እንዲወገድ የሚፈቅዱት የፈሳሽ መጠን ከግማሽ ሊትር አይበልጥም፡፡ በተቃራኒው ሰውነት በውሃ ብዛት ሲንበሸበሽ በቀን እስከ 20 ሊትር ውሃ በሽንት መልክ ማስወገድ እንደሚችሉ ያስመሰክራሉ፡፡ በአዘቦቱ ቀን የሽንት መጠን ከ1.3 እስከ 1.4 ሊትር ነው፡፡ ፕሮቲንና ጨው የበዛባቸው ምግቦች እንዲሁም የአልኮል መጠጦች ሽንትን በማብዛት ይታወቃሉ፡፡

በሳንባዎች በኩል
በአፍ እና በአፍንጫ ተስቦ የሚገባው አየር ከመተንፈሻ አካላት ስስ ልባስ በሚለገሰው እርጥበት ምክንያት ለውስጥ ሰውነት ወደ ሚስማማ እርጥበታማ አየር ይቀየራል፡፡ ውሃ ለእርጥበት መፈጠር ዋናው ግብዓት መሆኑን መገንዘብ ያስፈልጋል፡፡ ያለማቋረጥ በትንፋሽ የሚጠፋው የውሃ መጠን ከ350-400 ሚሊ በቀን ይገመታል፡፡
በትንፋሽ በኩል የሚወጣው የውሃ መጠን ያካባቢው አየር እርጥበት ሲቀንስ፣ ኤር ኮንዲሽነር ባለበት ክፍል፣ በተራራማ ቦታዎች፣ አይሮፕላን ውሰጥ እና በስፖርታዊ ልምምድ ወቅት ይጨምራል፡፡ እንደ አሁኑ ባለ ቀዝቃዛ ወራት በትንፋሽ የሚጠፋው ውሃ ይበራከታል፡፡ ለዚህም ነው በቅዝቃዜ ወቅት የአፍና አፍንጫ ውስጥ ድርቀትን የሚያስተናግዱት፡፡

በዓይነ ምድር በኩል
በቀን ከመቶ ሚሊ ሊትር ያልበለጠ ውሃ ከአይነ ምድር ጋር አብሮ ይወገዳል፡፡ ሰዎች እንደ ኮሌራ በመሰሉ አጣዳፊ የተቅማጥ በሽታዎች ሲያዙ ይህ አሃዝ በማይታመን መልኩ ወደ 1 ሊትር በሰዓት ሊያሻቅብ ሲችል አፋጣኝ የፈሳሽ መተካት ህክምና ካልተደረገ በአጭር ጊዜ ውስጥ ህይወትን ሊያሳጣ የሚችል ነው፡፡

ለውሃ እጥረት የተጋለጡ
ህፃናት

የማላብ ስርዓታችን ገና ስላልዳበረ ከፍ ያለ ሙቀት መቋቋም ይሳናቸዋል፡፡ ይህም ብቻ አይደለም፣ ለውሃ ጥም ስሜት እንደ አዋቂዎች ያለ አፀፋዊ ምላሽ አይሰጡም፡፡ አጣዳፊ ትውከትና ተቀማጥ ካጋጠማቸው ደግሞ ለሰውነት መሟሸሽ ፈጥነው ይጋለጣሉ፡፡
አረጋውያን

እንደ ወጣቶቹ ሰውነታቸው ውሃ ሲያጥረው ስለማይጠማቸው ለሰውነት መሟሸሽ ተጋላጭ ናቸው፡፡ ተደራራቢ በሽታዎች ለእነዚህም የሚወሰዱ መድሃኒቶች ካሉ የውሃ እጥረት ችግሩ ይባባሳል፡፡
ህፃናትና አረጋውያን በቂ ውሃ እንዲያገኙ ማስቻል ከቤተሰብ አባላት እንዲሁም ከህብረተሰቡ የሚጠበቅ በጎ ተግባር ነው፡፡

አትሌቶች

ከሌሎቹ ንጥረ ምግቦች ይልቅ የውሃ አወሳሰዳቸው ትኩረትን የሚሻ ጉዳይ ሆኖ እናገኘዋለን፡፡ ውሃ ፈርጣማ ጡንቻዎቻቸውን ለማብረድ፣ የሰውነታቸውን ሙቀት ለመቆጣጠር ቁልፍ ሚና ይጫወታል፡፡ የውሃ እጥረት ስፖርታዊ ክንውናቸውን ክፉኛ የማወክ ዝንባሌ ሲኖረው መዘዞችም አሉት፡፡ ለምሳሌ አንድ አትሌት ከሰውነት ክብደቱ ከ2-3 በመቶ ያለው በላብ ምክንያት ቢቀንስ በአግባቡ ተልዕኮውን ማከናወን ይሳነዋል፡፡ የፈሳሽ ጉድለቱ ከ7-10 በመቶ ከደረሰ ግን ሰውነት ከአቅም በላይ በሀነ ግለት ይመታና ከዚህች ዓለም ስንብት ይሆናል፡፡ የማራቶን ሯጮች በአንድ ሰዓት ውስጥ እስከ 2.8 ሊትር የሚገመት ላብ ያልባቸዋል፡፡ በስፖርታዊ ልምምድም ሆነ በውድድር ወቅት ከሚከሰት ከፍተኛ የፈሳሽ እጥረት ለመከላል ከድርጊቱ አስቀድሞ (2 ብርጭቆ ውሃ ከ2 ሰዓት በፊት፣ 1 ብርጭቆ ውሃ ከ15 ደቂቃ በፊት)፣ በክንዋኔው ወቅት (በየ20 ደቂቃው ከግማሽ እስከ 1 ሙሉ ብርጭቆ) እና ከውድድሩም በኋላ በቂ ውሃ መጠጣት ያስፈልጋል፡፡
ከዚህም ሌላ ከቤት ውጭ ባልተከለለ ቦታ ቀኑን ሙሉ የሚሰሩ ሰዎች ለፈሳሽ እጥረት የተጋለጡ ናቸው፡፡ ሞቃትና ከፍተኛ የአየር እርጥበት ከልፋት ጋር ሲደመሩ የፈሳሽ እጥረቱን ያባብሱታል፡፡ እንዲህ ያሉ ሠራተኞች ከጎናቸው ውሃ ሳይለያቸው በመካከል ውሃ ቢጎነጩ መልካም ነው፡፡

ለምን ይጠማናል?
ሰውነታችን የውሃ ፈሳሽ እጥረት እንዳጋጠመው አብዛኛውን ጊዜ የሚያስታውቀው ጥምንን በማወጅ ነው፡፡ አንድ ሰው የጥም ስሜትም ሆነ የህመም ስሜት ሳይሰማው የሽንቱ መጠን ሳይቀንስ መልኩም ሳይደርስ የጠራ ከሆነ ግለሰቡ የፈሳሽ ሚዛኑ የተጠበቀ ነው ብሎ መገመት ይቻላል፡፡ ታዲያ ሁሌም እንዲህ አይሆንም፡፡ ልማድ አድርገነው ውሃ እስኪጠማን ድረስ ሳንጠጣ የምንቆይ ከሆነ አንዳንዴ ሰውነታችን የፈሳሽ እጥረት እንኳ ገጥሞት አንጎላችን ጥምን ሳያውጅ የሚቆይበት ጊዜ አለና በየጊዜው በቂ ውሃ መውሰድ የዕለት ተዕለት ተግባራችን ሊሆን ይገባል፡፡ በተለይ ህፃናት፣ አረጋውያን፣ ስፖርተኞች፣ እና አትሌቶች የሰውነት ውሃ ፍላጎታቸው በጥም ላይ ሊመሰረት አይገባውም፡፡

በየቀኑ ምን ያህል ውሃ መጠጣት አለብን?

እያንዳንዱ ሰው በጤና ለመሰንበት በቂ ውሃ በየቀኑ መጠጣት ይኖርበታል፡፡ ይህ መጠን እንደሰውየው ዕድሜ፣ ፆታ፣ ጤና እና አካላዊ እንቅስቃሴ ሁኔታ ይለያያል፡፡ የአየር ሁኔታውም ተፅዕኖ አለው፡፡ በደምሳሳው ሲታይ ከባድ የሰውነት እንቅስቃሴ የማያደርግ፣ በምቹ የአየር ንብረት ያለ አንድ ጤናማ አዋቂ ሰው በቀን አነሰ ከተባለ 2 ሊትር (8 ብርጭቆ) አለበለዚያ 3.5 ሊትር (13 ብርጭቆ) ውሃ መጠጣት ሲያስፈልገው ካላቸው የስብ ክምችት የተነሳ የሴቶች የውሃ ፍላጎት ከወንዶቹ በአማካይ በ1 ሊትር ያንሳል፡፡
ውድ አንባብያን በቂ ውሃ የመጠጣት ልምድን ለማዳበር ከዛሬ ጀምሩ፤ በቀስ በቀስ የውሃ አወሳሰድን አጎልብቱ! ለዚህ እኔ ምስክር ነኝ፣ ከ2 ብርጭቆ ተነስቼ አሁን ላይ 13 ብርጭቆ ደርሻለሁ፤ ቤተሰቦቼም እንደኔ የመጠጥ ውሃ ይደፍራሉ፡፡

አብዛኛው የህብረተሰብ ክፍል ከመደበኛው በታች የሆነ የፈሳሽ አወሳሰድ ስላለው በመለስተኛ የሰውነት መሟሸሽ ደረጃ ውስጥ እንደሚገኝ ይገመታል፡፡ ስር የሰደደ የሰውነት ፈሳሽ እጥረት ለኩላሊት ጠጠር እና ሌሎች መዘዞቹ እንደሚዳርግ የሞያ ተሞክሮዬ አስገንዝቦኛል፡፡ የህክምና መጻህፍት ከዚህ ጋር ይስማማሉ፡፡
በእነዚህና እነዚህ ምክንያቶች የተነሳ ውሃ ለህይወታችን መሰረት ነው፤ ውሃ ህይወት ነው እላለሁ!
ቸር እንሰንብት፡፡

Health: የአንድ ሰው አካል 100 ትሪሊዮን በሚያህሉ ጥቃቅን ሴሎች የተገነባ ነው –ለመሆኑ ሴል ማነው? ስራውስ?

$
0
0

Boday cells
የአንድ ሰው አካል 100 ትሪሊዮን በሚያህሉ ጥቃቅን ሴሎች የተገነባ ነው፡፡ ጠቂቶቹን ለመጥቀስ ያህል የአጥንት ሴሎች፣ የደም ሴሎችና፣ የአንጎል ሴሎች ይገኙበታል፡፡ በአካላችን ውስጥ ከ200 የሚበልጡ የተለያዩ የሴል አይነቶች ይገኛሉ፡፡

ከላይ የጠቀስናቸው ብዛት ያላቸው የሴል አይነቶች ቅርፃቸውና ስራቸው ቢለያይም እጅግ ውስብስብ በሆነ መንገድ ተቀናጅተው ይሰራሉ፡፡ በዘመናችን ልዩ የሚባሉት እንደ ኮምፒዩተር ያሉ የቴክኖሎጂ ውጤቶች፣ የኢንተርኔት መረጃ መረቦች እንኳ ከእነዚህ ሴሎች ጋር ሲነፃፀር በጣም ቀርፋፋ ነው፡፡

ሴልና ህልውና
ሴሎች ሁሉም ኒውክሊዮስ ያላቸውና የሌላቸው ተብለው በሁለት ይከፈላሉ፡፡ የሰው፣ የእንስሳትና የዕፅዋት ሴሎች ኒውከሊዮስ አላቸው፡፡ የባክቴሪያ ሴሎች ደግሞ ኒውክሊየስ የላቸውም፡፡ ኒውክሊየስ ያላቸው ሴሎች ዩካርዮቲክ ይባላሉ፡፡ ኒውክሊየስ የሌላቸው ደግሞ ፕሮካርዮቲክ በመባል ይታወቃሉ፡፡ ኒውክሊየስ የሌላቸው ሴሎች ኒውክሊየስ ካላቸው ሴሎች አንፃር ሲታዩ እምብዛም ውስብስብ ስላልሆኑ ብዙዎች የእንስሳትና የአዕፅዋት ሴሎች ከባክቴሪያ ሴሎች ተሻሽለው እንደመጡ ያምናሉ፡፡
ፐሮካርዮቲክ ሴልን ከፋብሪካ ጋር ማነፃፀር ይችላል፡፡ ይህ ሴል ከአንድ ትንሽ የጤፍ ቅንጣት በብዙ መቶዎች እጥፍ ያነሰ ቢሆንም፤ ጠንካራ የሆነውና የመተጣጠፍ ባህሪይ ያለው የሴሉ ሽፋን ባዕድ ነገር ወደ ውስጥ መግባት እንዳይቻል ይከላከላል፡፡

የሴሉ ሽፋን የሚያከናውነው ተግባር ከጡብ እና ከሲሚንቶ ከተገነባ የአንድ ፋብሪካ አጥር ጋር ይመሳሰላል፡፡ ወደ 10,000 የሚጠጉ የሴል ሽፋኖች ቢነባበሩ እንኳን የሚኖራቸው ውፍረት ከአንድ ወረቀት ውፍረት አያልፍም፡፡

የሴል ሽፋን ልክ እንደ ፋብሪካ አጥር በሴሉ ውስጥ ያሉትን ነገሮች በዙሪያው ካሉ ጎጂ ነገሮች ይጠብቃቸዋል፡፡ ይህ ሽፋን እንዲህ ያለውን የመከላከል ተግባር ቢፈፅምም ድፍን ያለ ግን አይደለም፡፡ ከዚህ ይልቅ እንደ ኦክስጅን ያሉ ጥቃቅን ሞሎኪዩሎች እንዲገቡና እንዲወጡ በማድረግ ሴሉ ‹‹እንዲተነፍስ›› ያስችለዋል፡፡ ጉዳት ሊያስከትሉ የሚችሉ ውስብስብ የሆኑ ሞሎኪውሎች እንኳን ከሴሉ ፈቃድ ውጭ እንዳይገቡ ይከላከላል፡፡ በተጨማሪም ጠቃሚ የሆኑ ሞሎኪዩሎች ከሴሉ እንዳይወጡ ያደርጋል፡፡ በአጠቃላይ ፋብሪካው ወደ ውስጥ የሚገባውንም ሆነ የሚወጣውን ምርቶች የሚቆጣጠሩ ጠበቃዎች ሊኖሩት ይችላሉ ማለት ነው፤ በተመሳሳይም የሴሉ ሽፋን እንደበርና እንደጠባቂ ሆነው የሚያገለግሉ ለየት ያሉ የፕሮቲን ሞሎኪውሎች አሉት፡፡

ፕሮቲኖች የሚመረቱበት መንገድ
የፕሪካርዮቲክ ሴል ውስጠኛ ክፍል አል ምግቦችን፣ ጨዎችንና ሌሎች ንጥረ ነገሮችን በያዘ ፈሳሽ የተሞላ ነው፡፡ ሴሉ የሚያስፈልጉትን ነገሮች ለማምረት እነዚህን ንጥረ ነገሮች ይጠቀማል፡፡ ይሁን እንጂ ስራው በዘፈቀደ የሚከናወን አይደለም፡፡ ጥሩ የስራ አመራር እንዳለው ፋብሪካ ሁሉ ሴሉ በሺዎች የሚቆጠር ኬሚካላዊ ሂደቶች በተወሰነላቸው ቅደም ተከተልና በተመደበላቸው ጊዜ እንዲከናወኑ ያደራጃቸዋል፡፡

አንድ ሴል አብዛኛውን ጊዜውን የሚያሳልፈው ፕሮቲኖችን በመስራት ነው፡፡ ይህን የሚያደርገው፣ በመጀመሪያ ሴሉ 20 የሚያህሉ የተለያዩ አሚኖ አሲዶችን ሲሰራ ይታያል፤ እነዚህ አሚኖ አሲዶች ፕሮቲን ለመስራት የሚያገለግሉ መሰረታዊ ነገሮች ናቸው፡፡ ለግንባታ የሚያስፈልጉት እነዚህ መሰረታዊ ነገሮች ወደ ራይቦዘሞች ይወሰዳሉ፤ ሪይቦዘም አሚኖ አሲዶች በተወሰነላቸው ቅደም ተከተል ተጣምረው ራሱን የቻለ አንድ ፕሮቲን እንዲያስገኙ የሚያደርግ አውቶማቲክ ማሽን ነው ሊባል ይችላል፡፡ የአንድ ፋብሪካ የስራ ሂደት ማዕከላዊ በሆነ የኮምፒዩተር ፕሮግራም እንደሚመራ ሁሉ በሴል ውስጥ የሚከናወኑት ብዙዎቹ ተግባሮችም የሚመሩት ዲኤንኤ በሚባል ‹‹የኮምፒዩተር ፕሮግራም ወይም ኮድ በሚመስል አማካኝነት ነው›› ራይቦዞም የትኞቹን ፕሮቲኖች መስራት እንዳለበትና በምን አይነት መንገድ እንደሚሰራቸው የሚገልጽ ዝርዝር መመመሪያ ከዲኤንኤ ይቀበላል፡፡
ፕሮቲን ከተሰራ በኋላ የሚያከናውነው ነገር በጣም የሚያስደንቅ ነው! እያንዳንዱ ፕሮቲን ይተጣጠፍና በአይነቱ ልዩ የሆነ ባለሶስት ገና ቅርጽ ይይዛል፡፡ ፕሮቲን የሚያከናውነውን ተግባር የሚወስነው ይህ ቅርጽ ነው፡፡

ሴሎች ከሚሰሯቸው ፕሮቲኖች አንዱ ኢንዛይም ነው፡፡ እያንዳንዱ ኢንዛይም አንድን አይነት ኬሚካላዊ ሂደት ማፋጠን እንዲችል በተለየ መንገድ ይተጣጠፋል፡፡ በመቶዎች የሚቆጠሩ ኢንዛይሞች እርስ በርሳቸው ተባብረው በመስራት የሴሉን እንቅስቃሴ ይቆጣጠራሉ፡፡
አንድ ፕሮቲን በትክክል ካልተሰራና ተገቢው ቅርፅ እንዲኖረው ተደርጎ ካልተጣጠፈ የሚፈለግበትን ተግባር በተገቢው ሁኔታ ማከናወን የማይችል ከመሆኑም በላይ ሴሉ ላይ ጉት ሊያደርስ ይችላል፡፡

በሴል ውስጥ የሚመረተው እያንዳንዱ ፕሮቲን፣ የት መሄድ እንዳለበት የሚገልፅ አድራሻ አለው፡፡ በእያንዳንዱ ደቂቃ በሺ የሚቆጠሩ ፕሮቲኖች ተሰርተው ወደሚፈለጉበት ቦታ የሚደርሱ ቢሆንም አንዳቸውም እንኳን ወደ ተሳሳተ ቦታ አይሄዱም፡፡

ኢንዛይሞችን ለመስራት ዲኤንኤ ሲያስፈልግ ዲኤንኤ ለመስራት ደግሞ ኢንዛይሞች ያስፈልጋሉ፡፡ በተጨማሪም ሌሎች ፕሮቲኖች በሴል ብቻ ሊመረቱ ይችላሉ፤ ይሁን እንጂ አንድ ሴል ሊመረት የሚችለው በፕሮቲኖች ብቻ ሊሆን ይችላል፡፡

በሰው አካል ውስጥ የሚገኙ አንዳንድ ሴሎች 10,000,000,000 በሚያህሉ የፕሮቲን ሞሎኪዩሎች የተገነቡ ሲሆን እነዚህ ሞሊኪዩሎች አይነታቸው በመቶ ሺ የሚቆጠር ሊሆን ይችላል፡፡

ሴሎች በምን ያህል ፍጥነት ይባዛሉ?

አንዳንድ ባክቴሪያዎች በ20 ደቂቃ ውስጥ ራሳቸውን መተካት ይችላሉ፡፡ እያንዳንዱ ሴል ዋናውን የኮምፒዩተር ፕሮግራም ከገለበጠ በኋላ ለሁለት ይከፈላል፡፡ የማያቋርጥ ኃይል ካገኘ አንድ ሴል ብቻ እንኳ በከፍተኛ ፍጥነት ሊበዛ ይችላል፡፡ በዚህ ፍጥነት ቢበዛ በሁለት ቀን ውስጥ ብቻ ቁጥሩ በጣም በዝቶ ክብደቱ ከምድር ክብደት 2,500 ጊዜ በላይ ሊበልጥ ይችላል፡፡ ይበልጥ ውስብስብ የሆኑ ሴሎችም በፍጥነት መበዛዘት ይችላሉ፡፡ ለምሳሌ በእናታችን ማህፀን ውስጥ በነበርንበት ጊዜ የአንጎላችን ሴሎች በከፍተኛ ፍጥነት በመባዛት በደቂቃ 250,000 ያህል ሴሎችን ይሰሩ ነበር፡፡

የዲ.ኤን.ኤ ሞሎኪዩል በተደጋጋሚ ጊዜያት እንደሚነበብና እንደሚባዛ መፅሐፍ ነው፡፡ በአንድ ሰው አማካይ ዕድሜ ውስጥ ዲ.ኤን.ኤ ፈጽሞ እንከን በማይወጣለት መንገድ ወደ 10,000,000,000,000,000 ለሚጠጋ ጊዜ ይባዛል፡፡

አንድ ግራም ዲ.ኤን.ኤ አንድ ትሪሊዮን ሲዲዎች ሊይዙ የሚችሉትን ያህል መረጃ መያዝ ይችላል፡፡

Health: በአልኮል መጠጥ የተጎዳ ሰውነትን ለመጠገን የሚረዱ ምግቦች

$
0
0

Mediterranean food ethiopia
ለበርካታ አመታት ምናልባትም የአንድ ወጣት እድሜ እና ከዛ በላይ ለሆነ ጊዜ በብዛት የአልኮል መጠጦችንና ጠጥተው ወይም ሲጋራ አጭሰው ዛሬ ከእነዛ ደባል ሱሶች ተላቀዋል ።

በወጣትነት ተጀምሮ ለብዙ አመታት የቆየን ልምድ ወይም ሱስ በተለይም ደግሞ የአልኮል ሱሰኝነትን ማቆም እጅግ ከባዱ እና አስቸጋሪው ነገር ነው ። ይህን ተቋቁመው ከዚህ ሱስ ከወጡ እንኳን ደስ ያለዎት ።

ምክንያቱም በማቆምዎ እድሜ ልክዎን የሃኪም ደጅ እንዲጠኑ ከሚያደርግዎት ነገር በመጠኑም ተላቀዋልና ። የአልኮል መጠጦች ፤ የአዕምሮ ክፍልን ፣ ጉበትን ፣ ልብን ፣ የአንጀት ክፍልንና ሌሎች የሰውነት ክፍሎች ሙሉ በሙሉ ከጥቅም ውጭ የማድረግ አቅም አላቸው ።

እንዳለመታደል ሆኖ ግን ብዙዎች ለማቆም ሞክረው የተወሰኑት ሲቀጥሉ አብዛኞቹ ግን ተመልሰው በመግባት እድሜ ልካቸውን የተበላሸ እና ምስቅልቅሉ የወጣ ህይዎት እንደሚመሩ የተለያዩ ጥናቶች ያሳያሉ ።

ከዚህ በታች ያሉት ደግሞ በከባድ ሁኔታ ለበርካታ አመታት በዚህ ሱስ ውስጥ አልፈው አሁን ከአልኮል መጠጦች የራቀ ህይዎት የሚመሩ ካሉ ትናንት ያበላሹትን ጤንነት ዛሬ እንዴት ማደስ እንደሚችሉ የሚያሳዩ ናቸው ።

ለተጎዳው ሰውነትዎ የተመረጠ አመጋገብ ስርአት ቢኖርዎት

በርካታ የአልኮል ሱሰኞች ለሰውነት አስፈላጊ በሆኑ የምግብ እጥረቶችና አልኮል በሚያመጣው ተፅዕኖ ሰውነታቸው እጅግ የተጎዳና የተጎሳቆለ ነው ።

ሰውነትዎ ካጣው የተመጣጠነ የምግብ እጥረትና በአልኮል ምክንያት ከተፈጠረበት ጉዳት እንዲያገግም ካልረዱት ደግሞ ውጤቱ የከፋ ይሆናል ።

አልኮልን አብዝቶ መጠጣት በደም ውስጥ የስኳር መብዛትን ያስከትላል ፣ የልብና የአተነፋፈስ ስርአትን ያዛባል ፣ እጅግ የተጎዳና የተጎሳቆለ ገጽታ ፣ ለስኳር በሽታ ፣ ለካንሰር ፣ ላልተፈለገ እና ጤነኛ ላልሆነ የስብ ክምችት ፣ የስርአተ ምግብ ሂደት መዛባት እና ከፍተኛ ለሆነ የመርሳት ወይም የአዕምሮ መቃወስ ያጋልጣል ።

በርካቶች ከዚህ ደባል ሱስ ሲላቀቁ እንደ መርሻ ወይም መተኪያ ብለው የሚወስዷቸው ጣፋጭ እና አንዳንድ አነቃቂ ፈሳሾችን ነው ፤ ይሁን እንጅ ይህ ልማድ ከቀደመው ሱስ ያልተናነስ አደገኛ እና የማይመከር ነው ይላሉ የአሪዞናው ዶክተር ጆን ኒውፖርት ።

ከሰላሳ አመታት በላይ በተቋረጡ ሱሶች እና ተያያዥ ጉዳዮች ላይ የሰሩት እና ምርምር ያደረጉት ዶክተሩ ፤ መሰል መተኪያ መንገዶች ወደ ቀደመው ሱስ እንዲመለሱ በማድረግ ለአደገኛ በሽታ እና ህልፈት ያጋልጣሉ ።

ከዛ ይልቅ የሜዲትራንያን የአመጋገብ ስርአትን መከተሉ አዋጭ ነው ።

የጥራጥሬ ውጤቶችን ፣ ፍራፍሬዎች ፣ አትክልትቶችና በጥሬ ሊዘጋጁ የሚችሉ ቅጠላ ቅጠሎች ፣ በፕሮቲን የበለጸጉ ስራስሮችና ቦሎቄ ፣ ቅባት ያልበዛባቸው እና ብዙ እሳት ያልመታቸው ምግቦች በአመጋገብ ስርአትዎ ውስጥ መካተት አለባቸው ይላሉ።

ከሜዲትራንያን የአመጋገብ ስርአት ጋር ተዋህዶ ገበታ ላይ የማይጠፋው ቀይ ወይን ግን በዚህ ሂደት ውስጥ አላስፈላጊ እንደሆነም ነው ዶክተር ኒውፖርት የሚናገሩት ፤ ስለዚህም በንጹህ ውሃ እና መሰል ፈሳሾች ምግብዎን ቢወስዱት መልካም ነው።

በንጥረ ነገሮች የበለጸጉ ምግቦችን ለሰውነትዎ ቢመርጡ

ከነበሩበት ሁኔታ ተላቀው ወደ አዲስ ምዕራፍ ሲሸጋገሩ ለተጎዳው ሰውነትዎ የተመረጡና እጅግ አስፈላጊ የሆኑ ምግቦችን መውሰዱ ዋስትና ይሰጥወታል ።

በዚህ በኩል እነዚህ ምግቦች ውጤታማ ናቸው ፤

ከስንዴ ዘር የሚገኙ ምግቦች ፤

እነዚህ የአሚኖ አሲድ አይነቶች ለሰውነትዎ ብርታትና ጥንካሬን ከመስጠታቸውም ባለፈ ፤ በሰውነትዎ ውስጥ አላስፈላጊ የሆነ የስኳር ፣ የአልኮል እና ሌሎች እጾችን ወይም መድሃኒቶችን ለማስወገድ ያግዙዎታል ።

ኦሜጋ 3 ፋቲ አሲድ ፥ እነዚህ ደግሞ ከመጠን በላይ በወሰዱት የአልኮል መጠጥ የተጎዱ የሰውነት ክፍሎችዎን እንዲሁም በመጠጥ የተጎዳን የልብ ክፍልን እና የተዛባውን የስርአተ ምግብ መፈጨት ሂደትን እንዲስተካከል ያስችላሉ ።

ከዚህ ባለፈም ከመጠን በላይ በሆነ የአልኮል መጠጥ የተዛባውን እና የጠፋውን የማስታወስ ችግርን ለማስወገድ እና የአዕምሮ ክፍልዎ ያጣውን ነገር ለማስተካከልም ይረዳሉ ።

የአሳ ዘይት እና ዘቢብ ደግሞ በዚህ ይዘታቸው የበለጸጉ እና በቀላሉ ሊያገኟቸው የሚችሏቸው ምግቦች ናቸው ።

በቪታሚን ኤ የበለጸጉ ምግቦች ፥ በዚህ ይዘታቸው የበለጸጉ ምግቦች በጠጡት የአልኮል ብዛት በጉዳት የሳሳ እና ምናልባትም የተበላሸ አጥንትዎን እና ጥርስዎን የማገገሚያ ጊዜ ይሰጡታል ።

ከእህል በበለጠ አልኮልን ወስደው ላቋረጡ ጠጭዎች ቪታሚን ኤን መጠቀም ከካንሰርም ይጠብቃቸዋል።

ቪታሚን ቢ ፥ ይህ ደግሞ በመጠጥ ብዛት ደንዝዞ የነበረውን የሰውነትዎን የነርቭ ስርአት ለማስተካልና ንቁ ለማድረግ ያግዝዎታል ።

ከዚህ በተጨማሪም ሰውነትዎን ዘና በማድረግ እና ከድብርት በመከላከል ከአላስፈላጊ ጭንቀትና ወደ ነበሩበት ሱስ እንዳይመለሱም ያግዙዎታል ።

ቪታሚን ሲ ፥ በቀላሉ የሚያገኟቸው በቪታሚን ሲ የበለጸጉ ምግቦች ደግሞ አጠቃላይ የሰውነትዎን ሁኔታ ለማስተካል የሚረዱ ናቸው ፤ የተዛባውን የደም ዝውውር ስርአትዎንም ያስተካክላሉ ።

በአመታት የአልኮል ብዛት ከጥቅም ውጭ የሆነውን ጉበትም የተስተካከለ እና መደበኛ ስራውን እንዲሰራ ያስችሉታል ።

በቪታሚን ኢ የበለጸጉ ምግቦች ፥ እነዚህ ምግቦች በአልኮል ብዛት ለተዳከመውና ለተጎዳው ሰውነትዎ የተዛባውን የልብ ስርአት ለማስተካከልና የደከሙትን የሰውነትዎን የጡንቻ ክፍሎች በማበርታት የተስተካከለ ገጽታዎን ለመመለስ ያግዛሉ ።

አነቃቂ ነገሮችን አይጠቀሙ ፤

ምናልባት ጠዋት ሲነቁ አንድ ሁለት ሲኒ ቡና እና የሻይ መጠጦች መልካም ሊሆን ይችላል ። በካፌይን የበለጸጉ መጠጦች ሲበዙ ግን መዘዘኛ ናቸው እና እነሱን ባይጠቀሙ መልካም ነው ይላሉ ዶክተር ኒውፖርት ።

አብዛኞቹ ከአልኮል ሱስ ያገገሙ ሰዎች በካፌይን የበለጸጉ መጠጦችን አብዝተው ሲወስዱ ይታያል ፥ ይህ ደግሞ በደም ውስጥ ያለውን ስኳር በማብዛት ጤናዎን አደገኛ ሁኔታ ውስጥ ይከተዋል ።

ከፍተኛ ጭንቀት ፣ የእንቅልፍ እጦት ፣ መቅበዝበዝ ወይም ድንገተኛ እና ያልታሰበበት የሰውነት እንቅስቃሴ እና ያልተለመደ እና ጤነኛ ያልሆነ የሽንት ብዛት ደግሞ በዚህ መልኩ የተጠመዱ ሰዎች መገለጫዎች ናቸው ።

ለዚህ ደግሞ የበዛ የቡና ፣ የስፕሪስ ፣ ለስላሳ መጠጦች ( እንደ ኮካ ኮላ ያሉ ) እንዲሁም ጣፋጭ ቼኮሌቶችን ባይጠቀሙ መልካም መሆኑን ይናገራሉ ።
ለሚያገግመው ሰውነትዎ አነቃቂ ነገር ወይም ካፌይን የሌለበት አረንጓዴ ሻይ ፣ ንጹህ ውሃ ከቻሉ የታሸጉ እንዲሁም በውሃ ቀጠን ያለ የፍራፍሬ ጭማቂዎችን መውሰዱም ይመከራል ።

የሲጋራ ሱስ ካለብዎት ያቁሙ ፥

የሲጋራ ሱስ ካለብዎት ሳያመነቱ ቢያቆሙት ይመከራል ። የአልኮል መጠጥ ሱሰኛ የሆኑ ሰዎች ካልሆኑት ይልቅ በከፍተኛ ሁኔታ ሲጋራ ያጨሳሉ ፤ እነዚህ ሰዎች ከአልኮል ነጻ ቢሆኑ እንኳን ከሲጋራ ሱስ ሲላቀቁ አይታይም ።

ሲጋራ ማጨስ አደገኛ ቢሆንም አልኮልን ለሚወስዱት ደግሞ ከመርዝም በላይ አደገኛነቱ ይጎላል ፤ ምክንያቱም በአልኮል ምክንያት በነርቭ ላይ አደጋ ከማስከተሉም ባለፈ የአዕምሮ የነርቭ ክፍሎችን ሙሉ በሙሉ ከአገልግሎት ውጭ ማድረግ በመቻሉ ነው ።

ሲጋራን ከአልኮል ጋር ሲወስዱ በሂደት በጭንቅላትዎ ውስጥ ያሉ የደም ማስተላለፊያ ቱቦዎች ላይ ጉዳት በማድረስ በጭንቅላትዎ ውስጥ በቂ የደም ፍሰት እንዳይኖርና ከዛ ጋር ተያይዘው ለሚመጡ እጅግ አደገኛ ሁኔታዎች ያጋልጣል ።

የተደረጉ ጥናቶች እንደሚያሳዩት ብዙዎቹ ከአልኮል ሱሰኝነታቸው ቢላቀቁም ሲጋራ ማጨሱ ላይ ግን ያመነታሉ ፤ ካጨሱ ደግሞ ወደ አልኮል መመለስዎ አይቀርምና ተዳብለው ከሚጎዱዎት ለጤናዎ የሚበጅዎን ቢመርጡ መልካም መሆኑን ባለሙያዎቹ ይመክራሉ ።

መጠጡን ለማቆም ያደረጉት ጥረት ለሲጋራውም ይረዳዎታልና ይጠቀሙበት ፤ የህክምና ክትትል እና የባለሙያ ምክርም ይረዳዎታልና እሱን በማድረግ አደገኛውን ልማድዎን ያስወግዱት ።

ምንጭ ፥ ቦተም ላይን ሄልዝ

Health: እንዴት አንድ ሰው ለሁሉም የጉበት ቫይረስ ፖዘቲቭ ሊሆን ይችላል?

$
0
0

Print

እንደሚታወቀው የጉበት በሽታን ሊያስከትሉ የሚችሉ የተለያዩ ምክንያቶች ያሉ ሲሆን ከእነዚህም ውስጥ ቫይረሶች በዋናነት የሚጠቀሱ ናቸው፡፡

ጉበትን ከሚያጠቁ ዋና ዋና ቫይረሶች ደግሞ ዋነኛው ‹‹ሂፖታይተስ›› በመባል የሚታወቁት አምስት አይነት ቫይረሶች ሲሆኑ ከእነዚህም አንዱ ‹‹Hepatitis B virus›› የተባለው ሲሆን ሁለተኛ ደግሞ ‹‹Hepatitis C virus›› የተባለው እና በጠያቂያችን ላይ የተገኙት ናቸው፡፡ እነዚህ ቫይረሶች ለጉበት በሽታ በተለይም በታዳጊ አገራት ዋና መንስኤ ናቸው፡፡ የሚያስከትሉት በሽታም አጣዳፊ ወይም ስር የሰደደ ሊሆን ይችላል፡፡ ይሁንና ምንም አይነት በሽታ ሳያስከትልም ወይም ከአጣዳፊ በሽታም ካገገሙ በኋላ በተወሰኑ ታማሚዎች ላይ ምንም በሽታ ሳያስከትል በደም ውስጥ ሊገኙ ይችላሉ፡፡ (B እና C የተሰኙት አይነቶች)፡፡ በሌላ አገላለፅ የቫይረሱ ተሸካሚ ከቫይረሱ ጋር አብሮ ኗሪ ናቸው ማለት አይደለም፡፡ ምናልባት ለሌላ የጤና እክል ካልተዳረጉ በስተቀር በሽታው አያገረሽም ወይም ጎልቶ አይወጣም፡፡ የማገርሸቱ እድልም በጣም ትንሽ ነው፡፡ ስለሆነም ጉበትን ለጉዳትና ለተጨማሪ ኢንፌክሽ የሚዳርጉ ሁኔታዎችን በማስወገድ እና በመከላከል ማገርሸቱን መከላከል ይቻላል፡፡ ስለዚህም ጠያቂያችን ይህን ከማድረግ ባለፈ ምንም ሊያሳስቦት አይገባም፡፡ በእርግጥ እነዚህ የቫይረሱ ተሸካሚዎች በደም ንክኪ ወይም በልቅ የግብረ ሥጋ ግንኙነት ወደ ሌላ ሰው ሊያስተላልፉ ስለሚችሉ መጠንቀቁ ተገቢ ነው፡፡

ጉበት በቫይረስ መጠቃቱን እንዴት ማወቅ ይቻላል?

ይህም ጠያቂያችንን ያሳሰባቸው ሌላው ጥያቄ ነው፡፡ በተለይም የላቦራቶሪ ውጤታቸው ‹‹ፖዘቲቭ›› መባሉ፡፡ እንደማንኛውም በሽታ የጉበት በሽታም መጠቃቱና መጎዳቱን ለመለየት የሚረዱ ዋና ዋናዎቹ ዘዴዎች በህመምተኛው ላይ የሚደርሱት የበሽታ ምልክቶች፣ የላቦራቶሪ ምርመራዎች፣ የአልትራሳውንድ ምርመራዎችና ሌሎችም ናቸው፡፡ ሁሉም የየራሳቸው ፋይዳ አላቸው፡፡

ከልዩ ልዩ የላቦራቶሪ ምርመራዎችም ውስጥ የቫይረሱን በደም ውስጥ መኖር የሚጠቁሙ የተለያዩ የምርመራ አይነቶች ያሉ ሲሆን በጥቅሉ ‹‹Viral Markers›› ተብለው ይጠራሉ፡፡ እነዚህም ሰውነታችን ኢንፌክሽኑን ለመቋቋም በሚያደርገው የመከላከል ሂደት ውስጥ የሚከሰቱ የቫይረሱ ‹‹አንቲጂኖች›› ወይም ‹‹አንቲቦዲዎች›› ናቸው፡፡ ከእነዚህም አንዱ በጠያቂያችን ደም ውስጥ የተገኙት እነዚህ ማርከሮች (ጠቋሚ ፕሮቲኖች) ናቸው፡፡ እነዚህም በአጣዳፊ በሽታ ወቅት ብቻ ሳይሆን ስር የሰደደ ህመም (Chronic viral Hepatitis) አሊያም በሽታው በሌለበት የተሸካሚነት ሁኔታም ሊገኙ ይችላሉ፡፡ በጠያቂያችን ላይ የበሽታ ምልክቶች ያለመኖራቸው የቫይረሱ ተሸካሚ እንጂ ታማሚ አለመሆናቸውን ስለሚያረጋግጥ ሊጨነቁ አይገባም፡፡ ጥንቃቄ ማድረጉ ብቻ በቂ ነው፡፡ ቤተሰብም መመርመሩ ከቫይረሶቹ የደም፣ የግብረ ሥጋና የወሊድ ተላላፊነት አንፃር ለጥንቃቄ ሲባል ነውና አይረበሹ፡፡

ለመሆኑ ቫይረሱ ሄፖታይተስ እና ህክምናው ምን ይመስላል? የሚለው ሌላው የአቶ መላኩ ጥያቄ ነው፡፡ አጣዳፊ የጉበት ኢንፌክሽ በሆስፒታል ውስጥ ተኝተው መታከም ካለባቸው በሽታዎች አንዱ ነው፡፡ እንዳብዛኛው የቫይረስ በሽታዎች ቫይረሱን ሙሉ ለሙሉ የሚያጠፉ ፈዋሽ መድሃኒቶች ባይኖርም በአሁኑ ወቅት በዓለም አቀፍ ደረጃ ግን ከፍተኛ ለውጥ የሚያመጡ መድሃኒቶች ተገኝተው በጥቅም ላይ መዋል መጀመራቸው ሌላኛው አስደሳች ነገር ነው፡፡ በሽታው ተወሳስቦ ለከፋ ጉዳት ለሞት እንዳያደርስ የሚያደርጉ የተለያዩ ህክምናዎችም አሉት፡፡ ዋና ዋናዎቹ የሚከተሉት ናቸው፡፡

– የበሽታው ዋነኛ መገለጫ የሆኑትን ምልክቶች ለመግታት የሚዳርጉ እገዛዎች ማለትም ትውከትን ማስቆም፣ ህመምን ማስታገስ፣  ምግብን የግሉኮስ እርዳታ መስጠት ትኩሳትን ማስታገስ እና የመሳሰሉትን ያካትታል፡፡

– የሚያባብሱ ነገሮችን ማስወገድ ማለትም አልኮል፣ አንዳንድ መርዛማ መድሃኒቶችንና የመሳሰሉትን ማስወገድ፡፡

– ውጤታማ ፀረ ቫይረስ መድሃኒቶችን መስጠት፡፡

– ሌሎች ተጓዳኝ ህመሞች ካሉ በአግባቡ ማከም፡፡

– ተገቢውን የቅርብ ክትትልና እርዳታ ማድረግ ናቸው፡፡

– አጠቃላይ ምርመራዎችን በማድረግ የተዳከመ የቫይረሱ አይነት እንዳለብንና እንደሌለብን በማረጋገጥ ቫይረሱ እርስዎ እንደጠቀሱት ያለህመም ስሜት የሚገኝም ከሆነ በበቂ ህክምና ወደ ባሰ ሁኔታ እንዳይሄድ ማድረግ ይገባል፡፡

አንባቢያን ስለዚህ ህመም ማወቅ ያለባቸው አጋላጭ ሁኔታዎች ምን ምን ናቸው?

ቫይረሶቹን ወደ ደም ውስጥ ብሎም ወደ ጉበት እንዲደርስ የሚያጋልጡ ሁኔታዎች ዋነኞቹ የሚከተሉት ናቸው፡፡

– በእርግዝና ወይም በወሊድ ወቅት ከእናት ወደ ልጅ፣

– ልቅ የግብረ ሥጋ ግንኙነት (በተለይም ቢ ለተባለው አይነት)

– የደም ልገሳ (በተለይም ሲ ለተባለው አይነት)

– በቀዶ ህክምና መሳሪያዎች ሳቢያ እና

– በጉበት ልገሳና ዝውውር ምክንያት ናቸው፡፡

ይሁንና ቫይረሶቹ ወደ ጉበት ደረሱ ማለት የግድ በሽታውን ያስከትላሉ ማለት አይደለም፡፡ ይህ የሚሆነው አልፎ አልፎ ነው፡፡ በተለይ ጉበት ቀደም ሲል በተጠቀሱት በሽታዎች ለምሳሌ በአልኮል ሳቢያ ከተጎዳና እየተዳከመ ከሄደ የቫይረሶቹ ኢንፌክሽኖች ወደ በሽታ የመለወጣቸውን እድል ያስፋፋል፡፡

በተቻለ መጠን የጉበት ህመምን የሚያባብሱ የአልኮል መጠጥ አዘውታሪነት ካለ መቀነስ እንዲሁም የቅባት ምግብ መጠንንና ክብደት መቀነስም ያስፈልጋል፡፡ በቤተሰብዎ ውስጥም በቀላሉ ለደም ንክኪ የሚያጋልጡ ስለታም ነገሮችን በጋራ ከመጠቀም ይቆጠቡ፡፡ ደም ከመለገስም እንዲሁ፡፡ በዚህ አጋጣሚም የኤች.አይ.ቪ ምርመራ ቢያደርጉ እንደሚመከር ይረዱ፡፡ የእነዚህ ቫይረሶች መኖር ለኤች.አይ.ቪ መኖር መሰረታዊ አመላካች ባይሆንም መተላለፊያ መንገዳቸው ተመሳሳይነት ያለው በመሆኑ አብሮ የመከሰት ዕድል አላቸው፡፡ ልጆችዎንም በማስመርመር በአገራችን የሚሰጠውን የፀረ ጉበት ቫይረስ (በተለይ ለ‹‹ቢ››) ክትባት እንዲወሰዱ ያድርጓቸው፡፡ ከዚህ በተረፈ ለወደፊት የጉበት ህመም ማለትም ቫይረሱ ወደ ጉበት ህመምተኝነት የመቀየሩ ጉዳይ በጥቂቶች ላይ የሚስተዋል በመሆኑ ተጋላጭነትን የሚቀንሰው አንዱ ወሳኝ ጉዳይ ንፁህ እድልም ጭምር ነውና መልካም ዕድል

Health: ካሮትን ቀቅሎ የመብላት 5 የጤና በረከቶች

$
0
0

carrot
በሳሙኤል ዳኛቸው

ካሮት በተፈጥሮ በያዘው የቫይታሚን እና የፋየበር ክምችት ለጤናችን እጅግ ጠቃሚ መሆኑ ይነገርለታል።

ሰውነታችን ወደ ቫይታሚን ኤ የሚቀይረው ካሮቲኖይድ የተባለውን ጠቃሚ ንጥረነገርም በበቂ ሁኔታ ይዘዋል።

ፋልካሪኖል የተሰፀ እና ካንሰርን በመዋጋት አቻ የሌለው ንጥረነገርም ሌላው የካሮት የጤና ገፀ-በረከት ነው።

ታዲያ እነዚህንና ሌሎችን በርካታ የጤና ጠቀሜታዎች የሚያስገኝልንን ካሮትን በምን መልኩ ብንመገበው የተሻለ ተጠቃሚ እንሆናለን? የሚለው የብዙዎቻችን ጥያቄ ነው።

1.ካንሰርን የመከላከል አቅሙ ስለሚጨምር፣

የበሰለ ካሮት ካንሰር የመከላከል አቅሙ ከጥሬው በ25 በመቶ ከፍ ያለ መሆኑን ነው ጥናቶች የሚያመለክቱት።
ጥናቶች በተጨማሪም ካሮቱ በአንድ መያዣ ውስጥ መብሰሉ አስፈላጊ ንጥረነገሮቹን በአንድ ላይ ማግኘት እንድሚያስችልን ይገልፃሉ ።

2. ጣፋጭነቱ ስለምጨምር፣

ካሮትን ጣፋጭ ጣዕም እንዲኖረው የሚያደርጉት ተፈጥሯዊ ስኳሮች የሚፈጠሩት ካሮቱ በሚበስልበት ወቅት ነው።

3 የአንቲኦክሲዳንትስ መጠን በእጅጉ ስለምጨምር፣

የበሰለ ካሮት ካልበሰለው ጋር ሲነፃፀር ጠቃሚ አንቲኦክሲዳንትስ ከ34 በመቶ በበለጠ አለው።

4.የቫይታሚን መጠኑ ስለምጨምር፣

ካሮት በሚበስልበት ወቅት የከለር፣ የቅርፅ እና የጣእም ለውጥን ብቻ ሳይሆን የሚያስከትለው፥ በውስጡ የሚፈጠሩት ውህዶች እና በውስጣቸው የሚገፀው የቫይታሚን መጠንም በተመሳሳይ ይቀየራል።

5.የካሎሪ መጠኑ ከፍተኛ በመሆኑ

የበሰለም ሆነ ያልበሰለ ካሮት የተሻለ ካሎሪን በማስገኘት ረገድ የሚታማ ባይሆንም በተመሳሳይ የበሰለው ካሮት በሁለት እጥፍ ካልበሰለው ካሮት የተሻለ ካሎሪ ሰውነታችን እንድያገኝ ያስችላል።

ምንጭ፦http://www.dailymail.co.uk/health


Health: ከባለቤትህ ጋር ስምምነት ፈጥረህ ለመኖር የምትችልባቸው 7 ዘዴዎች

$
0
0

‹‹ከባለቤቴ ጋር ስምምነት መፍጠር ተሳነኝ 

እባካችሁ አንድ በሉኝ››

ዕድሜዬ ሰላሳዎቹ መጨረሻ አካባቢ ሲሆን ባለቤቴም በዚሁ ክልል አጋማሽ ላይ ናት፡፡ ለአስር ዓመት ያህል በትዳር ህይወት አሳልፈናል፡፡ ደስ የሚሉ ሁለት ህፃናት ያሉን ሲሆን ሁለታችንም ዲግሪና ቤተሰባችንን ሊያስተዳድር የሚችል በቂ ገቢ እናገኛለን፡፡ ችግሬ ከባለቤቴ ጋር በነገሮች አለመስማማት ነው፡፡ ከሰዎች ጋር ተግባቢና ተጫዋች ስሆን ኧረ ለሌላው ችግርም አማካሪ ነኝ፡፡ ሚስቴ እኔ የማደርገው በብዛት አይጥማትም፣ የሆነ ነገር ገዝቼላት ስመጣ እንኳ አመሰግናለሁ በማለት ፈንታ ማሽሟጠጥና ማጣጣል ነው የሚቀናት፡፡ ይቅርታ የሚባል ነገር ፈፅሞ አልፈጠረባትም፡፡ ስህተቷን በጩኸትና ለቅሶ ለመሸፈን ትሞክራለች፡፡ ቤቴን ለማሻሻል ብዙ ነገሮችን ሞከርኩ፣ ከእኔም ችግር እንዳለ ለመፈተሽ ጣርኩ፡፡ አልሆነም፡፡ በዕውነት እንዳሰብኩት እየሆነም አይደለም፤ ደካከምኩኝ፡፡ ወደ ቤተክርስቲያን እንኳ አብረን እየሄድን ግማሽ መንገድ ሳንጓዝ መጨቃጨቅ እንጀምራለን፡፡ ትዳራችን በሰላምና በፍቅር መዝለቅ ይችል ዘንድ ምን ማድረግ እንደሚገባን ለሌላም ስለሚጠቅም ምክራችሁን ብትለግሱን፡፡

SONY DSC

SONY DSC


መልስ፡- መቼም ስለትዳር ብዙውን ጊዜ ብናወጋ በቀላሉ የምንጨርሰው አይመስለኝም፡፡ በተለያዩ አምዳችን ላይ አንስተናል፤ በሰዎች ላይም የሚያደርሰውን ተፅዕኖ በመረዳት ብዙ መንፈሳዊና አለማዊ ፀሐፍትም በየፊናቸው አውግተዋል፡፡ አሁንም ቢሆን በየትኛው የትምህርት እርከን ላይ እንደምንመድበው ባይገባንም ትዳር በህይወት ዘመናችን በርካታ ጉዳዮችን የምንማርበት መድረክ እንደሆነ እንረዳለን፡፡ በዕውነት ልክ እንደሌላው ስርዓተ ትምህርት ተቀርፆለት ባለትዳሮች በዘመናቸው የሚማሩበት ዕድል ቢኖር ተመሳሳይ ችግሮች ገነው ባልተፈጠሩ፤ ቢፈጠሩ እንኳ በቀላሉ መፍትሄ ባገኙ ነበር፡፡ በቅድመ ጋብቻ ወቅት የነበረውን ለስላሳ ባህሪና ሁሌ የሚናፈቅ መረዋ ድምፅ በድህረ ጋብቻ ጊዜ ሊጎረብጥና ጆሮ ሊያሳምም ይችላል፡፡

በትዳር ህይወት ውስጥ የሚገኙ ብዙ ነገሮች አሉ፡፡ መቼም የአምላክ በረከቱ የትየለሌ ነው፡፡ ‹መባረክ› በገንዘብና ቁሳዊ ነገር ብቻ መስሎን ከመንገድ ወጣ ማለት ጀመርን እንጂ አሰጣጡ በተለያየ መንገድ ነው፡፡ ላንዳንዶቻችን ብዙዎች እንደምናስበው በንብረት፣ ለሌላኛው በሰው፣ ለሌላው ደግሞ በዕውቀት፣ ለሌሎቻችን በመንፈስ ፍሬዎች (ፍቅር፣ ሰላም፣ ደስታ፣ ትዕግስት፣ ቸርነት፣ በጎነት፣ እምነት፣ የዋህነትና ራስን መግዛት) ይባርከናል፡፡ በእርግጥ ብዙዎች ያለንን አናውቅም፤ ያወቅነውም ቢሆን ያለንን በአግባቡ አልተጠቀምንም፣ ለመጠቀምም ፈቃደኞች ያልሆንን ብዙ አለን፡፡ ያልገባን ነገር ምን መሰላችሁ ያለን የሚበዛልን የያዝነውን በመደበቅና ያለጥቅም ቁጭ እንዲል በማድረግ ሳይሆን እያወጣን ለሌላው እያካፈልን ስራ ላይ ስናውለው ነው፡፡

ሌላው ከፅሑፍህ የምንረዳው ከሰዎች ጋር በጣም ተግባቢ መሆንህን ነው፡፡ ስለዚህ ነገር በእውነት ደስ ብሎናል፡፡ እያንዳንዱ ግለሰብ ሊኖው ከሚገባ ቁልፍ ማህበራዊ ክህሎት ውስጥ አንዱ ከሌሎች ጋር ተግባብቶ መኖር ነው፡፡ አየህ እንደነገርከን ከሰው ጋር መልካም ግንኙነት ሲኖርህ የተለያዩ ሀሳባችን መካፈል ያስችልሃል፡፡ ሰዎችን ከጭንቀታቸው እረፍት እንዲያገኙ ስታደርግ፤ ውስጥህ ያለውን ዕምቅ አቅምና ክህሎት በማውጣት ለሌሎች መፍትሄ መሆን ስትጀምር በእርግጥ ደስ ይላል፡፡ ታዲያ አንተም በዚህ ሂደት ውስጥ ብዙ የምትማራቸው ነገሮች እንዳሉ እውን ነው፡፡ ከሌሎች ሰዎች ትማራለህ፤ ከራስህም ድርጊትና ተሞክሮ እንዲሁም በህይወትህ ከሚገጥሙህ መነሳትና መውደቅ ትማራለህ፡፡ ይህን ወደፊት አጠናክረህ ልትገፋበት የሚገባ መልካም ባህሪና ትልቅ ችሎታም ነው፡፡

አምላክህ እግዚአብሔር በሰጠህም ልጆች በመደሰትህ መልካም ነገር ነው፡፡ በህይወታችን ብዙ የምናማርራቸው ነገሮች እንዳሉን ሁሉ ለቁጥር የሚታክቱ ደስ የሚሉና ስለነዛም ነገር ልናመሰግንባቸው የሚገቡ ስጦታዎች አሉን፡፡ አንዳንዴ ስራ ውለህ ደክመህ፣ ቤትህ ውስጥም ከባለቤትህ ጋር በገጠመህ ጊዜያዊ ችግር ተመስጠህ ሳለህ ልጆችህ በደስታ ሲቦርቁ ስታይ ጭንቀትህን ያስረሱሃል፡፡ ከነበርክበትም ጊዜያዊ ቻናል ያወጡህና ወደ ኤፍ.ኤም… ያስገቡሃል፡፡ ልጆችህን ስታስብ ዛሬንና ነገን የተሻለ ነገር እንድትሰራ ያደርግሃል፤ ያበረቱሃልም፡፡ እንግዲህ ወንድማችን በህይወት ብዙ ተግዳሮቶች ቢኖሩም፣ በቀላሉም አሁን እንደምንላቸው ቶሎ እውን ባይሆኑም መልካም፤ ብሩህና ጥሩ የሆነውን ነገር ባሰብክ ቁጥር መልካምና የተሻለ ነገር ትሰራለህ የሚል እምነት አለን፡፡ መልካም አስብ፣ መልካም ነገር ስራ፣ መልካምም ነገር ይከናወንልሃል፡፡

ወደ ዋናው ቁም ነገሩ ስንመጣ ጥያቄህ ላንተ ብቻ ሳይሆን ለበርካታ ጥንዶችና ባለትዳሮች እንቆቅልሽ የሆነ ነገር ይመስለናል፡፡ በትዳርም ሆነ ማንኛውም ግንኙነት አልጋ በአልጋ የሆነ ምንም ነገር እንደሌለ እናምናለን፡፡ እንዲኖርም የምንጠብቅ ከሆነ የዋህነት ነው፡፡ ነገር ግን በህይወት የሚገጥሙንን ክስተቶች በአግባቡና አዎንታዊ በሆነ መንገድ ለመመለስ ከሞከርን ትዳራችንን ወደ ፈለግነው አቅጣጫ ልናመጣው እንችላለን፡፡ መሰረታዊ ከሆነው የስሜት ፍላጎቶች (የማፍቀርና የመፈቀር፣ ለራስ ያለን መልካም እይታ፣ ራስን የመቻል…ወዘተ) ባሻገር አንዳቸው የሌላኛውን ፍላጎት ማወቃቸው ለትዳራቸው መጠናከርና መሻሻል ወሳኝ የሆኑ ነገሮች ናቸው፡፡

ስለዚህ ጉዳይ በአንድ ወቅት አንዱ ወዳጃችን ሚስቶች ከባሎች ምን ይፈልጋሉ? ባሎችስ ከሚስቶቻቸው ምን ይሻሉ? የሚል ፅሑፍ የላከልንን መነሻ በማድረግና ሌሎችን መፅሐፍት በማጣቀስ የሚከተሉትን ምክሮች ተግባራዊ ብታደርጉ ትዳራችሁን አሁን ካለበት ወደተሻለ ደረጃ ታደርሳላችሁ ብለን እነሆ ብለናል፡፡ አሰጣጣችንም ለአያያዝ ስለሚያመች በአግባቡ በመያዝ በህይወታችሁ እንድትለማመዱ መሞከር የእናንተው ባለጉዳዮቹ ድርሻ ነው፡፡ ለአሁኑ እስቲ ከሚስቶች ፍላጎት እንጀምር፡፡

1. ሁልጊዜ እወድሻለሁ በላት

መቼም ስታገባት ተገደብ እንዳልሆነ ይገባናል፡፡ ወደህና ፈቅደህ ከሆነ ደግሞ ያገባሃት ልብህ ውስጥ ያለውን በማውጣት እወድሻለሁ በላት፡፡ ይህን ማለት እኮ ወጪ የለውም፡፡ ብላት ሌላ ነገር ይሰማት ይሆናል፣ ወይም ይህ ክብሬ ይቀንስብኛል አትበል፡፡ ከአምላክህ ቀጥሎ ክብርህ እርሷ ናት፤ ለርሷም አንተው ነህ፡፡ እዚህ ላይ ታዲያ በል ስላልንህ ብቻ ሳይሆን በእርግጥም ስለምትወዳት ነው ማለት የሚገባህ፡፡ መፅሐፉስ ከተደበቀ ፍቅር ግልፅ ዘለፋ ይሻላል… ሲል አላነበብክምን? አየህ እህቶች ሁሌም ቢሆን መወደዳቸውን በንግግርና በድርጊት እንድታረጋግጥላቸው ይፈልጋሉ፡፡ በእርግጥ የሚከብደው በውስጥህ የሌለውን ፍቅር ለማለት ስትሞክር ነው፡፡ ያ ማታለል ነው፣ በራስ ላይ የከፋ የስነልቦና ችግር መፍጠር ነው፡፡ ገባህ የምንልህ?

2. መረዳትና ይቅር መባልን (Understand and forgiveness)

ከሚስቶችም ሆነ ከሌሎች ሰዎች ጋር ባለን ግንኙነት አንዳችን ሌሎች የሚሉትን ነገር መረዳት መቻላችን ወሳኝ ነገር ነው፡፡ የሚናገሩትንና የሚያደርጉትን ካልተረዳን፣ በነርሱም ቦታ ሆነን ካልተመለከትን አተረጓጎማችንም የተሳሳተ ነው የሚሆነው፡፡ ማንም ሰው ፍፁም ስላልሆነ ባለቤትህም ጥፋት ልትሰራ ትችላለች፡፡ ችግሯን በመረዳት ይቅርታ ለማድረግ ወደኋላ ማለት አይገባህም፡፡ እርሷ እንዳልፈጠረባት ብትነግረንም አንተ ግን ሁሌም ቢሆን ይቅር ከማለትና ከመረዳት መቦዘን የለብህም፡፡ በዚህ ሂደት ውስጥ እርሷን ይቅርታ ማድረግን፣ ትዕግስትን፣ ቻይነትን፣ ታስተምራለህ፡፡

መማር ዩኒቨርሲቲ ገብቶ በመመረቅ ብቻ ነው ለማለት አንደፍርም፣ ይልቁኑ አብረውን ከሚውሉ ሰዎችም መለወጥ እንዳለ እንረዳለን፡፡ ስለዚህ የምንልህ ነገር ከገባህ መልካም ግንኙነት መዝለቅ የሚችለው ይቅር በመባባል ነው፡፡ የምድሩ ብቻ ሳይሆን የሰማዩም የሚቀናው ይቅር ከልብ ስንባባል ነው፡፡ ቂም አርግዞ ብዙ መንገድ መጓዝ አይቻልም፡፡ ጊዜው ሳይደርስ ይጨናገፍና ለችግር ይዳርገናል፡፡

3. በቂ ጊዜ ማግኘትን 

ብዙዎች ሆዳችንን ለማሸነፍ አሊያም ዝናን ለማቅረብ ስንል አብዛኛውን ጊዜያችንን በስራ ማሳለፋችን አይቀርም፡፡ መድከማችን ለበጎ ቢሆንም የትዳር ህይወታችንን ግን እንዲጎዳ መፍቀድ የለብንም፡፡ ችግራችን በስራ ደክመን ጀርባችንን ከፍራሽ ላይ ለመጣል ስንጣደፍ የትዳር ህይወታችንንም አብረን እናጋድማለን፡፡ በድካም ያተረፍነውን በሽታ ስንተካከም ወንድማን እህት ሆነን እንከርማለን፡፡ የምንልህ፣ ከገባህ ሚስቶች በቂ የሆነ ጊዜ ከባሎች ማግኘትን ይሻሉና የምትወያይበት፣ አብረኻት የምትዝናናበት፣ ዕቅድህን ነጻና ግልፅ በሆነ መንገድ የምታዋይበት ጊዜ በሚገባ ስጣት፡፡ እግዚአብሔርን ባትፈራ ጥላህ ጊዜ ወደሚሰጣት ቦታ በሄደች ነበር፡፡ ነገር ግን እምነቷ ልቧን እንዳተሸፍት ስለሚከለክላት ስሜቷን ብቻ በማራቅና በመነጫነጭ ዕድሜዋን እንድትገፋ ያደርጋታል፡፡ ስሊሊህ ከዚህ አንጻርም ያላችሁበትን ሁኔታ ማጤን አግባብ ነው እንላለን፡፡

4. ከእምቢታ ይልቅ እሺ መባልን

ብዙውን ጊዜ ባለቤትህም ሆነች ልጃችሁ በሚጠይቁህ ነገር ላይ አይሆንም/እምቢታን ካስለመድካቸው አንተን መሸሻቸው እውን ነው፡፡ ምክንያቱም ሌላም ጊዜ መጠየቅ ቢፈልጉ እንኳ እሺ አይለንም የሚል ግምት ስለሚኖራቸው የጨለመ አመለካከትን ያዳብራሉ፡፡ አሁን ባለው ሁኔታ ሳይሆን በፊት በነበሩ ክስተቶች ላይ ይመረኮዛሉ፡፡ የጠየቁህ አይሆንም ከማለትህ በፊት ደግመህ ለማሰብ ሞክር፡፡ ይህን ስንልህ ሁሉንም ነገር እሺ በላቸው እያልን እንዳልሆነ ይታወቅልን፡፡ በእርግጥም ማለት ከተገባህ ለምን እንዳልካቸውና ለሁላችሁም ጥቅም እንደሆነ ግለፅላቸው፡፡ በተቃራኒው ደግሞ ለምትጠይቀው ነገር አዎንታዊ ምላሽ በመስጠት ግንኙነታችሁን በቀላሉ ሲለወጥ ማየት ትችላለህ፡፡… እሺ ይበልጣል ከሺ… ሲባል አልሰማህም? አየህ ሰዎች እሺ በመባል ከጭንቀት ያርፋሉ፤ የተለያየ መላምቶችን እያሰቡ አዕምሮአቸውን በመጥፎ ነገር ከመሙላት ይተርፋሉ፡፡

5. መደመጥን

ማድመጥ ግንኙነትን ሊያሻሽሉ ከሚችሉ ነገሮች ውስጥ አንዱ እንደሆነ በተለያዩ አምዶቻችን ላይ ያነሳን ይመስለናል፡፡ በንግግራችን ወቅት ሀሳባችንን ሳንከፋፍል ትኩረት ልንሰጥ ይገባል፡፡ ማንኛውም ሰው ሚስቶችንም ጨምሮ ከሚያናግሯቸውና አብረዋቸው ካሉ ግለሰቦች መደመጥን ይሻሉ፡፡ ሚስት ከልቡ እየሰማኝ ነው ብላ የተናገረችውን ቁም ነገር ባለቤቷ እንዳልሰማ ብታውቅ ምንኛ ሊያማትና ባለቤቷ አብሯት እንዳልነበር ስትረዳ እንደሚሰማት መገመት ትችላላችሁ፡፡ ይህ ደግሞ ለርሷ ቦታ እንደማንሰጣት ሊሰማት ይችላል፡፡ በሌላ አነጋገር የምታመጪው ሀሳብ፣ ወሬ የትም የሚገባ አይደለም ነው፡፡ ስለዚህ ጉዳቱ ከማየሉ በፊት በደንብ አድምጣት፣ እየተከታተልካት ለመሆኑም የምልክት ቋንቋ አሳያት፣ ከዛም ባለፈ ያለችውን በትክክል ለመረዳት ደግመህ በሌላ ቋንቋ ንገራት፡፡ ስለዚህ የምንልህ ከጆሮ በዘለለ ባለቤትህን ከልብህ ልታዳምጣት ይገባል ነው፡፡

6. ፍቅርና ርህራሄን

ሌላው ጋብቻን ከሚያጠናክሩትና ውጤታማ ከሚያደርጉ ጉዳዮች መካከል አንዳችን ለሌላኛው የምናሳየው ፍቅርና ርህራሄ ነው፡፡ በንግግራችን ወቅት እባክሽን፣ አመሰግናለሁ ቢቻል ደግሞ ለብቻ የምንጠራባቸው ስም ቢኖረን ጥሩ ነው እንላለን፡፡ ሰዎች በኛ ውስጥ ትልቅ ስፍራ እንዳላቸው የሚገነዘቡት በምንለውና በምናደርገው ላይ በመመርኮዝ ነው፡፡ ችግሩ አንዳንድ ጥንዶች ከተጋቡ በኋላ ይህን ነገር ይዘነጋሉ፡፡ አንዳንዴ ተሳስተው እንኳ ጉንጭ፣ ከንፈር አሊያም ግንባር ላይ ያልተጠበቁ/ድንገተኛ አሳሳም አድርገው አያውቁም፡፡

7. የቤት ውስጥ የልጆች አስተዳደግ ኃላፊነትን መጋራት

ሌላው በጣም ሚስቶች የሚሹትና ባሎች ሊረዷቸው ከሚፈልጓቸው ጉዳዮች ውስጥ አንዱ የቤት ውስጥ ኃላፊነትን መጋራት ላይ ነው፡፡ ሁለታችሁም ሰራተኞች እንደመሆናችሁ ቤት ስትገቡ ይደክማችኋል፡፡ ይህን ከግምት በማስገባት በቤት ውስጥ የስራ ክፍፍል ታደርጋላችሁን? ልጆችንስ በመንከባከብ በኩል ኃላፊነት በሚሰማው መንገድ ትተጋገዛላችሁን? ይህን ካላደረግን ሚስቶች ሊማረሩ፣ ወደፊት ልጅ ሁሉ ሲባል ላይስቡ ይችላሉ፡፡ ሁሉም የጋራ ፍሬዎቻችሁ እንደመሆናቸው በጋራ ልትንከባከቧቸው የግድ ይላል፡፡ እቤት ውስጥ የሚሰሩ ማናቸውንም ነገሮች እርሷ እስክትልህ ድረስ መጠበቅ የለብህም፡፡ ለዚህ ደግሞ ፍትሃዊ የሆነ የስራ ክፍፍልን ማድረግ ይጠይቃል፡፡

እንግዲህ የሰው ልጅ ፍላጎት እንዲሁ በቀላሉ የሚገታ ባይሆንም አቅምህ በፈቀደ መጠን ከላይ የጠቀስናቸውን ምክሮች ተግባራዊ ብታደርግ፣ ጋብቻን የሚያፀናው አምላክም ሲፈርስ ማየት ስለማይሻ ይረዳሃል የሚል እምነት አለን፡፡ ሌላው ልታስታውስ የሚገባው… ባሎች ሚስቶቻቸውን እንደገዛ ስጋቸው መውደድ ይገባቸዋል፡፡ ሚስቱን የሚወድ ራሱን ይወዳል፡፡ የገዛ ስጋውን የሚጠላ ማንም የለም፤ ይመግበዋል፤ ይንከባከበዋል፤ ክርስቶስም ለቤተክርስቲያን ያደረገው ልክ እንደዚሁ ነው… የሚለውን ነው፡፡

ከላይ የዘረዘርናቸውን ነጥቦች ሚስቶችም ተግባራዊ ልታደርጉት ይገባል፡፡ ምክንያቱም ጎጂ የሚፀናው በሁለታችንም ጥረትና በእግዚአብሔር እርዳታ ነው፡፡ ከዚህ በመቀጠል ደግሞ ባሎችስ ከትዳራቸው/ሚስቶቻቸው ምን ይሻሉ? የሚለውን አጠር ባለ አገላለፅ ለማቅረብ እንሞክራለን፡፡

– ባሎች ያላቸውን ችሎታና ክህሎት ሚስቶቻቸው እንዲያምኗቸው ይፈልጋሉ፡፡ ይህን ደግሞ እንዲያውቁት በተለያየ መንገድ ግለፁላቸው፡፡ ላከናወኑትም ተግባር በተለያየ መንገድ አበረታቷቸው፡፡ ጀርባ መታ፣ ሳም፣ ባሌ እኮ ባትሆን… የመሳሰሉትን ነገር ማንሳት ተገቢ ይመስለናል፡፡

– ተጨባጭ የሆነ መረጃ ሳታዩ ባላችሁን አትጠርጥሩ፡፡ በሚያደርጉት ነገር እመኗቸው፤ የሞሳድና የሲ.አይ.ኤ ስራ ከመስራትም ይልቅ ልክ እንደዚህ አይነት ምክር የምታገኙበትን ተቋም መጎብኘት መልካም ነው እንላለን፡፡

– ባሎቻችሁን አንዳንዴ በማይፈልጉት አካሄድ ለመለወጥ አትሞክሩ፡፡ በቀላሉ መለወጥ የምትችሉት መጀመሪያ ራሳችሁን ነው፡፡ ባሎቻችሁ ላይ ስህተታችሁን ለመሸፈን አልቅሶ ማታለልና መቆጣት የሚፈጥረው ዘላቂና የተሻለ ነገር የለም፡፡

– ፍቅር የማይለውጠው ነገር የለምና ፍቅራችሁን ሳትሰስቱ ለግሷቸው፡፡ ያለ እናንተ ማን አላቸው ብላችሁ? ይህንንም በተለያየ መንገድ ማለትም በፅሑፍ፣ በመሳም፣ በማቀፍ፣ የተለያዩ ነገሮችን በመስጠት ግለጡላቸው፡፡

– ባሎች መከበርን ይሻሉና ተገቢው ክብር ስጧቸው፡፡ በሚያመጡት አሳብና ምክር ላይ አሉታዊ አስተያየት ለመስጠት አትቸኩሉ፡፡

ለዛሬ ይህንን ካልን የሚበቃ መሰለን፡፡ ጤና ይስጠን እንጂ ወደፊት በዚህ ርዕስ ላይ በሰፊው እናወጋለን የሚል እምነት አለን፡፡ ከሁሉ በላይ ደግሞ አምላካችሁ በትዳራችሁ ላይ ጣልቃ እንዲገባ ጋበዙት፡፡ እርሱ የሌለበት ነገር በሙሉ ከንቱ ነው፡፡ ቸር እንሰንብት፡፡

በኢስላም ማህፀንን ማከራየትና መከራየት እንዴት ይታያል?

$
0
0

 

ዳኢ መንሱር ሁሴን ስለ ማህፀን ማከራየት ከኢስላም አስተምህሮ አንፃር እንደሚከተለው አብራርተውልናል፡፡

ምስጋና ለአሏህ (ሱ.ወ) የተገባ ነው፡፡ ሶላትና ሰላም በአሏህ መልዕክተኛ በሙሐመድ (ሰ.ዐ.ወ) ላይ ይስፈን፡፡

ወደ ዋናው ርዕሳችን ከመግባታችን በፊት እንደ ኢስላም አስተምህሮ የሰው ልጆች የተፈጠሩባቸውን አራት መንገዶች እንመልከት፡፡

የመጀመሪያው መነሻችን የሆኑት የአባታችን አደም (ዐ.ሰ) አፈጣጠር ሲሆን፣ እርሳቸውም ያለ እናትና አባት በአሏኅ ችሎታና ጥበብ ከአፈር መፈጠራቸው ነው፡፡ በመቀጠልም እናታችን ህዋ ደግሞ ያለ ሴት ከአባታችን አደም ጎን ተፈጠሩ፡፡ በሶስተኛ የምናገኘው የነቢዩሏህ ዒሳ (ዐ.ሰ) ከእናት ብቻ ያለ አባት በአሏህ (ሱ.ወ) የ‹‹ሁን›› ቃል የተወለዱበት ተአምራዊ አፈጣጠር ነው፡፡ በመጨረሻ የምናገኘው ብዙሃኑ የአደም ልጆች ከእናትና አባት የተወለድን የምንራባበት መንገድ ነው፡፡
pregnancy-facts04
የሰው ልጆች ምድር ላይ የተገኘንባቸውን መንገዶች ካየን፣ በርዕሳችን ስላነሳነው ልጅ ምናልባትም ከሶስት ወላጆች እንዲገኝ ‹‹ሰለጠንኩ›› የምትለው ዓለም ስላመቻቸችው፣ ‹‹የማህፀን ኪራይ›› ኢስላም የሚለውን ትንሽ እንበላችሁ፡፡

እንደሚታወቀው ይህ ጉዳይ፣ በቀደሙት ጊዜያቶች የማይታወቅና ከቅርብ ጊዜ ወዲህ ተጀምሮ ዓለም ላይ እየተስፋፋ ያለ ነገር ነው፡፡ ከዚህ በፊት ስላልነበረ ቀደምት የኢስላም ምሁራን በጉዳዩ ላይ የተናገሩት ነገር የለም፡፡ በተጨማሪም ታዋቂ የሙስሊሙ ማህበረሰብ መሪዎች (የመዝሃብ ባለቤቶች) የነበሩ፣ ይህን ጉዳይ በኢስላም መፈቀዱን ወይም አለመፈቀዱን የዘገቡትም የተናገሩትም ነገር የለም፡፡

እዚህ ላይ ልብ ልንል የሚገባን ነገር ቢኖር፣ የሙስሊሙ የመዝሃብ መሪዎች ከቁርአን እና ከሐዲስ (የነብዩ ሙሐሙድ አስተምህሮ) ባገኙት ትንተና ሰጥተዋል፡፡ ይህ አይነቱ ትንታኔ ደግሞ ከቁርአን እና ከሐዲስ ቀጥሎ ሙስሊሙ ማህበረሰብ ዘንድ ትልቅ ቦታ አለው፡፡ ሕይወቱንም እዚያ ላይ ባገኘው ሕግ ነው የሚመራው፡፡

ለዚህም ነው ከላይ በጉዳዩ ላይ ከነርሱ የተገኘ ማብራሪያ አለ? ወይስ የለም የሚለውን ለማስቀመጥ የሞከርነው፡፡ እነሱ የሰጡት ትንታኔ የለም ማለት ግን ኢስላም ስለዚህ ጉዳይ የሚሰጠው ብያኔ የለም ማለት አይደለም፡፡ አሏህ (ሱ.ወ) ከቁርአኑ ላይ እንዲህ ብሏል፡-

‹‹በመጽሐፉ (በቁርአን) ውስጥ ምንም (ስለምንም) ነገር (ሳንገልፅ) አልተውንም›› (አል አንአም 38) በሌላ ምዕራፍ ላይም፣ ‹‹ዕውቀቱ ከሌላችሁ የዕውቀት ባለቤቶችን ጠይቁ›› (አል አንቢያእ 7)

ይህ ማለት፣ የትኛውም አዲስ ነገር ቢፈጠር የሚፈጠረው ነገር ጠቅለል ብሎ በተቀመጠው የአሏኅ (ሱ.ወ) ቃል (ቁርአን) እና የመልዕክተኛው ንግግር (ሐዲስ) ሕግ ስር በጊዜው በሚኖሩ ምሁሮች ጥልቅ እይታ እና ግንዛቤ በሚኖሩ ምሁሮች ጥልቅ እይታ እና ግንዛቤ መሰረት ተገቢ የሆነ ትንተና እና ብያኔ ይሰጥበታል፡፡ ከላይ እንደተጠቀሰው፣ ይህ ጉዳይ መጤ ከመሆኑም ጋር አንዳንድ ሰዎች ስለ ጉዳዩ ሰፊ ጥናት ሳያደርጉ፣ በደፈናው ችግር እንደሌለውና ለሰዎች ጥሩ የሕይወት መቀጠያ ዘዴ አድርገው ይገልፁታል፡፡ ነገር ግን ይህ አመለካከት እንደማያዋጣና ጉዳዩን ትኩረት ሰጥተን ልናየው እንደሚገባ በዚህ ጽሑፍ ለመጠቆም እንሞክራለን፡፡

ማህፀንን ስለማከራየትም ሆነ መከራየት አሁን ላይ ያሉ ሙስሊም ምሁራ የሰጡትን ትንታኔ እና ብያኔ ከማየታችን በፊት አላህ (ሱ.ወ) ስለ ሀፍረተ ገላችን ምን እንደተናገረ አጠር ባለ መልኩ እንመልከት፡፡

አንደኛ፡- ‹‹(አማኞች) እነዚያ ብልቶቻቸውን (ከሐራም) የሚጠብቁት…›› (አል ሙእሚኑን፤ 5-6)

ከአንቀፁ እንደምንረዳው፣ አላህ (ሱ.ወ) አንድ ወንድ በሸሪዓዊ መንገድ ከተፈቀደችለት ሴት ውጭ የሚያደርገውን የግብረ ሥጋ ግንኙነት እርም አድርጓል፡፡

ሁለተኛ፡- አሏህ (ሱ.ወ) የሰውን ልጆች ዘራቸውን እና ልጆቻቸውን እንዲጠብቁ አደራ ብሏል፡፡

ሀፍረተ ገላችንን እና ክብራችንን እንዴት መጠበቅ እንዳለብን በአጭሩ ይህን ካልን፣ ወደ ዋናው ርዕሰ ገዳይ ስንገባ ማህፀን ማከራየት ካለምንም የሐሳብ ልዩነት በኢስላም ክልክል (ሐራም) ነው ይሉናል- ሙስሊም በኢስላም ክልክል (ሐራም) ነው ይሉናል- ሙስሊም ምሁራኑ፡፡ ለዚህም የሚከተሉትን ምክንያቶች ያቀርባሉ፡፡

1. የሚወለደው ልጅ የእናት፣ የአባት ብሎም የዘር እውቅናን ሙሉ በሙሉ ይህ ነው ለማለት ብዥታ ውስጥ ይከተላል፡፡ ይህ ብዥታ በኪራይዋ እናት እና በዋናዋ እናት መካከል ወደ ፀብ ይወስዳል፡፡ የሚወለደው ልጅ ከሁለቱ እናቶች የአንዷ እንደሆነ እርግጠኛ ብንሆንም፣ በእርግጠኝነት የዚህች ነው ብሎ መወሰን ግን አንችልም፡፡ ከሳይንሱም ጋር ተያይዞ በዘርፉ ሰፊ ጥናት ያደረጉት ዶክተሮችና ፕሮፌሰሮች ስለ ችግሩ ብዙ የሚሉት ስላለ ያንን ፈልጎ መረዳት ከእኛ የሚጠበቅ ይሆናል፡፡ ስለዚህ እንደ ኢስላም ህብረተሰቡ ይህን እንዲርቀው ይመከራል፡፡

2. ይህን ጉዳይ ከወንዱ ፍትወት እንዲሁም ከሴቷ እንቁላል ለመውሰድ ሂደቱ የእሷንም የሱንም ሀፍረተ ገላ ማየት ይጠይቃል፡፡ በተጨማሪም የኪራይዋ እናት ሀፍረተ ገላን ማየት ግድ ይላል፡፡ ይህ ደግሞ ከላይ ከተጠቀሰው የኢስላም አስተምህሮ ጋር ይጋጫል፡፡ የሌላን ወገን ሀፍረተ ገላን ማየት ክልክል ስለሆነ (ባል የሚስትን ሚስት የባልን ሐፍረተ ገላ ማየት ሲቀር)

ይህን በተመለከተ አሏህ (ሱ.ወ) እንዲህ ይላል፡- ‹‹ለአማኝ ወንዶች እይታቸውን እንዲቆጣጠሩና ብልቶቻቸውንም እንዲጠብቁ ንገራቸው›› (አን ኑር 30)

ይህም አንዱ የሌላውን ሀፍረተ ገላ አይመልከት፡፡ ለዚያም እይታውን ወደ ታች ይመልስ፣ የራሱንም ሀፍረተ ገላ ይሸፍን ማለት ነው፡፡ ከፊል ሙስሊም ምሑራን በጣም ለከፋ ችግር ጥንቃቄ በተሞላበት መልኩ፣ (ሴት ከሆነች አባቷ፣ ባሏ፣ ለአቅመ አዳም የደረሰ ወንድሟ ወይም ልጇ ባሉበት) መታየት እንደሚቻል ብይን ይሰጣሉ፡፡

ይህ አይነቱ ጥንቃቄ ያስፈለገውም፣ ሰይጣን የሰው ልጆች ከአምላካቸው ጋር ያላቸውን ግንኙነት በማቋረጥ የራሱ ግብረ አበሮች እንዳያደርጋቸው በማሰብ ነው፡፡ ተቃራኒ ፆታዎች ከተፈጥሮ መሳሳቡ ጋር የሰይጣን ጉትጎታ ሲጨምር፣ ህገ ወጥ የሆኑ መነካካትና መተያየት ወደ ዝሙት እንዳያመራቸው ነው፡፡

3. የማህፀን ኪራይ የምዕራቡ ዓለም ‹‹ስልጣኔ›› የፈጠረው ግኝት ነው፡፡ በተለይ ከሃይማኖት ህግጋት አንፃር ስልጣኔቸው ደግሞ በከፊል ሰይጣኔ መሆኑ የታወቀ ነው፡፡ ኢስላም ከሳይንስና ቴክኖሎጂ ጋር ሰፊ ግንኙነት ቢኖረውም ሰዎች ከተፈጠሩለት አሏህን የማምለክና ለትዕዛዙ እጅ የመስጠት አላማ ጋር የሚያጋጭን የሳይንስና ቴክኖሎጂ ውጤት አያስተናግድም፡፡

ጠቅለል ባለ መልኩ፣ በስልጣኔ ስም ሁሉንም መከተል ሳይሆን ጥሩና መጥፎ ጎጂና ጠቃሚውን ለይተን ልንጠቀምበት እንደሚገባ ኢስላም ያስተምራል፡፡

ኢስላም እንደ እምነት፣ ለስነ ምግባርና ባህሪ በጥቅሉ ለመልካም ማህበራዊ እሴቶች ትልቅ ዋጋ ይሰጣል፡፡ በተቃራኒው ምዕራቡ ዓለም ደግሞ ለዚህ ጉዳይ ትኩረት ሲሰጥ አይታይም ይላሉ ምሁራኑ፡፡ ስለ ማህፀን ኪራይ ክልክልነት ለማስረዳት ከተነሱት ምክንያቶች፣ ማህበረሰባዊ ቀውሶችን ስለሚያስከትል ሸሪዓዊ (ኢስላማዊ ሕግ) መነሻ የለውም የሚል ነው፡፡ ይልቁንም ማህፀን የሴቷ ሀፍረተ ገላ ስለሆነ ለሕጋዊ ባሏ እንጂ ህጋዊ ባሏ ያልሆነ ወንድ ፍትወት ተቀብላ ልታሳድግበት አይፈቀድላትም፤ ሸሪዓ አምርሮ ይቃወመዋል፡፡

እንደ ኢስላም አንድ ወንድ ያላገባትን ሴት ባይተዋር ለሆነ እርግዝና የመጠቀም መብት የለውም፡፡ በሌላ አገላለፅ አንዲት ሴት ማህፀኗን ላላገባት ወንድ ስታከራይ ሀፍረተ ገላዋን በጋብቻ ላልተሳሰራት ወንድ እየፈቀደች ነው፡፡ እርሷም ለእርሱ እርሱም ለእርሷ ስለማይፈቀዱ ሙሉ ዝሙት ይሆናል ባይባልም ተግባሩ ግን ሙሉ በሙሉ ሐራም ነው፡፡

የእርሱን ፍትወት በእርሷ ውስጥ እንዲያሳድግ ከማድረጉም በላይ፣ ፅንሱ የሚመገበውና የሚያድገው በማህፀን ውስጥ ስለሆነ በጎም ሆነ መጥፎ ተፅዕኖ የሚያርፍበት ከኪራይዋ እናቱ ነው፡፡ ስለሆነም ይህቺ ሴት የጎጂ ልማዶች (መቃም፣ ማጨስ፣ አልኮል መጠጣት ወዘተ…) ተጠቂ ብትሆን ፅንሱ ከጅምሩ ገና ለአደጋ ተጋላጭ ሊሆን ይችላል፡፡ በዚህ ሂደት ላይ ጽንሱን የሚከታተለው ዶክተር፣ ፅንሱ ላይ የአካል ጉዳት ይታያልና የወሊድ ጊዜሽ ከመድረሱ በፊት በቀዶ ጥገና ወጥቶ ጽንሱ መታከም አለበት ቢላት ፈቃደኛ ትሆናለች? የእኔ ለማትለው የሰው ልጅ ትክክለኛዋ እናቱ ብትሆን፣ ልታደርገው የምትችለውን የራሷን ሕይወት ቤዛ የማድረግ ጥያቄ ትቀበላለች?

እዚህ ላይ ሌላ ሳንጠቅስ የማናልፈው ሐሳብ ቢኖር፣ በሕጋዊ ባልና ሚስቶች መካከል በተፈጠረ አንዳች ውስጣዊ ችግር ምክንያት፣ ሚስቲቱ መፀነስ ካልቻለች በሕክምና ድጋፍ የባሏን ፍትወትና የራሷን እንቁላል ውጭ ላይ አሳድጎ ፅንሱን ወደ ራሷ ማህፀን አስገብተው ቢወልዱ የራሳቸው እስከሆነ ድረስ ችግር እንደሌለው ሙስሊም ምሑራን ይገልፃሉ፡፡

4. በእርግዝና ወቅት ያልተጠበቁ እንደ ስኳር፣ የደም ግፊት ያሉ ከባባድ ህመሞች የሚገጥሟቸው ሴቶች አሉ፡፡ እነኚህ በሽታዎች በአፋጣኝ ህክምና ካላገኙ የነፍሰ ጡሯን ህይወት ሊቀጥፉ ይችላሉ፡፡ በተጨማሪም ፅንሱን ለመጠበቅ (ለማዳን) ቀዶ ህክምና (ኦፕራሲዮን) የግድ ሊሆን ይችላል፡፡ ይሁን ኃላፊነትስ የሚወጣው ማን ነው? ይህቺው የኪራይ እናት ወይስ የእንቁላሏ ባለቤት?

ከዚህ ሂደት ጋር ተያይዘው የተለያዩ እንግዳ ነገሮችም ሊከሰቱ ይችላሉ፡፡ እነዚህን የባህል፣ የስነ ልቦና እና ሌሎች ማህበራዊ ቀውሶች እንዴት ነው የምንፈታቸው? ኃላፊነቱን ለየትኛይቱ እናት እንስጣት?

ከዚህ በመነሳት አንድ ድምዳሜ ላይ እንደርሳለን፡፡ ይኸውም ፅሱ በዚያችው በእውነተኛ እናቱ ማህፀን አሏህ (ሱ.ወ) እንደፈቀደለት ይኑር፡፡ እናቱም ጽንሱን የመጠበቅና የመንከባከብና በአሏህ ፈቃድ ጊዜው ሲደርስም የመውለድ ሰብአዊ፣ ሃይማኖታዊና ህጋዊ ግዴታ ይኖርባታል፡፡

‹‹ማህጸን መከራየት ሞግዚት እንደመቅጠር ነው›› የሚሉ አንዳንድ ወገኖች አሉ፡፡ ፍየል ወዲያ… እንዲሉ፣ ይህ ጤነኛ አዕምሮ ሊቀበለው የማይችል ሐሳብ ነው፡፡ አንድን የተወለደ ልጅ ሞግዚት ብትንከባከበው፣ ጡቷን ብታጠባውና ብታሳድገው ልጁ በኪራይ ማህፀን እንደሚያድገው ፅንስ ያለ ተፅዕኖ አይገጥመውም፡፡ ከሞግዚቷ ጋር አለመግባባት ቢፈጠር ወይም በሆነ ምክንያት ጡት ማጥባት ብትከለክለው (ብታቆም)፣ ልጁ በቀላሉ ወደ ወላጅ እናቱ ተመልሶ አስፈላጊውን እንክብካቤ ማግኘት ይችላል፡፡ ህይወቱም ያለምንም እንከን መቀጠል ትችላለች፡፡

5. የማህፀን ኪራይ፣ በትዳር ህይወት ውስጥ በባልና ሚስት መካከል ሌላ ሶስተኛ ሰው ጣልቃ እንዲገባ ሁኔታዎችን ያመቻቻል፡፡ ባል ወደ ኪራይ እናት የሚሳብበት ክፍተት ይፈጠራል፡፡ ይኸው መጤ ፍልስፍና በምዕራቡ ዓለም ውስጥ ብዙ ቀውሶችን እያመጣ ይገኛል፡፡ አንድ ክስተት እንደ አብነት ብናነሳ፡፡ እንግሊዝ ሀገር ውስጥ ዋናዋ እናት ለኪራይዋ እናት ለመክፈል የተስማማችውን 20 ሺ ፓውንድ የማህፀን ኪራይ ጊዜው ደርሶ ልጇ ከተወለደላት በኋላ አልከፍልም በማለት ጭቅጭቅ አስነስታ ነበር፡፡ የኪራይዋ እናትም ‹‹ብሩን ካላመጣሽ ልጁ የእኔ ነው፣ እውቅና አልሰጥሽ›› ብላ ክስ እንደመሰረተችባት ተሰምቷል፡፡ ይህ ወረርሽኝ በእኛ ሀገር ደረጃ ደግሞ ከዚህ የከፋ ችግሮችን ይዞ እንደማይመጣ ምን ያህል እርግጠኞች ነን?  ስለዚህ ልብ ያለው ልብ ይበል ነው ነገሩ፡፡

የወንድ ዘር (ስፐርም) ልገሳ

ስለማህፀን ኪራይ ካነሳን ዘንዳ፣ ጉዳዩ ተቀራራቢነት ስላለው የወንድ ዘር (ስፐርም) ልገሳን በተመለከተ ትንሽ ማለት ወደድን፡፡ እርስዎ እስካሁን ከሰሟቸው ልገሳዎች ‹‹የደም፣ የልብ፣ የኩላሊት፣ የዓይን ልገሳ ወዘተ…›› ባለፈ ወንዶች ፍትወታቸውን በመለገስ ላይ ናቸው፡፡ በዚህ ሂደት ደግሞ አንድ ‹‹ቸር›› የሆነ ወንድ፣ በዚህ ልገሳ ከተሰማራ ስለማንነታቸውና ስለዚህች ምድር ዕጣ ፈንታቸው የማይጨነቅላቸውን ጭራሹንም የማያውቃቸውን የትየለሌ ልጆች ሊያፈራ እንደሚችል መገመት አያዳግትም፡፡

ይህ የማስተዋል አቅሙ ላልከዳው ሰው፣ እጅግ ከባድና ዘግናኝ በመሆኑ ለመስማት እንኳን የሚከብድ ጉዳይ ነው፡፡ ኢስላም በተለይ ወንድ እንደ አባት ለልጆቹ፣ የምድራዊም ሆነ ሰማያዊ ዓለም ሁለንተናዊ ዕጣ ፈንታቸው የሚበጃቸውን የማመላከት፣ የመንከባከብና መሰል ኃላፊነቶች አስረክቦታል፡፡ ወንዱ የአባትነት ሚናውን ለማይወጣበት ይህ አይነት የዘር (ስፐርም) ልገሳ ክልክል ነው፡፡

Health: ቤትዎ ውስጥ ሆነው ሳልዎን የሚከላከሉባቸው 5 ዘዴዎች

$
0
0

ሳል በበርካታ መንገዶች ሊከሰት ቢችልም በዋናነት ግን በአየር ንብረት ለውጥ(በቅዝቃዜ እና ሙቀት)፣ በጉንፋን እና ተያያዥ ህመሞች፣ በአለርጂ፣ በማጨስ እንዲሁም በአስም በሽታ ታማሚዎች ላይ ሊከሰት የሚችል ነው።
couph
አንዳንዴም ለተለያዩ በሽታ የሚታዘዙ መድሃኒቶችን አዛብቶ መውሰድ ፣ አነቃቂ ንጥረ ነገሮችን መጠቀም የሳል መነሾ ሊሆኑ እንደሚችልም የጤና ባለሙያዎች ይገልፃሉ።

ሳል ሲከሰትብን የተለያዩ መድሃኒቶችን መጠቀማችንና ፈውስን መሻታችን ትክክል ቢሆንም ከዚህ በተሻለ ግን በቀላሉ በቤታችን በምናከናውናቸው ተግባራት ራሳችንን በመጠበቅ ሳልን ልንከላከል እንደምንችልም ነው እነዚህ ባለሙያዎች የሚናገሩት።

ለዚህም እነዚህን አምስት ተግባራት በየጊዜው በማከናወን ሳልን መከላከል እንችላለን ሲሉም ይመክራሉ።

1.በቂ ውሃ ማግኘት፣

በአብዛኛው ሳል የሚከሰተው እንደ ጉሮሮ ያለው የመተንፈሻ አካላችን ላይ የውሃ እጥረት ሲከሰትና ሲደርቅ በመሆኑ በየቀኑ በቂ ውሃ መጠጣት ይኖርብናል።

ፈሳሽ ነገሮችን በየጊዜው በበቂ መጠን መውሰዳችን የጎሮሮ ድርቀትን ብቻ ሳይሆን የመከርከር ስሜትንም ለማስቀረት ያግዛል።

2.ትኩስ መጠጦችን ማዘውተር፣

ትኩስ ነገሮችን በተለይም ሻይ በማር አልያም ሻይ በብርቱካን መጠጣት ጉሮሮን ለማፅዳት እና ምቾት እንዲሰማን ለማድረግ እጅግ ተመራጭ ነው።
በአማራጭነት ከማር የተሰራ ከረሜላ (ሎዘንጅስ)ን መጠቀምም ይቻላል።

ከዚህ በተጨማሪም እንደ ሻይ ፣ ወተት ፣ አጃ የመሳሰሉትን መጠጣታችን በጉሮሯችን ያሉ አላስፈላጊ ነገሮችን ለማስወገድ ጠቃሚ ያደርጋቸዋል።

tea1.jpg

3. ሙቅ ሻወር፣

ሙቅ ሻወር መውሰድ በሰውነታችን ላይ የተከማቹ ቆሻሻዎች በላብ መልክ እንዲወገዱ ብቻ ሳይሆን አፍንጫችንም በማፅዳት የአተነፋፈስ ስርዓታችን እንዲስተካከል ይረዳል ፤ ከዚያም በላይ ከሳልና ከተለያየ አለርጂ ለመጠበቅም እጅግ ጠቃሚ ነው።

ከዚህ በተጓዳኝ ስቲም መውሰድም ተመሳሳይ ጥቅሞችን ያስገኝልናል።

4.ጠንካራ ሽታ ያላቸውን ነገሮች ማራቅ፣

ምቾት የሚነሱና ጠንከር ያለ ሽታ ያላቸው ሽቶዎችን አለመጠቀም፣ በተመሳሳይ ጠንካራ ታ ያለው ኤር ፍሬሽነር( አየር መልካም ጠረን እንዲኖረው የመንጠቀመው ስፕሬይ)ን አለመጠቀም፤ እነዚህ ነገሮች ሳይነስ እና ሳልን ሊቀሰቅሱ ስለሚችሉ ጥምንቃቄ ያሻቸዋል ነው የሚሉት አለን ዌስ የተሰኙት የክሌቭላንድ ክሊኒክ የጤና ባለሙያ።

እጅግ የከፋው ሳል ቀስቃሽ ነገር ግን የሲጋራም ሆነ የማገዶ፣ የከሰል፣ የእንጨት ወይም ሌላ ጭስ ሲሆን፥ በተለይም የሲጋራ ጭስ ሳል በመቀስቀስ ረገድ ተወዳዳሪ እንደሌለው ነው የሚነገረው።

ደረጃው ቢለያየም ሁሉም አጫሽ ማለት ይቻላል ለሳል የተጋለጠ ነው፤ ከሳል ለመጠበቅ የተሻለው አማራጭ ሲጋራ ማጨስን ማቆም ብቻ ነው።

5.አቧራን ማስወገድ፣

አቧራ ሳልን ብቻ ሳይሆን እንደ አስም ፣ ሳይነስ የመሳሳሉ ህመሞችን ከሚቀሰቅሱ ነገሮች የሚመደብ ነው።

አካባቢያችን በቂ እርጥበት እንዲኖረው በማድረግ አቧራን መከላከል የምንችል ሲሆን፥ በየዕለቱ ቤታችን በቂ አየር እንዲያገኝ ለተወሰነ ሰዓት መስኮት በመክፈት ምቾት የሚነሳ ሽታን ማስወገድ እንችላለን።

አቧራማ ስፍራዎችን በአረንጓዴ ዕፅዋቶች ማለበስም ሌላው አባሯን የማራቂያ መንገድ ሊሆን ይችላል።

ምንጭ፦ http://www.webmd.com

የአረንጓዴ ሻይ የጤና ጥቅሞች

$
0
0

Green Tea
(በዶ/ር ሆነሊያት ኤፍሬም ቱፈር)
*ለስኳር ህመም
አረንጓዴ ሻይ የስኳር መጠንን መቆጣጠር እና ከምግብ በኋላ በደም ውስጥ የሚገኘው የስኳር መጠን እንዳይጨምር በማድረግ ያግዛል።
*ለልብ ህመም
አረንጓዴ ሻይ የደም ስር ግድግዳዎችን ጤናማና የግፊት መጠን የመቆጣጠር አቅማቸውን ያዳብራል ይህም የደም መርጋት እንዳይከሰትና ለድንገተኛ የልብ ህመም እንዳንጋለጥ ይረዳል።
*ለኮለስቴሮል
መጥፎ ኮሌስቴሮል በመባል የሚታወቀውን በመቀነስ የጥሩ ኮሌስቴሮል መጠን እንዲጨምር ያግዛል።
*ለደም ግፊት
በመደበኛ ሁኔታ አረንጓዴ ሻይን መውሰድ ለደም ግፊት ህመም የመጋለጥ እድልዎን ይቀንሳል።
*ለመደበት
አረንጓዴ ሻይ በውስጡ አእምሮን የሚያፍታቱ እና የሚያረጋጉ ንጥረነገሮችን እንደሚይዝ ጥናቶች ያሳያሉ።
*ለቆዳ
የቆዳ መሸብሸብ እንዳይኖረን የማድረግ አቅም አለው።
*ፀረ ባክቴሪያነት ባህርይ ስላለው ኢንፌክሽኖች እንዳይስፋፉ የማድረግ አቅም እናዳለው ጥናቶች ያሳያሉ።
ጤና ይስጥልኝ

Health: መጾም ከመንፈሳዊው ጥቅም ውጭ ለጤና ያለው 7 በረከቶች

$
0
0

Fiftit

በሙለታ መንገሻ

ለተወሰነ ስዓት ከምግብና ከመጠጥ ዘሮች መራቅ ወይም መጾም ከሀይማኖታዊ ጥቅሙ በዘለለ በርካታ የጤና ጠቀሜታዎች እንዳሉት ጥናቶች ያመለክታሉ።

በሳምንት ውስጥ ቢያንስ ለሁለት ቀናት መጾም ከጉዳቱ ጥቅሙ ያመዝናል ይላል ጥናቱ።

መጾም የሚያስገኛቸውን የጤና ጠቀሜታዎች 

 1.የምግብ መፈጨት ስርዓታችን እንዲስተካከል ይረዳል

ጾመ የምግብ መፈጨት ስርዓታችን እረፍት እንዲኖረው በማደረግ የተረጋጋ እና ጤነኛ የምግብ ዝውውር እንዲኖር ያደርጋል። የምግብ መፈጨት ስርዓታችን መስተካከልም በሰውነታችን ውስጥ ያለን የስብ መጠን ለማቃጠል ይረዳናል።

  2.ትክክለኛው የረሃብ ስሜት እንድንለይ ያግዛል

መጾም የሰውነታችን ሆርሞኖች የተስተካከሉ እንዲሆኑ በማድረግ ትክክለኛውን የረሃብ ስሜት እንድንለይ ያደርገናል።

  3.የጠራ የሰውነት ቆዳ እንዲኖረን ያደርጋል

ጾም ሰውነታችንን ከምግብ መፍጨት ስራው ነጻ ስለሚያደረግ ሆርሞኖቻችን ወደ ሌሎች ስራዎች ይገባሉ።

ለአንድ ቀን ምግብ አለመመገብ ሰውነታችን በውስጡ ያሉትን መርዛማ ንጥረ ነገሮችን እንዲያጸዳ እድል የሚሰጥ ሲሆን፥ በዚህ ጊዜም ኩላሊታችን፣ ጉበታችን፣ ቆዳችን እንዲሁም ሌሎች የሰውነታችን ክፍሎች ተግባራቸውን በአግባቡ እንዲከውኑ ያግዛል።

   4.የአዕምሯችን የማሰብ አቅም ይጨምራል

ጾም አእምሯችን ብሬይን ድራይቭድ ኔውሮትሮፊክ ፋክተር የሚባል ፕሮቲን እንዲያመርት ይረዳዋል። ይህም አእምሯችን ጤነኛ እንዲሆን ያደርጋል።

በተጨማሪም ፕሮቲኑ ከአእምሮ ጋር ተያያዥነት ያላቸው እንደ አልዛይመር እና ፓረኪሰንሰ በሽታዎችን ይከላከላል።

    5. የሰውነት ክብደትን ለመቀነስ ይረዳል
አልፎ አልፎ መጾም የሰውነታችንን ክብደት ለመቀነስ እንደሚረዳ ጥናቶች ያመለክታሉ።

ለተወሰነ ስአት ከምግብ መራቅ ሰውነታችን ውስጥ ያለው የስብ መጠን እንዲቃጠል በማድረግ ክብደት ለመቀነስ ይረዳል።

  6. ጥንካሬ እንዲኖረን ያደርጋል

መጾም የሰውነታችንን ጥንካሬ እንደሚቀንስ ነው በዙዎቻችን የምናስበው። ይሁን እንጂ ጥናቶች የሚያሳዩት የዚህን ተቃራኒ ነው።

ትንሽ መብላት የመኖር እድሜያችንን ለመጨመር ፋይዳው ትልቅ መሆኑም ነው የሚነገረው።
 7. በሽታ የመከላከል አቅምን ይጨምራል

መጾም ሰውነታችን በሽታ የመከላከል አቅሙን እንዲጨምር ይረዳል። ይህም በሽታ አምጪ ነገሮችን እንዲሁም ካንሰር አምጬ ሴሎች በውስጣችን እንዳያድጉ ያደርጋል።

ጥናቱ ላይ እንደተገለጸው እንስሳት በተፈጥሮ በሚያማቸው ጊዜ ምግብ ከመፈለግ ይልቅ ራሳቸውን ከምግብ በማራቅ እረፍት ይወስዳሉ።

ይህም ሰውነታቸው በቀላሉ በሽታን ለመከላከል ይረዳቸዋል።

በተቃራኒው በህመም ወቀት ምግብ ለማግኘት የምንሯሯጠው ብቸኞቹ ፍጡሮች የሰው ልጆች ነን ይላል ጥናቱ።

ምንጭ፦ ideadigezt.com

 

Viewing all 281 articles
Browse latest View live